Get Mystery Box with random crypto!

አሸንዳ/የነፃነት በዓል/ አሸንዳ ዘመን መለወጫ ሁለት ሳምንት ሲቀረው አዲሱን ዘመን በደስታና በሀ | ቱንቢ ላቭ ሚዲያ 💟

አሸንዳ/የነፃነት በዓል/

አሸንዳ ዘመን መለወጫ ሁለት ሳምንት ሲቀረው አዲሱን ዘመን በደስታና በሀሴት ለመቀበል በብሩህ ተስፋ የሚከበር በዓል ነው።

ፍቅርና ይቅር ባይነት መረዳዳት እንዲሁም ሌሎች መልካም እሴቶች ይንፀባረቁበታል።

ፍቅርንና ትብብርን ከመስበክ ባለፈ በተግባር የሚታይበትም መድረክ ነው።

በዋናነትም ይሄ በዓል ልጃገረድ የሆኑ ሴቶች ነፃነታቸውን የሚያውጁበት፣ ከሌላው ጊዜ በተለየ ከቤታቸው ወጥተው የሚውሉበት ልዩ የሆነ በዓል ነው።

ነገር ግን ሴቶቹ ይህንን ነፃነታቸውን ማስጠበቅ የሚችሉት በዓሉ ተከብሮ እስከሚያልቅበት ቀን ብቻ ነው።

ለዘላለም የሚሆን ነፃነት ያውቃሉ?

አዎን ለዘለዓለም የሚሆን ነፃነት ኢየሱስ ክርስቶስ ዘንደ ይገኛል።

በሀጢያት ምክንያት ከገባንበት እስራት ተላቀን በነፃነት እንድንኖር ክርስቶስ ስለ እኛ የሀጢያትን ዕዳ ሁሉ ከፈለ።ፍቅሩንና መልካምነቱን በመስቀል ላይ ሞቱ አሳየን።

ይህንን ውድ ጌታ በማመንና በማወቅ ለዘላለም የሚሆን ነፃነት ይገኛል።

“እንግዲህ ልጁ አርነት ቢያወጣችሁ በእውነት አርነት ትወጣላችሁ።”
— ዮሐንስ 8፥36