Get Mystery Box with random crypto!

ትምህርተ አበው

የቴሌግራም ቻናል አርማ fgonfa — ትምህርተ አበው
የቴሌግራም ቻናል አርማ fgonfa — ትምህርተ አበው
የሰርጥ አድራሻ: @fgonfa
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 354
የሰርጥ መግለጫ

ይህ የአባቶቻችንን ትምህርት የምንማማርበት መንፈሳዊ ገጽ ነው።
ለሃሳብ አስተያየቶ @fgonfa

Ratings & Reviews

4.00

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

2

3 stars

0

2 stars

0

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች

2022-07-09 13:11:53 "ሁልጊዜ በጌታ ደስ ይበላችሁ" ፊል 4፥4

አንተ ደስታህን ከሰዎች አትጠብቅ ሰዎች ባስደሰቱህ ቅጽበት ያስከፉካል ምድራዊ የሆነ ደስታ ፍጹም አይደለም ዘለቄታም ላይኖረው ይችላል ደስታህ በዚህ ምድር አይሁን ይልቁኑ ፍፁም ደስታ ከላይ መሆኑን አስተውል (ያዕ1፥17) ስለዚህ ደስታህን ከሰዎች አትጠብቅ ደስታህንም በዚህ ምድር አላፊ በሆነ ቁሳቁስም አትወስን።

በጌታ ግን ሁሌ ጊዜ ደስ ይበልህ በማግኘትም በማጣትም፤በማትረፍም በመክሰረም፤
በመራብም በመጥገብም......
በሁሉ ደስ ይበልህ ዛሬ ያስከፋህ ማጣት ነገ ያስደስትሃልና ተስፋ ሰንቅ እንጂ ተስፋ አትቁረጥ እግዚአብሔር በሙላት ብቻ የሚመሰገን አምላክ አይደለም በማጣትም ጭምር እንጂ (ኢዮ 1፥17) እግዚአብሔር በመስጠት ብቻ የሚያስደስት አይደለም እኛ ልጆቹ ቀኝና ግራችንን የማናውቅ ነንና በመከልከልም ጭምር ነው (ማቴ 20፥22) ስለዚህ ሁል ጊዜ በጌታ ደስ ይበልህ።

በእግዚአብሐር ለመደሰት ጎተራህ ሙሉ መሆን አይጠበቅበትም፣
በህይወትህ ስኬታማ መሆን አይጠበቅብህም፣መሻቶችህ በሙሉ ሊሟሉ አይገባቸውም፣ብቻ ምንም ሳይኖረንም በጌታ ደስ ይበልህ ምንም የሌለን ሲመስለን ባለ ፀጎች ነንና (2ቆሮ 6፥15) ስለዚህ ቅዱስ ጳውሎስ እንደነገረን ሁሌ ጊዜ በጌታ ደስ ይበለን።

ማስተዋል እየተሳነህ ነው እንጂ የሉኝም ከምትላቸው ቁሳቁሶች ይልቅ በነፃ የተሰጠህ ዋጋ የማንትከፍልባቸው ብዙ ጸጋዎች አሉህ እስኪ አስተውል ማየት የሚያስከፍል ቢሆን፣መስማት የሚያስከፍል ቢሆን፣የሚተነፍሰው አየር የሚያስከፍል ቢሆን....... የምድር ኑሮህ ህልውና ውስጥ ይወድቅ ነበር። ምን አለኝ የሚለውን ትተህ በተሰጡህ ጸጋዎች ደስ ተሰኝተህ አመስግን።

ይልቅስ ሁላችንም ከነብዩ ዕንባቆም ጋር አብረን ደስተኞች እንሁን
"ምንም እንኳ በለስም ባታፈራ፥ በወይንም ሐረግ ፍሬ ባይገኝ፥ የወይራ ሥራ ቢጐድል፥ እርሾችም መብልን ባይሰጡ፥ በጎች ከበረቱ ቢጠፉ፥ ላሞችም በጋጡ ውስጥ ባይገኙ፥እኔ ግን በእግዚአብሔር ደስ ይለኛል፤ በመድኃኒቴ አምላክ ሐሤት አደርጋለሁ"
ዕንባቆም 3፥17

"የክርስቶስን ምሥጢር እንድንነግር እግዚአብሔር የቃሉን ደጅ ይከፍትልን ዘንድ ስለ እኛ ደግሞ ጸልዩ፤
ልናገር እንደሚገባኝ ያህል እገልጠው ዘንድ ጸልዩልኝ" ቆላ 4፥3



ዲ/ን ፍቃዱ ጎንፋ (ዘፍቁረእግዚእ)
ሐምሌ2፥2014ዓ.ም
44 viewsፍቅር በ ኢትዮጵያ, 10:11
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-28 12:33:55
ሀሌ ሉያ ለቤተክርስቲያን
ሃነጻ ልዑል ለቤተክርስቲያን

ሰኔ 21 ቀን ለመቅደሷ መቅደስ የተሰራበት ዕለት ነው አማናዊት መቅደስ ድንግል ማርያም በስሟ መቅደስ በዛሬው ዕለት ታንጾላታል።በመቅደስ ጽላት እንደሚያድር አማናዊ ጽላት እግዚእነ አምላካችን ኢየሱስ ክርስቶስ ማህጸኗን ዓለም አድርጎ 9 ወር ከ5 ቀን የከተመባት አማናዊት መቅደስ ድንግል ማርያም ናት።

ይህች አማናዊት መቅደስ በታህሳስ 3 ስንክሳር እንደምናነበው የኖረችውም በሶሎሞን ቤተመቅደስ ነው የሚደንቅ ነው እርሷ ራሷ ቤተመቅደስ ኑሮዋ እና እድገቷም በቤተመቅደስ ዛሬ ደግሞ በስሟ ቤተመቅደስ ታንጾላታል።

በቤተክርስቲያን ሊቃውንት አስተምህሮ መሠረት ቤተመቅደስ ቤተመቅደስ ነው ለመባል ከሚያስፈልጉት መሰረታዊ ነገሮች አንዱ በውስጡ ታቦት መኖሩ ነው ቅዱስ ኤፍሬም ሶርያዊ ደግሞ "አንቲ ውእቱ ታቦት" ይላታል

ታቦት :-ማደርያ ማለት ነው በውስጡ ጽላት ይቀመጥበታልና በቀድሞው ጽላት ደግሞ በእግዚአብሔር ጣት 10ሩ ቃላት ተጽፈውበታል አምላካችን ክርስቶስ በማህፀኗ ያደረባት አማናዊት ታቦት ደግሞ ድንግል ማርያም ነች መቅደስ ያሏትን ታቦት ብለውም ያመሰጥሯታል ስለዚህ በአዲስ ኪዳን ቤተክርስቲያን ቤተክርስቲያን ለመባል ድንግል ማርያም ልትኖርበት ያስፈልጋል።


ለዚህ ነው ሊቁ ስል እርሷ እንዲህ ያለው
"ዕበያ ለድንግል ኢይትከሃል ለተነግሮ (የድንግልንንና ገናናነትና ሊናገሩት አይቻልም)


ሰኔ 21/2014
ዲ/ን ፍቃዱ ጎንፋ (ዘፍቁረእግዚእ)
ከዮሐንስ ማርያም
157 viewsፍቅር በ ኢትዮጵያ, edited  09:33
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-24 13:43:16 “በአንድ ልብ ሁኑ፥ በሰላም ኑሩ፥ የፍቅርና የሰላምም አምላክ ከእናንተ ጋር ይሆናል።” 2ኛ ቆሮ 13፥11


ክርስትና ከዘር ከብሔር ከጎሳ በላይ ነው ክርስቲያኖች የኔ የምንለት ዘር ብሔር ጎሣ የለንም ርስታችን በዓይን ያልታየች በእጅ ያልተሰራች ሰማያዊት ናት የዚህ ምድር ኑሮአችን ልክ እንደ ኪራይ ቤት ነው ወደ ዘላለማዊ ርስታችን የምንጓዝበት ወረፋ እስከሚደርሰን ብቻ የምንቆይበት ጊዜያዊ ነው።ዘራችን ከክርስቶስ ነገዳችን ከሰማያውያን መላእክት ዘንድ ነው እንደ ሰው በዚህ ምድር ብንኖር በሰማይ እንደ መላእክት የምንሆን ነን::(ማቴ 22፥30)

ክርስቲያን የሰውን ደም በከንቱ አያፈስም የቃየልን ታሪክ ያውቃልና (ዘፍ 4፥12) ክርስቲያን የምስኪን እናትን እንባ በከንቱ እንዲፈስ ምክንያት አይሆንም እናቱን እንዲያከብር መጽሐፍ ይዘዋልና (ዘጸ 20፥12) ክርስቲያን አንተ ከዚህ ወገን ነህ አንተ ከዚህ ነው የመጣከው እያለ በብሔሩ ምክንያት ሰውን የሚያፈናቅል የሰውን ደም በከንቱ የሚያፈስ አይደለም ከሁሉ ጋር በፍቅር እንዲኖር ታዟልና (ሮሜ 12፥18)

ገዳዮች የዘነጉት ትልቁ ጉዳይ እነሱም ሟች መሆናቸውን ነው የምስኪናንን ደም በከንቱ ያፈሰሰ ደሙ ሳይፈስ አይቀርም የእናቶቻችን እንባ እንደ ራሄል ጸባኦትን ያንኳኳ ጊዜ ፍርድ ከሰማያዊው ጌታ ይመጣል ያኔ የምስኪናኑ ደም በምድር ያቅበዘብዛል በሰማይ ርስት ያሳጣል የዛሬ ባለ ግዜ አፈናቃዮች ነገ ከመንግሥተ እግዚአብሔር ይፈናቀላሉ የዛሬ ደም አፍሳሾች ነገ ደማቸው ይፈሳል የፍጥረቱ ደም በከንቱ ፈሶ ዝም የማይል አምላክ በተነሳ ጊዜ ለሁሉም እንደየሥራቸው ይከፍላል።


እባካችሁ ለግል ምድራዊ ጥቅማችሁን ስትሉ የምታፋጁን የተማራችሁ መሃይሞች ተውን ተውን ተውን ።እንደ ጥንቱ እንደ አባቶቻችን ልዩነታችንን ተቻችለን አንድነታችንን አጽንተን እንኑር ተውን ተውን ተውን።

እማምላክ ድንግል ማርያም በአስራት ሃገርሽ በምድርሽ በኢትዮጵያ ላይ የእናቶቻችን እንባ በከንቱ ፋሷል እና አንቺ አብሽልን።አዛኝቱ የወገኖቻችንን እልቂት በቃ በይን ከመሐሪው ልጅሽ አማልደሽ ምህረትን አስጭን

ዲ/ን ፍቃዱ ጎንፋ (ዘፍቁረእግዚእ)
ሰኔ 17/2014
147 viewsፍቅር በ ኢትዮጵያ, 10:43
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-22 21:07:51 ፀሀዩን ስንፈራ ተቃጠልን ብለን
ዝናብም በጊዜው ጎርፍ ሆኖ ጨረሰን
እቤቱ ይቅር በለን ራራልን ለእኛ
ከምድር አተናል ደገኛ እረኛ
ደማችን በምድር ፈሰስ እንደዋዛ
አምላክ ሆይ እግዘን ልብ እንድንገዛ
እማምላክ ምድርሽን ርስትሽን እያት
ካንቺ በቀር እኮ ተስፋ ምንም ያላት።

(በየቦታው በግፍ ለተገደሉት ወገኖቻችን ምህረትን ለሁላችን መጽናናትን የድሉን። ሰላማችንን ይመልስልን)

ዲ/ን ፍቃዱ ጎንፋ (ዘፍቁረእግዚእ)
ሰኔ 15/2014 ዓ.ም
139 viewsፍቅር በ ኢትዮጵያ, 18:07
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-21 17:32:44 "ሐሜትን መስማት የጆሮአችን ጠላት ነው አላማሁም ወይም በሐሜት አልተባበርኩም ልትል ትችላለህ ነገር ግን ሐሜትን መስማት በራሱ ኃጥያት ነው።ሐሜትን መስማት እያደር በሰዎች ላይ ወደ መፍረድ በእነርሱም ላይ የተሳሳተ አመለካከትን ወደ ማሳደርና ለሌሎችም ስለ እነርሱ ክፉነት ወሬን ወደ መንዛት ያደርሳል።

አንድ ሰው ስለ እኔ ለሰው እንዲህ ብሎ እንዳወራብኝ ሰማሁ የሚለው ጭንቀት ለብዙ ወጣቶች ትልቅ ራስ ምታት ነው።አንድ ሰው ወደ አንተ መጥቶ እገሌ ከጀርባህ እንዲህ ብሎ እያማህ ነው ብሎ ከነገረህ ከዚያ ሰው ጋር ተጨማሪ ውይይት ማድረግ የለብህም ያልተረዳከው ነገር ቢኖር ከጀርባህ እገሌ አምቶሃል ብሎ እየነገረህ ያለው ሰው ራሱ ሐሜተኛ ያለውን ሰው ከጀርባው እያማው መሆኑን ነው።

ለዚህ መፍትሄው ምንድነው መታማትህን ለሚነግርህ ሰው ባማኝ ሰው ፊት መተህ ይህንን ነገር ንገረኝ በለው ካልነገረህ ዋሽቶሃል ማለት ነው።

አስታውስ ሰው እስካልተረጋገጠበት ድረስ ንጹህ ነው።የማይጠቅም ተራ ወሬን ከመስማት ጆሮዎችህን ጠብቅ"

አባ አትናትዮስ (ዘግብጽ)
144 viewsፍቅር በ ኢትዮጵያ, 14:32
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-17 12:37:01
177 viewsፍቅር በ ኢትዮጵያ, 09:37
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-15 09:20:36 እየጦሙ አለመጦም


(ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ)

ተወዳጆች ሆይ እየጦሙ የጦምን ፍሬ የማያገኙበት ሁኔታ እንዳለ ታውቁ ዘንድ እወዳለሁ።ይህስ እንደምን ነው? ያላችሁኝ እንደሆነ:-

ከምግብ ሥጋ ተከልክለን ከምግበ ኋጥያት ያልተከለከልን እንደሆነ።

ከጥሉላት ርቀን ነዳያንን ያልጎበኘን እንደሆነ።

ወይን ከመጠጣት ታቅበን በክፋ መሻት ከመስከር ያልራቅን እንደሆነ።

ጀምበር እስክትጠልቅ ድረስ ከእህል ከውሃ ርቀን በአይናችን ክፉ ከማየት ያልጦምን እንደሆነ።

ስለዚህ እየጦሙ እንዲህ አለመጦም እንዳለ ተረዱ።


ዲ/ን ፍቃዱ ጎንፋ (ዘፍቁረእግዚእ)
ግንቦት 8/2014
165 viewsፍቅር በ ኢትዮጵያ, 06:20
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-09 16:31:26
187 viewsፍቅር በ ኢትዮጵያ, 13:31
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-07 18:05:27 " ለሁሉ ጊዜ አለው”መክ 3፥1

የሰው ልጅ በሕይወቱ አራት ዘመናትን ያሳልፋል የመጀመርያው ዘመነ ነፋስ ሲሰኝ ይሄውም የህጻንነት ዘመን ነው ሁለተኛው ዘመነ እሳት ሲሆን ይሄውም የወጣትነት የማዕከላዊነት የዕድሜው ክፍል ነው ሦስተኛው የውሃነት ዘመን ሲሆን ይህም የጎልማሳነታችን ወቅት ነው የመጨረሻው የመሬትነት ዘመን ሲሆን ይሄም ወደ ምድር የምንመለስበት ነው ታድያ እነዚህ ዘመናት የሚፈራረቁት ግዜያቸውን ጠብቀው በጊዜያቸው ነው ወዳጄ ዳዴ ሳይል የቆመ የለም ለሁሉም ጊዜ አለው።

በምድር የምናያቸውን ፍጥረታት እግዚአብሔር ለመፍጠር 6ቀን ፈጅቶበታል ይህን ስታስብ ምን ይሰማሃል? ሁሉን ከዓይን ጥቅሻ ፈጥኖ መከወን የሚቻለው ጊዜ የማይወስነው የጊዜ ባለቤት እግዚአብሔ 22 ሥነ ፍጥረታትን በ6 ቀን ፈጠረ?ወዳጄ በቅጽበት ማድረግ የማይሳነው አምላክ እንዲህ ያደረገው የጊዜን ምንነት ሲያስረዳ ነው እንደውም ሊቃውንት የሙሴን ቃል ይዘው ሲያመሰጥሩ ቀዳሚው ፍጥረት ጊዜ እና ሥራ ነው ይላሉ"በቀዳሚ እግዚኣብሔር ግብረ ሰማየ ወምድረ" ዘፍ 1፥1

በሕይወት ማድረግ የሚገባህን በጊዜው አድርግ ከጊዜህ ቀድመህም ዘግይተህም አትገኝ ሁሉን በጊዜህ አድርግ ጊዜህንም በአግባብ ተጠቀም ከወተቱ አጥንቱን አታስቀድም በወጣትነትህ ምርኩዝ ለመያዝ አትመኝ ሁሉን ማድረግ በሚገባህ ጊዜ አድርግ ነገ እንዳትቆጭ ዛሬ በእድሜህ መስራት ያለብህን ሰርተህ እልፍ ነገ እንዳትፀፀት ዛሬ መስራት ከማይገባህ ግብር ራቅ።


የምታስበው ሁሉ ባይሆንልህ ተስፋ አትቁረጥ ይህንን አስብ "ለሁሉም ጊዜ አለው" እግዚኣብሔር የሚመጣበት ጊዜው ዛሬ ላይሆን ይችላል አንተ እንዲኖርህ የምትመኛቸውን ነገሮች ሲኖሩህ ምን ማድረግ እንዳለብህ አስብ በጊዜህ የምትሰራውን ብቻ ሥራ አንተ ድርሻህን ከተወጣህ ነገሮችን መፈጸም የፈጣሪ ድርሻ ነውና የእርሱን ጊዜም ጠብቅ።

ጊዜህን በአግባብ ተጠቀም ሁሉ ዛሬ ካልሆነ አትበል የዛሬን አድርገህ በትላንት ትዝታ በነገ ተስፋ ትኖራለህን የአንተ ስጦታ ዛሬ ናት ዛሬ ማድረግ የሚገባህን ብቻ አድርግ ምናልባት ነገ ላትኖር ትችላለህ ብትኖርም የነገውን ነገ ትደርስበታለህ ብቻ ዛሬ የምታስቀምጠው ዛሬ የምትሰራው ነገ የምትፀፀትበት እንዳይሆን ለማድረግ ጣር።

አታርፍድም አትቸኩልም
“ለሁሉ ዘመን አለው፥ ከሰማይ በታችም ለሆነ ነገር ሁሉ ጊዜ አለው።”
መክብብ 3፥1


ግንቦት 30/2014ዓ.ም
ዲ/ን ፍቃዱ ጎንፋ (ዘፍቁረእግዚእ)
174 viewsፍቅር በ ኢትዮጵያ, 15:05
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-04 22:38:49
ባለመኪናዎች እንኳን ደስ አላችሁ።

የቤተክርስቲያናችንን ልጆች እናበረታታለን ወንድማችን ቢኒ ከመኪና ጋር በተያያዘ ከታች የተገለፁትን አገልግሎቶችን ብትፈልጉ እንደ ቤተክርስቲያን ልጅነቱ በታማኝነት እንደ ባለሙያነት በጥራት ሊሰራሎት ዝግጁ ነው ይደውሉለት።

አድራሻ ቅዱስ ዮሐንስ ቤተክርስቲያን በር ላይ(ሰባራ ባብር)
169 viewsፍቅር በ ኢትዮጵያ, 19:38
ክፈት / አስተያየት ይስጡ