Get Mystery Box with random crypto!

'ሐሜትን መስማት የጆሮአችን ጠላት ነው አላማሁም ወይም በሐሜት አልተባበርኩም ልትል ትችላለህ ነገር | ትምህርተ አበው

"ሐሜትን መስማት የጆሮአችን ጠላት ነው አላማሁም ወይም በሐሜት አልተባበርኩም ልትል ትችላለህ ነገር ግን ሐሜትን መስማት በራሱ ኃጥያት ነው።ሐሜትን መስማት እያደር በሰዎች ላይ ወደ መፍረድ በእነርሱም ላይ የተሳሳተ አመለካከትን ወደ ማሳደርና ለሌሎችም ስለ እነርሱ ክፉነት ወሬን ወደ መንዛት ያደርሳል።

አንድ ሰው ስለ እኔ ለሰው እንዲህ ብሎ እንዳወራብኝ ሰማሁ የሚለው ጭንቀት ለብዙ ወጣቶች ትልቅ ራስ ምታት ነው።አንድ ሰው ወደ አንተ መጥቶ እገሌ ከጀርባህ እንዲህ ብሎ እያማህ ነው ብሎ ከነገረህ ከዚያ ሰው ጋር ተጨማሪ ውይይት ማድረግ የለብህም ያልተረዳከው ነገር ቢኖር ከጀርባህ እገሌ አምቶሃል ብሎ እየነገረህ ያለው ሰው ራሱ ሐሜተኛ ያለውን ሰው ከጀርባው እያማው መሆኑን ነው።

ለዚህ መፍትሄው ምንድነው መታማትህን ለሚነግርህ ሰው ባማኝ ሰው ፊት መተህ ይህንን ነገር ንገረኝ በለው ካልነገረህ ዋሽቶሃል ማለት ነው።

አስታውስ ሰው እስካልተረጋገጠበት ድረስ ንጹህ ነው።የማይጠቅም ተራ ወሬን ከመስማት ጆሮዎችህን ጠብቅ"

አባ አትናትዮስ (ዘግብጽ)