Get Mystery Box with random crypto!

Vision-power Page

የቴሌግራም ቻናል አርማ vision224 — Vision-power Page V
የቴሌግራም ቻናል አርማ vision224 — Vision-power Page
የሰርጥ አድራሻ: @vision224
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 495

Ratings & Reviews

3.00

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

0

3 stars

2

2 stars

0

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች

2023-05-16 08:35:41 *** ትኩረትህን ዛሬ ላይ አድርግ! ***

በየቀኑ ከእንቅልፍህ ስትነቃ ትላንት ባላሳካሃቸው ጉዳዮች በመፀፀት አይሁን። ይልቁንም ዛሬ ምን ልታሳካ እንደምትችል በመሰብ ንቃ!

ትላንት እና የትላንት ዕቅዶች በመልካምም ይሁን በመጥፎ ላይመለሱ አልፈዋል። ስለ ትላንት በማሰብ የምትለውጠው ምንም ነገር የለም። ዛሬ ግን በእጅህ ላይ ነው ያለው። እናም ብዙ ልታሳካቸው የምትችላ ቸው ጉዳዮች አሉህ። ትኩረትህን ሁሉ እነዚህ ላይ ብቻ አድርግ።

ስኬታማ እና የተባረከ ቀን ይሁንላችሁ!
36 viewsTefera Muluneh, 05:35
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-16 08:34:31
መልካም አዲስ ቀን!
Tefera M.
— telegram: @Vision22
36 viewsTefera Muluneh, 05:34
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-15 08:22:25 *** “ትዕግስት መራራ ብትሆንም ፍሬዋ ግን ጣፋጭ ነው” ***

ሰዎች ወርቅ ለማግኘት ብዙ ይቆፍራሉ፤ ብዙ ይደክማሉ፤ በመጨረሻም ግን በጣም ጥቂት ወርቅ ያገኛሉ። ያቺ ከብዙ ልፋትና ድካም በኋላ የተገኘችዋ ወርቅ ግን ትንሽ ብትሆንም ወርቅ ናት።

የስኬት መንገድም እንዲሁ ነው። የምንፈልገውን እስክናሳካ ብዙ መውጣትና መውረድ፤ ብዙ ፈተናና መውደቅ ሊያጋጥመን ይችላል። በመጨረሻ የምናገኘው ግን በጣም ጣፋጭ ይሆናል። የመጨረሻውን ጣፋጭ ፍሬ ለማግኘት ግን ይሄንን ሁሉ መታገስና በጽናት ማለፍን ይጠይቃል።

ስኬታማ እና የተባረከ ቀን ይሁንላችሁ!
130 viewsTefera Muluneh, 05:22
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-15 08:21:22
መልካም አዲስ ቀን!
Tefera M.
— telegram: @Vision22
129 viewsTefera Muluneh, 05:21
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-14 07:32:27 *** ከእንቅልፍህ የሚቀቅስህ ማነው? ***

ሁልጊዜ በማለዳ ከአልጋህ ላይ አስፈንጥሮ የሚያስነሳህ ግብ ይኑርግ!

በህይወትህ ልታሳካው የምትፈልገው የህይወት ዓላማ እና ግብ ሲኖርህ ጠዋት የሚቀሰቅስህ ሰው ወይም ‘አላርም' አያስፈልግህም። ራሱ ያስቀምጥከው ህልምህ ይቀሰቅስሃል።

የህይወት ዓላማ እና ግብ ከሌለህ ግን በጠዋት ብትነሳም ባትነሳም ለውጥ የለውም። እናም ተኝተህ ታረፍዳለህ፤ በየቀኑ ቀስቃሽ ትፈልጋለህ፤ … ህይወት ተደጋጋሚና አሰልቺ ትሆንብሃለች። ከዚህ ለመውጣት ዋነኛው መፍትሔ ለምን እንደምትኖር ማወቅ እና ይህንኑ ለማሳካት ዓላማና ግብ ማስቀመጥ ነው።

ስኬታማ እና የተባረከ ቀን ይሁንላችሁ!
157 viewsTefera Muluneh, 04:32
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-14 07:29:14
መልካም አዲስ ቀን!
Tefera M.
— telegram: @Vision22
171 viewsTefera Muluneh, 04:29
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-13 08:20:21 *** የራሳችንን ሻማ እንለኩስ ***

ሁሉም ሰው አነሰም በዛ የራሱ የሆነ ሻማ አለው። ይህ ሻማ ሲበራ ለሌሎች ብርሃን ይሆናል። የሁላችን ሻማ ቢበራ ደግሞ የበለጠ ብርሃን ይበራል። ግን ብዙ ጊዜ እኔ ብቻየን ምን ላመጣ እችላለሁ፤ እንዴትስ ለውጥ ማምጣት እችላለሁ፤ … እንላለን።

ከእኔ የሚጠበቀው በእጄ ያለውን ሻማ መለኮስና ለሌሎች ብርሃን መሆን ነው። ምክንያቱም በእጃችን ያለው ሻማ እንዲበራ የሚጠባበቁ በርካታ ሰዎች በዙሪያችን አሉ፤ የእኛን ብርሃን አይተው የራሳቸውን ለማብራት መንገዱን የምንገልጥላቸው ሰዎችም ይኖራሉና፤ ሁላችንም በእጃችን ያለውን ሻማ እናብራ!

ስኬታማ እና የተባረከ ቀን ይሁንላችሁ!
172 viewsTefera Muluneh, 05:20
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-13 08:18:45
መልካም አዲስ ቀን!
Tefera M.
— telegram: @Vision22
160 viewsTefera Muluneh, 05:18
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-12 08:17:39 *** ትልቁ ክብር! ***

"በመኖር ውስጥ ትልቁ ክብር ያለው ባለመውደቃችን ሳይሆን በወደቅን ቁጥር መነሳት መቻላችን ላይ ነው።" - ኔልሰን ማንዴላ

በህይወት ጎዳና ብዙ መውደቅ ሊያጋጥም ይችላል። ስኬት ወይም ክብር የሚባለውም በዚህ ጎዳና ላይ ምንም ሳይወድቁ መጓዝ ሳይሆን በወደቅንበት ጊዜ ሁሉ መነሳት እና ያለመታከት ጉዟችንን መቀጠል መቻላችን ነው።

እናም ወዳጄ ሆይ በመውደቅህ አትዘን፤ ይልቁንም ጉዞህ እንዳይቋረጥ ጥረትህን መቀጠሉ ላይ ትኩረትህን አድርግ።

ስኬታማ እና የተባረከ ቀን ይሁንላችሁ!
190 viewsTefera Muluneh, 05:17
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-12 08:16:28
መልካም አዲስ ቀን!
Tefera M.
— telegram: @Vision22
180 viewsTefera Muluneh, 05:16
ክፈት / አስተያየት ይስጡ