Get Mystery Box with random crypto!

ሰላም እንዴት ናችሁ ልናደርግ ያሰብነውን ድጋፍ በተመለከተ እንደ ግብዓት ይሆነን ዘንድ፣ ዛሬ በ | ዋድላ ልማት ማኅበር

ሰላም እንዴት ናችሁ

ልናደርግ ያሰብነውን ድጋፍ በተመለከተ እንደ ግብዓት ይሆነን ዘንድ፣ ዛሬ በዋድላ ወረዳ ከሚገኙት 4 የሁለተኛ ደረጃ እና መሠናዶ ት/ቤቶች ውስጥ የኮኑን እና የጋሸናውን የጎበኘን ሲሆን የቋና እና የሓሙሲት ት/ቤቶች ርዕሳነ መምህራንን ደግሞ በስልክ ለማውራት እና ውድመቱንም ለመረዳት ችለናል፡፡

በመሆኑም ት/ቤቶቹ አሁን ላይ ባላቸው ቁመና ብዙ ጉድለቶች ያሉባቸው ቢሆንም መማር ማስተማር ሒደቱን ከማሳለጥ አንፃር፣ ለተማሪዎች የሚሆን አጋዥ መፅሐፍት ላይ ርብርብ ቢደረግ ጠቃሚ እንደሚሆን ገልፀውልናል፡፡

ከዚህ የመስክ ጉብኝት በህዋላ የ1 ደርዘን ደብተር ለአንድ ተማሪ ፕሮግራም እና የመፅሐፍ ግዥዎቹ በአስቸኳይ በዚህ ሳምንት ውስጥ እንዲጠናቀቅ ወስነናል፡፡

ስለሆነም በነገው እለት(ማክሰኞ10-05-2014) ለጊዜው አ.አ ለሚገኘው የማህበራችን ሊቀ-መንበር ጀማል ፈለቀ ከማህበሩ የባንክ አካውንት ላይ ወጪ የሚደረግ አንድ መቶ ሺህ ብር የምናስረክብ ሲሆን ገንዘቡም አ.አ ላይ በሰፊው እየተንቀሳቀሱ ከሚገኙት ከነ #መስፍን #ሙሉጌታ ፣ #አበበ አባተ እና #ቴዲ ተፈራ ጋር በመሆን እነሱ በሸገር ከሰበሰቡት ጋር የሚጨምር እና ለደብተር መግዣ ብቻ የሚውል ነው፡፡

☞ለግንዛቤ ይሆን ዘንድ ከዚህ በፊት ለደብተር መግዣ ተብሎ በውጭ ከሚኖሩ የማህበራችን አባላት 70ሺህ ብር አከባቢ የተላከ ሲሆን 30ሺህ ብር ደግሞ ከማህበሩ ካዝና ላይ ተቆንጥሮ የተጨመረ ነው፡፡ ይህ የሆነበት ምክኒያት ደግሞ በዚህ አመት ብዙ እጃችን የሚጠብቁ ተማሪዎች ስለበዙ ነው፡፡