Get Mystery Box with random crypto!

ዋድላ ልማት ማኅበር

የቴሌግራም ቻናል አርማ wadilaye — ዋድላ ልማት ማኅበር
የቴሌግራም ቻናል አርማ wadilaye — ዋድላ ልማት ማኅበር
የሰርጥ አድራሻ: @wadilaye
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 169
የሰርጥ መግለጫ

የዚህ ስብስብ ዋና አላማ የዋድላ ልጆችና ወዳጆች እራሳቸውን በቢዝነስና በበጎ አድራጎት ማህበራት ውስጥ በማሳተፍ የወጡበትን ማህበረሰብ እየረዱ (እያሻሻሉ) እራሳቸውን መለወጥ ነው።
ስብስቡ አላማውን ማሳካት ይችል ዘንድ እያንዳንዱ አባል ሙሉ እራሱን ለለውጥ አሳልፎ ይስጥ (ለውጥን ብቻ ያልም፤ ለለውጥ መኖርንም ይልመድ)።

Ratings & Reviews

1.50

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

0

3 stars

0

2 stars

1

1 stars

1


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች

2022-05-14 20:28:04 ሰላም እንዴት ናችሁ የተወደዳችሁ...!

የማህበሩን አጠቃላይ የስራ ሪፖርት በpdf አስረን እዚሁ ቴሌግራም ላይ እና በጠቅላላ ጉባኤ ስብሰባችንም ጭምር አቅርበንላችሁ ነበር፡፡

ለአብነት ያህል፡
ማህበሩ ህጋዊ እውቅና አግኝቶ ከተቋቋመበት ከታህሳስ 6/2010 ዓ.ም ጀምሮ ባሉት ተከታታይ አመታት ከ1.5ሚሊዮን ብር በላይ እንዳንቀሳቀሰ፤

በዚህም ማህበሩ ከነበረው አጠቃላይ በጀት፡
-69.25 % ለትምህርት
-11.07 % ለጤና
-10.02 % ለግብርና
-0.16 %ለስራ እድልፈጠራ
-9.5% ለስራ እድል ፈጠራ እንደተጠቀመ አሳውቀናችሁ ነበር፡፡

ጠቅለል ሲል በዚህ አሀዛዊ መረጃ መሠረት ማህበሩ 90.5 ፐርሰንቱን ለድጋፍ ስራ ያዋለ ሲሆን፣ ቀሪውን 9.5 ፐርሰንት ደግሞ ለስራ ማስኬጃ ወጭ አድርጓል፡፡

ማህበሩ ይህን ያህል በጎ ስራወች ላይ በብርቱ የተሳተፈ ቢሆንም ከጦርነቱ ማግስት ያለው የእናንተ ተወዳጅ አባላቶቻችን ተሳትፎ ግን ከወርሀዊ የገንዘብ መዋጮ ጀምሮ በሀሳብም አለን እስካለማለት ደርሷል እና ማህበራችን የአደጋ ስጋት አንዣቦበታል እና እስኪ እንወያይበት....?
አክባሪችሁ....!
369 views17:28
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-01 16:50:16
448 views13:50
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-04-04 17:09:38 Hey! Join our video chat: https://t.me/+iyMDyAYvEjo1MWM0
774 views14:09
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-03-06 12:16:04 Hey! Join our video chat: https://t.me/+iyMDyAYvEjo1MWM0

አጭር ውይይት በማኅበራችን ወቅታዊ ሁኔታ ላይ

ከቀኑ 10 ሰዓት!
817 viewsedited  09:16
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-01-17 23:00:22 ሰላም እንዴት ናችሁ

ልናደርግ ያሰብነውን ድጋፍ በተመለከተ እንደ ግብዓት ይሆነን ዘንድ፣ ዛሬ በዋድላ ወረዳ ከሚገኙት 4 የሁለተኛ ደረጃ እና መሠናዶ ት/ቤቶች ውስጥ የኮኑን እና የጋሸናውን የጎበኘን ሲሆን የቋና እና የሓሙሲት ት/ቤቶች ርዕሳነ መምህራንን ደግሞ በስልክ ለማውራት እና ውድመቱንም ለመረዳት ችለናል፡፡

በመሆኑም ት/ቤቶቹ አሁን ላይ ባላቸው ቁመና ብዙ ጉድለቶች ያሉባቸው ቢሆንም መማር ማስተማር ሒደቱን ከማሳለጥ አንፃር፣ ለተማሪዎች የሚሆን አጋዥ መፅሐፍት ላይ ርብርብ ቢደረግ ጠቃሚ እንደሚሆን ገልፀውልናል፡፡

ከዚህ የመስክ ጉብኝት በህዋላ የ1 ደርዘን ደብተር ለአንድ ተማሪ ፕሮግራም እና የመፅሐፍ ግዥዎቹ በአስቸኳይ በዚህ ሳምንት ውስጥ እንዲጠናቀቅ ወስነናል፡፡

ስለሆነም በነገው እለት(ማክሰኞ10-05-2014) ለጊዜው አ.አ ለሚገኘው የማህበራችን ሊቀ-መንበር ጀማል ፈለቀ ከማህበሩ የባንክ አካውንት ላይ ወጪ የሚደረግ አንድ መቶ ሺህ ብር የምናስረክብ ሲሆን ገንዘቡም አ.አ ላይ በሰፊው እየተንቀሳቀሱ ከሚገኙት ከነ #መስፍን #ሙሉጌታ ፣ #አበበ አባተ እና #ቴዲ ተፈራ ጋር በመሆን እነሱ በሸገር ከሰበሰቡት ጋር የሚጨምር እና ለደብተር መግዣ ብቻ የሚውል ነው፡፡

☞ለግንዛቤ ይሆን ዘንድ ከዚህ በፊት ለደብተር መግዣ ተብሎ በውጭ ከሚኖሩ የማህበራችን አባላት 70ሺህ ብር አከባቢ የተላከ ሲሆን 30ሺህ ብር ደግሞ ከማህበሩ ካዝና ላይ ተቆንጥሮ የተጨመረ ነው፡፡ ይህ የሆነበት ምክኒያት ደግሞ በዚህ አመት ብዙ እጃችን የሚጠብቁ ተማሪዎች ስለበዙ ነው፡፡
959 views20:00
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-01-16 22:07:31 ሰላም ተወዳጆች
በኮን የሚገኘውን ቢሯችን ነገ ሰኞ ወይም ማክሰኞ በይፋ ከፍተን ስራ እንጀምራን ብለን አስበናል(እስካሁን ስራ ያልጀመርነው የበፊቱ ቢሯችን በር እና መስኮቱ የወደመ በመሆኑ አገልግሎት ለመስጠት እማይመች ስለሆነ ነው)፡፡

በመሆኑም በኮን የምትገኙ አባላቶቻችን እጅግ በጣም ብዙ፣ ድርብርብ እና በአፋጣኝ መሰራት ያለባቸው፦
-እንደ ደብተር እና እስኪብርቶ የማደል
-ሙሉ በሙሉ እና በከፊል ለወደሙት በዋድላ ለሚገኙት አራቱም የ2ኛ ደረጃ እና መሠናዶ ት/ቤቶች፣ ለቴክኒክና መያ ኮሌጁ፣ ለሆስፒታሉ የሚደረጉትን ድጋፎች ጨምሮ የተለመደውን የበጎ አድራጎት ስራወች ስላሉብን ቢሮ እየመጣችሁ ሀሳብ አስተያየታችሁን እንድታካፍሉን ይሁን!

ከኮን ውጭ ያላችሁ ተወዳጅ አባላቶቻችን ደግሞ እዚሁ ቴሌግራም ላይ ሀሳባችሁን አካፍሉን
704 views19:07
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-01-13 07:54:02 ማኅበራችን በንግድ ባንክ ያለውን ገንዘብ ለማሳወቅ ያክል...! እርዳታ ለአረጋችሁ ሁሉ እናመሰግናለን
693 viewsedited  04:54
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-01-11 22:38:46 በትላንትናው እለት ማለትም በ03-05-2014 ሰኞ በተካሄደው የዋድላ አንድነት በጎ አድራጎት ማህበር አባላት መሀል መደበኛ ያልሆነ አስቸኳይ ውይይት የተደረገ ሲሆን፣ ያለፈውን በጥቂቱ ገምግመን ለወደፊቱ የሚሆን አንዳንድ ምክረ ሀሳቦችን አስቀምጠናል፡፡

☞በውይይቱ የተነሱ ነጥቦች፡-

-በዋ/አ/በጎ/አድ የባንክ አካውንት ውስጥ ያለውን የገንዘብ መጠን ለማህበሩ አባላት ማሳወቅ
-ቀጣይ የበጎ አድርጎት ስራወችን መለየት
-ለማህበሩ መጠናከር ዋናው የሰው ሀብታችን በመሆኑ አባላትን የማብዛቱን ስራ ማጠናከር
-አባላቶቻችን የበለጠ ለማጠናከር እና ስራወችን የተቀላጠፈ ለማድረግ በአዲስ አበባ ተጨማሪ ቅርንጫፍ ማድረግ ስለማስፈለጉ
-የስብሰባ ሰዐትን እንዳሻ የመወሰን አባዜን ማስተካከል እንደሚገባ
-ለመከላከያ ተብሎ ከውጭ ወዳጆቻችን ለመከላከያ ድጋፍ ተብሎ የተሰበሰበው ገንዘብን ተከትሎ የሚነሱ ጥያቄዎች በመበራከታቸው፣ ይኸ ገንዘብ ወደ ማህበራችን አካውንት የገባ አለመሆኑን እና በአጠቃላይ ከማህበራችን ጋር እንደማይገናኝ ማሳወቅ አስፈላጊ መሆኑን! በሚሉ ዋና ዋና ጉዳዮች ላይ ለመወያየት ችለናል፡፡
641 viewsedited  19:38
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-01-02 21:36:14 ታሪክ ስለአይረሴ እና ዘመን አይሽሬ ክስተቶቹ ሁሉ እማኝ ሊያደርገን እነሆ በመመድረኪያው ፊት ሲያነብረን፣ ምስክር ይሆን ዘንድ ይሔን ከተብን፡፡
* *
ብዙ ህልም እንዳልነበር ሲሆን
ያቀድነው ባጭር ሲቀር
እናቶች ደረት ሲደቁ
አባቶች ሲተክዙ
እህቶቻችን ሲሸማቀቁ
ወንድ ልጅ ሲያቀረቅር....ያኔ እኛ በኮን ነበርን


የተዘራው በአረር ሲቆላ
ሰብሉ በባሩድ ሲታጠን
ለጋው ያለጊዜው እንኩቶ ሲሆን... አሁንም በዚያ ነበርን

ክቡሩ የሰው ገላ አፈር ብርቅ ሆኖበት የአራዊት
መራኮቻ ሲሆን...
ወንዞች እና መንገዶች በደም ሲቀልሙ.... ያኔም በዚያ ነበርን

ምድር ነጎድጓድን በሚያስንቅ ጩኸት ስትደነቁር
በመድፍ እና ሞርታር ቁና ስትሆን
በድሮን እና ጀት ጥቃት ስትቃትት... ይሔኔም በኮን ነበርን

የምንኖረው ሁሉ ህልም ይመስል ነበር፣ በፍፁም መንቃት የማይቻልበት ህልም፡፡ አምላክ ግን ሊያስተምረን ብቻ ፈልጓል እና ለታሪክ አቆየን፡፡
እናንተም "ማን ያርዳ የቀበረ
ማን ይናገር የነበረ " ከማለት ዳናችሁ

ከቶማስ☜
667 views18:36
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-12-23 20:02:49 ጤና ይስጥልን ለእህትና ወንድሞቻችን።

እንደሚታወቀው ወራሪው ኃይል በወረዳችን ዉስጥ መሽጎ በመቆየት ዘርፈ ብዙ ጥፋቶችን በወገኖቻችን ላይ አድርሷል። ይኸ ወራሪ ኃይል ወደ አማራ ክልል ዉስጥ ከገባበት ቀን ጀምሮ ከባድ ጥፋትን ሲያደርስ እነደነበር ይታወቃል። ታዲያ ይኸን ጉዳት ያደረሰው በእያንዳንዱ አካባቢ ውስጥ ባሉ ባንዳዎች አማካኝነት ጭምር በመታገዝ መሆኑን መረጃዎች እየወጡ ይገኛል። በእኛው ወረዳም ጥቂት ተመሳሳይ ዓይነት ባህርይ የተላበሱ ባንዳዎች መኖራቸው እየተነገረ ይገኛል። ስለሆነም በመረጃ የተደገፈ ወይም የተረጋገጠ የባንዳነት ሥራ ሲሰሩ የነበሩ ካሉ እነሱን የማጋለጡ ሥራ በጥንቃቄ ሊሰራ ይገባዋል።

ከወራሪው ኃይል ጋር ሲሰሩ የነበሩ ባንዳዎች ሊጋለጡ ይገባልና ጠቃሚ የምንለውን መረጃ ሁሉ በጥንቃቄ ማጣራትና ማሰባሰብ የሁላችንም ኃላፊነት መሆን አለበት።

መልካም ምሽት ለሁላችንም ይሁን።

በዚህ አጋጣሚ በውድ ወንድማችን በአበበ አባተ አማካኝነት ከወንድሞቻችን ዘንድ የተሰበሰበው ድጋፍ ሊደነቅ የሚገባው ነው። ሥንተባበር ያምርብናል
681 viewsedited  17:02
ክፈት / አስተያየት ይስጡ