Get Mystery Box with random crypto!

'ሀሰተኛ መረጃ ነው!' በሉን እንጂ! ከቀናት በፊት ጋዜጠኛ ሰለሞን ሹምዬን ለማፈን ወደቤቱ ያመራ | የ አማራው ድምፅ (ፋኖ)

"ሀሰተኛ መረጃ ነው!" በሉን እንጂ!

ከቀናት በፊት ጋዜጠኛ ሰለሞን ሹምዬን ለማፈን ወደቤቱ ያመራው የአንባገነኖች ቡድን ፥ ጋዜጠኛውን በአጋጣሚ ከቤቱ ሲያጡት ፥ ከቤት ያገኟትን ታናሽ እህቱን በመያዣነት አግተው እስር ቤት መውሰዳቸውን ሰምተን "አጀብ ጉድ!" ብለን ነበር፡፡

"የባስ አለ …..!" እንዲሉት ነገር ፥ ዛሬ ደግሞ በምስራቅ ጎጃም ዞን የጁቤ ከተማ ነዋሪ የሆነው ፋኖ አበባው እጁን ለመንግስት ታጣቂዎች ይሰጥ ዘንድ ፥ ይህን የሰውን ልጅ ክፋትና ደግነት እንኳ የማያውቅ እንቦቀቅላ ህፃን አግተው ወደፖሊስ ጣቢያ በማስገባት አስረውታል የሚል ፥ በድንቃድንቅ መዝገብ የሚሠፍር ጉድ አሰምተውናል!

መቼም የሆነ ግፍ በጣም ገኖ ጫጫታ ሲበዛ ወይም ፥ ስውር ሴራዎች በአደባባይ ሲጋለጡ ፥ ግፍና መከራውን የተሸከመውን ህዝብ "ዝም ብለህ አትንጫጫ! መረጃው ሀሰተኛ ነው!" ሲሉ አንዳች ሀፍረት አይሰማቸውምና ነገ በሌላ ነውር ዳግም እስክንገናኝ "ሀሰተኛ መረጃ ነው!" ይበሉንና ይረፉት እንጂ! በወንጀላቸው ይወንጅሉን! በነውራቸው ያነውሩን እንጂ!

የህዝብ እምባና ደም ተጠራቅሞ መአበል እስከሚሆን ድረስ ፥ ያሻችሁን ብታደርጉ ምን አለባችሁ! ማንስ ሊጠይቃችሁ!

https://t.me/voice_of_amhara_FANO