Get Mystery Box with random crypto!

ልጅን አልያዘም በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው፡፡ 39፥4 አላህ ል | ወሒድ የንጽጽር ማኅደር

ልጅን አልያዘም

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው፡፡

39፥4 አላህ ልጅን መያዝ በፈለገ ኖሮ ከሚፈጥረው ውስጥ የሚሻውን ይመርጥ ነበር፡፡ ጥራት ተገባው፡፡ እርሱ አሸናፊው አንዱ አላህ ነው፡፡ لَّوْ أَرَادَ اللَّهُ أَن يَتَّخِذَ وَلَدًا لَّاصْطَفَىٰ مِمَّا يَخْلُقُ مَا يَشَاءُ ۚ سُبْحَانَهُ ۖ هُوَ اللَّهُ الْوَاحِدُ الْقَهَّارُ

አምላካችን አሏህ በእርሱ ባሕርይ ላይ መውለድ እና መወለድ የለውም፥ "አሏህ ወለደ" ያሉት እነርሱም በእርግጥ ውሸታሞች ናቸው፦
112፥3 አልወለደም፤ አልተወለደምም፡፡ لَمْ يَلِدْ وَلَمْ يُولَدْ
37፥152 «አላህ ወለደ፡፡» አሉ፥ እነርሱም በእርግጥ ውሸታሞች ናቸው፡፡ وَلَدَ اللَّهُ وَإِنَّهُمْ لَكَاذِبُونَ
43፥15 ከባሮቹም ለእርሱ ቁራጭን ልጅ አደረጉለት፡፡ ሰው በእርግጥ ግልጽ ከሓዲ ነው፡፡ وَجَعَلُوا لَهُ مِنْ عِبَادِهِ جُزْءًا ۚ إِنَّ الْإِنسَانَ لَكَفُورٌ مُّبِينٌ

ከአንዱ አምላህ ባሕርይ ባሕርይን ወስዶ፣ ከአካሉ አካልን ወስዶ፣ እርሱን አህሎና መስሎ ከእርሱ ወጣ፣ ተወለደ፣ ተገኘ በማለት አሏህን ወላዲ መሢሑን ተወላዲ በማድረግ ለአሏህ ቁራጭን አደረጉለት።
ፈጣሪ እምቅድመ ዓለም "ወለደ" ከሚሉት በተጨማሪ አንዳንድ የክርስትና አንጃዎች "ፈጣሪ ልጅ ይዟል" የሚል አስተምህሮት በጥንት ጊዜ ነበረ፥ ለምሳሌ፦ ኖላዊ ዘሄርማስ(የሄርሜኑ እረኛ)፣ ኢቦናይታውያን ክርስቲያን እና በበባዛንታይኑ ቴዎዶስ እና በአንጾኪያው በጳውሎስ ሳምሳጤ የተጀመረው ዳይናሚክ ሞናርኪዝም"Adoptionism" ሁሉም "ፈጣሪ ልጅ ይዟል" ብለዋል። ነገር ግን አሏህ ምንም ልጅን አልያዘም፦
19፥88 «አር-ረሕማንም ልጅን ያዘ» አሉ፡፡ وَقَالُوا اتَّخَذَ الرَّحْمَـٰنُ وَلَدًا
23፥91 አላህ ምንም ልጅን አልያዘም፡፡ ከእርሱም ጋር አንድም አምላክ የለም፡፡ مَا اتَّخَذَ اللَّهُ مِن وَلَدٍ وَمَا كَانَ مَعَهُ مِنْ إِلَـٰهٍ

"ኢተኸዘ" اتَّخَذَ የሚሉት "ወለደ" وَلَدَ ከሚለውን እሳቤ ለመሸሽ ያመጡት እሳቤ ነው፥ "መያዝ" እና "መውለድ" ልዩነት አለው፦
28፥9 የፈርዖንም ሚስት፦ "ለእኔ ለአንተም የዓይኔ መርጊያ ነው፤ አትግደሉት፡፡ ሊጠቅመን ወይም "ልጅ አድርገን ልንይዘው ይከጀላልና" አለች፡፡ وَقَالَتِ امْرَأَتُ فِرْعَوْنَ قُرَّتُ عَيْنٍ لِّي وَلَكَ ۖ لَا تَقْتُلُوهُ عَسَىٰ أَن يَنفَعَنَا أَوْ نَتَّخِذَهُ وَلَدًا
12፥21 ያም ከምስር የገዛው ሰው ለሚስቱ፦ «መኖሪያውን አክብሪ! ሊጠቅመን ወይም "ልጅ አድርገን ልንይዘው" ይከጀላልና» አላት፡፡ وَقَالَ الَّذِي اشْتَرَاهُ مِن مِّصْرَ لِامْرَأَتِهِ أَكْرِمِي مَثْوَاهُ عَسَىٰ أَن يَنفَعَنَا أَوْ نَتَّخِذَهُ وَلَدًا

የፈርዖን ሚስት ለፈርዖን ስለ ሙሣ፦ "ልጅ አድርገን ልንይዘው ይከጀላል" ስትል "እንወልደዋለን" ማለቷ አይደለም፥ የተወለደን ልጅ ማደጎ አርጎ መያዟን የሚያመለክት ነው። በተመሳሳይ ዮሡፍን ያም ከምስር የገዛው ሰው ለሚስቱ፦ "ልጅ አድርገን ልንይዘው ይከጀላል" ሲላት "እንወልደዋለን" ማለቱ አይደለም፥ የተወለደን ልጅ ማደጎ አርጎ መያዟን የሚያመለክት ነው። እዚህ ድረስ ከተግባባን አሏህ በማደጎ ልጅ መያዝ አይፈልግም፥ ቢፈልግ ኖሮ ግን "ከ-ሚፈጥረው" ውስጥ መርጦ ይይዝ ነው፦
39፥4 አላህ ልጅን መያዝ በፈለገ ኖሮ "ከ-ሚፈጥረው" ውስጥ የሚሻውን ይመርጥ ነበር፡፡ ጥራት ተገባው፡፡ እርሱ አሸናፊው አንዱ አላህ ነው፡፡ لَّوْ أَرَادَ اللَّهُ أَن يَتَّخِذَ وَلَدًا لَّاصْطَفَىٰ مِمَّا يَخْلُقُ مَا يَشَاءُ ۚ سُبْحَانَهُ ۖ هُوَ اللَّهُ الْوَاحِدُ الْقَهَّارُ