Get Mystery Box with random crypto!

አሥ ሠላሙ ዐለይኩም ያ ጀመዓህ! ሰዎችን ሸሃዳህ አስይዛችሁ ሥታሠልሙ የሚያሳይ ቪድዮ ሚድያ ላይ | ወሒድ የንጽጽር ማኅደር

አሥ ሠላሙ ዐለይኩም ያ ጀመዓህ!

ሰዎችን ሸሃዳህ አስይዛችሁ ሥታሠልሙ የሚያሳይ ቪድዮ ሚድያ ላይ ማውጣቱ ከጥቅሙ ጉዳቱ ያመዝናል። የሠለሙት ልጆች በዒልም፣ በኢማን፣ በሒክማህ ሳይጠነክሩ ማውጣት አግባብ አይደለም። ከቤተሰባቸው ድብደባ፣ ኩርፊያ እና ነቆራ ሲደርስባቸው ወይ ወደነበሩበት ኩርፍ ይመለሳሉ አሊያም ከቤት ወጥተው ጎዳና ላይ ይወጣሉ። ዞር ብላችሁ ላታያዋቸው ነገር ሚድያችሁን ለማሞቅ ስትሉ የሰውን ሕይወት አታበላሹ! ዲኑል ኢሥላምን መቀበል እና አለመቀበል የጀነት እና የእሳት ጉዳይ ነውና አሏህን ፈርተን ከዚህ ድርጊት እንቆጠብ።

ወጀዛኩሙሏህ ኸይራ

ከዐቃቢ ኢሥላም ወሒድ
https://t.me/Wahidcom