Get Mystery Box with random crypto!

ኦርቶዶክሳዊ መጻሕፍት እና ጽሑፎች

የቴሌግራም ቻናል አርማ tseomm — ኦርቶዶክሳዊ መጻሕፍት እና ጽሑፎች
የቴሌግራም ቻናል አርማ tseomm — ኦርቶዶክሳዊ መጻሕፍት እና ጽሑፎች
የሰርጥ አድራሻ: @tseomm
ምድቦች: ሃይማኖት
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 3.02K
የሰርጥ መግለጫ

በዚህ ቻናል ላይ አበው ያስረከቡንን መጻሕፍትን እንዲሁም መንፈሳዊያት ጽሁፎችን ለምዕመናን ተደራሽ ማድረግ ነው።
https://www.youtube.com/@Tsegaye-kiflu ሰብስክራይብ ያድርጉ

Ratings & Reviews

3.00

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

1

3 stars

1

2 stars

1

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች

2022-08-31 17:58:31

94 views14:58
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-30 16:33:17

131 views13:33
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-30 07:07:20 + ድንገት የተበጠሰ ገመድ +

የደብረ ዳሞ ገዳም በገመድ ብቻ የሚወጣ እጅግ ጥንታዊ ገዳም ነው:: ይህንን አቡነ አረጋዊ በዘንዶ የወጡትን ታላቅ ገዳም ለመውጣት በግንባታው ወቅት በአፄ ገብረ መስቀል የተሠራ ደረጃ ነበረው:: ሆኖም አቡነ አረጋዊ ደረጃውን ዳህምሞ (አፍርሰው) ብለው በማዘዛቸው እስከ አሁን ድረስ በገመድ የሚወጣበት ገዳም ሆኖአል::

የደብረ ዳሞ መውጫ ገመድ እጅግ ወፍራም ሲሆን እስከ አሁን ድረስ በብዙ ሺህዎች የሚቆጠሩ ሰዎች ተንጠላጥለው ወጥተው ወርደውበታል:: ይህ እጅግ ወፍራም ገመድ ለዘመናት ሲያገለግል ተበጥሶ ሰው ጥሎ አያውቅም:: በታሪክ የማይዘነጋና መሃል ላይ የተበጠሰበትና ሰው የጣለበት ቀን አለ:: (የዲያቢሎስ መተናኮል ነው የሚል አለ)

በዚያ ቀን በተበጠሰው ገመድ ላይ የወረደው መንገደኛ ጻድቁ አባ ተክለ ሃይማኖት ነበሩ:: መነኮሳቱን ተሰናብተው በዚያ ገመድ ሲወርዱ ተበጥሶ የማያውቀው ገመድ ድንገት ተበጠሰ:: ከላይ የሚያዩት አባቶች ቁልቁል እያዩ በድንጋጤ ጮኹ:: ሆኖም እግዚአብሔር ለጻድቁ የብርሃን ክንፍ ሠጥቶአቸው ከተበጠሰው ገመድ ተለይተው እንደ መልአክ በርረው ሁለት ሺህ ክንድ ያህል ወርደው መሬት ላይ አረፉ:: ባረፉባት ሥፍራም ቤተ ክርስቲያን ተሠራባት::

ወዳጄ በሕይወትህ ድንገት የተበጠሰ ገመድ የለም? ሳትጠብቀው የተበጠሰ ገመድ ማንም ላይ ሳይበጠስ አንተ ላይ የጨከነ ገመድ የለም? ምን ዓይነት ገመድ አትበለኝ:: የእንጀራ ገመድ የኑሮ ገመድ የትምህርት ገመድ የፈለግኸው ገመድ በለው:: እሱን ተጠምጥመህ ይዘህ ወደ አንዳች ቦታ ለመድረስ የተማመንክበት ተስፋህን ሙሉ በሙሉ የጣልክበት ገመድ የለም? ድንገት ተበጥሶ ዙሪያው ገደል አልሆነብህም? ሰዎች ማንም ላይ ያልተበጠሰ ገመድ አንተ ላይ ሲበጠስ አይተው "ምኑ ዕድለ ቢስ ነው?" ብለው የተደነቁብህ እንደ ቅዱስ ጳውሎስ "ከባሕር አደጋ ተርፎ ዕባብ የነደፈው እንዴት ኃጢአተኛ ቢሆን ነው?" ብለው በትዝብት ዓይን እንዲያዩህ ያደረገ በሕይወትህ ሳታስበው ተበጥሶ ዙሪያው ገደል የሆነ ሥፍራ ላይ የጣለህ የሕይወት ገመድ ይኖር ይሆናል::

በዕድልህ አትማረር በሕይወትህ ድንገት የሚበጠስብህ ገመድ የምትወድቅበት ሳይሆን ክንፍ አውጥተህ የምትበርበት ነው:: ፈጣሪ የተማመንክበትን የምታየውን ገመድ እንዲበጠስብህ ከፈቀደ ያላየኸውን ክንፍ ሊሠጥህ እንጂ ሊጥልህ አይደለም:: የሕይወትህን ገመድ የተበጠሰበትን ቀን "እግዚአብሔር ለመልካም አሰበው" ብለህ እንደ ዮሴፍ ታመሰግንበታለህ::
ገመድህን የሚበጥሰው ከገደል ሊጥልህ ሳይሆን በክንፍ አብቅሎ ሊተክልህ ነው:: የሚተክልህ በበረሃ ሳይሆን በእግዚአብሔር ቤት ውስጥ ነው:: ተራ ተክል የምትሆን እንዳይመስልህ:: የሃይማኖት ተክል (ተክለ ሃይማኖት) ትሆናለህ:: ተክለ መንፈስ ቅዱስ ተክለ ወልድ ተክለ አብ ትሆናለህ:: አብ የተከለው ደግሞ አይነቀልም!

ዲያቆን ሄኖክ ኃይሌ
ታኅሣሥ 24 2013 ዓ ም

T.me/tseomm

የዩቲዩብ ገጻችንን ለመከታተል ይህንን ይጫኑ

https://youtube.com/channel/UC_fJjDRvh_n9IWY-3LtyLRA

መዝሙር ለማዳመጥ



185 viewsedited  04:07
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-30 07:07:16
131 views04:07
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-29 19:27:12 + ጊዮርጊስ ሆይ ከእኛ ወገን ነህን? +

ወደ አድዋ ከዘመተው ሕዝብ አብዛኛው ባዶ እግሩን ነበር:: ዳዊት ጎልያድን ሊዋጋ ሲወጣ ከያዛት በትር በቀር አብዛኛው ሰው መሣሪያ አልታጠቀም:: አብዛኛው ዘማች ባዶ እጁን የዘመተው ሁለት ነገር አስቦ ነው:: መሣሪያ ባይኖረውም በውጊያው መካከል ከጠላት ጦር መሣሪያ ነጥቄ እዋጋለሁ አለዚያም ከሚወድቁት ላይ መሣሪያ አንሥቼ እዋጋለሁ ብሎ ነበር:: በውጊያው ታንክ በጎራዴ እስከመማረክ ያደረሳቸውም ይህ ቆራጥነታቸው ነበር::

ለመንፈሳዊ ጥንካሬያቸው ደግሞ ምሥጢሩ አብራ የዘመተችው የቤተ ክርስቲያን ጸሎት እና ንጉሡ በድንግል ማርያም ስም ምለው የሠጡት አደራ ነበር:: ለተገፉ የሚቆመው ሰማዕቱ ጊዮርጊስም በግፍ ባሕር አቁዋርጠው በደሃ ሕዝብ ላይ እሳት ከሚያዘንቡት ከአባቱ ዘመዶች ከሮማዊያን ጋር ሳይሆን እንደ ዳዊት በትር ይዘው በእግዚአብሔር ስም ከወጡት ባለማተቦች ጋር በምልጃው ተሰልፎ ዋለ::
በዚያች ዕለት አንድ ጣሊያናዊ ቅዱስ ጊዮርጊስን አግኝቶ ኢያሱ ቅዱስ ሚካኤልን እንደጠየቀው "ከእኛ ወገን ነህ ወይንስ ከጠላቶቻችን ወገን ነህ? " ብሎ ቢጠይቀው ኖሮ "እኔ አሁን ከእግዚአብሔር ተልኬ መጥቻለሁ ይልቅስ የቆምክባት መሬት ኢትዮጵያ የተቀደሰች ናትና ጫማህን ከእግርህ አውልቅ" ባለው ነበር::

የዐድዋ ዘማቾች ጾመኞች ነበሩ:: እንግሊዝም ጣሊያንም ሰይጣን ይመስል ኢትዮጵያን የተዋጉአት በዐቢይ ጾም ነበር:: "ወድቀህ ብትሰግድልኝ መንገድና ፎቅ እሰራልሃለሁ" ያለንን ጣሊያን አባቶቻችን "ሒድ አንተ ጣሊያን የራስህን እንጂ የእኔን አታስብምና" ብለው ድል ነሡት::

ዘማቾቹ የምግብ እጥረት ቢኖርም እንኩዋን ጾሙን ትተን ካልበላን አላሉም:: ድንገት መሞቴ አይቀር ብበላ ይሻለኛል ሳይሉ ተዋግተው ድል ተቀዳጁ:: እኛ በሰላም ጊዜ የምንተወውን ጾም እነርሱ በጦርነት ላይም ሆነው አልተዉትም:: በዚያ ድል ሀገሪቱ ለዐርባ ዓመት ከጦርነት ስታርፍ ለዕድሜ ዘመንዋ ደግሞ ከቅኝ ግዛት ዐረፈች::

ቅኝ ግዛት ብንገዛ ኖሮ ደሃ አንሆንም ነበር የሚል ሰው አይጠፋም:: ይህንን አሳብ የብዙ አፍሪካውያን ሀገራት ጆሮ አይስማው:: ዛሬ ነጻ ከወጡም በኁዋላ በባርነት ሕሊና የሚሰቃዩ ብዙ ናቸው::

ብዙ በፈረንሳይ የተገዙ የምዕራብ አፍሪካ ሀገራት ዛሬም ድረስ በአደራ አስተዳደር በፈረንሳይ በእጅ አዙር ይተዳደራሉ:: በተባበሩት መንግሥታት ሳይቀር ቅኝ ገዢዎቻቸውን ተወካይ ሁነኝ ብለው የሚልኩ ሀገራት አሉ::
ዛሬም ድረስ በአንዳንድ አፍሪካ ሀገራት ጥቁሮች ሊስተናገዱ በተሰለፉበት ሱፐር ማርኬት አንድ ነጭ ከመጣ ሰልፍ ሳይይዝ ቅድሚያ ይስተናገዳል:: (በዓይኔ ያየሁት ነው)

ዛሬም ድረስ ብዙ አፍሪካዊያን ጥቁር በአስተሳሰብ ከነጭ በታች ነው ብለው ያምናሉ:: በዜኖ ፎቢያ የገዛ ወንድሞቻቸው አፍሪካውያንን የሚያሰቃዩ ደቡብ አፍሪካውያን ነጭ ሰፈር ግን ዝር አይሉም:: ሂሳብ ስታሰላ ሲያዩህ እንኩዋን አንተ ጥቁር ሆነህ እንዴት ያለ ካልኩሌተር መደመር ቻልክ የሚሉ ሰዎች ተፈጥረዋል::

በአውሮፓ በአሜሪካ ተወልደው አድገው ስኬታማ የሆኑት ጥቁሮች እንኩዋን የቤተሰብ ስማቸው ላይ አያቶቻቸውን በባርነት የገዛው ነጭ ገዥ ስም አብሮ ስለሚለጠፍ የዕድሜ ልክ የበታችነት ይሰማቸዋል:: አባቶቻችን ከብዙ ጣጣ አድነውናል አሁን ራሳችን የምንፈጥረውን ችግር ቢያዩ ለማመን የሚቸገሩ የሚሆኑትም ዘር ሳይለዩ አብረው የተዋደቁት ጀግኖች ናቸው:: ቅዱስ ጊዮርጊስ ዛሬም ቤሩታዊት ኢትዮጵያን ከዘረኝነትና ጥላቻ ደራጎን ይታደጋት ዘንድ የምንማጸንበት ጊዜ ነው:: የካቲት 23 ከዐድዋ ድል ጋር የቃና ዘገሊላ ተአምር የተፈጸመበት ጥንተ ዕለትም ነው:: ወይን ያለቀባት ሀገራችንን ወላዲተ አምላክን ጠርታ ውኃ ልጆችዋን በወይን እንድታስቀይረን የምንለምንበት ዘመን ነው::

ዲያቆን ሄኖክ ኃይሌ
የካቲት 23 2012 ዓ ም
ወላይታ ሶዶ ኢትዮጵያ

ለተጨነቀች ነፍስ ዕረፍት የሆነው የእግዚአብሔር ቃል ለሁሉ ይዳረስ ዘንድ :: እኔም ለእናንተ ከሰበክሁ በኁዋላ የተጣልሁ እንዳልሆን ስለ እኔ ዘንድ ጸልዩ! ሌሎች እንዲያነቡትም የሚከተሉት አድራሻዎች Like እና Share ያድርጉ



168 views16:27
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-29 10:01:15 ‹‹መድኃኔ ዓለም ክርስቶስ በሌሊት የተቀደደ ቀሚስ ለብሶ ታየኝ ፤ እኔም ‹ጌታዬ ሆይ ልብስህን ማን ቀደደው?› ብዬ ጠየቅሁት፡፡ ‹አርዮስ ልብሴን ቀደደው ፤ ከባሕርይ አባቴ (ከአብ) ለይቶኛልና ፤ እንዳትቀበለው ተጠንቀቅ› አለኝ›› አላቸው፡፡ ተፍጻሜተ ሰማዕት ቅዱስ ጴጥሮስ በእኔ ደም መፍሰስ የክርስቲያኖች ደም እንደጎርፍ መፍሰሱ ይቁም ብሎ ተስሎ በሰማዕትነት አርፏል፡፡ ጌታችን ‹ልብሴን ቀደደው› ብሎ ለዚህ ፓትርያርክ እንደነገረው የጌታችን የባሕርይ አምላክነት ላይ የክህደት ቃልን የሚናገሩ ሰዎች ሁሉ ሮማውያን ወታደሮች ያልቀደዱትን የክርስቶስን ቀሚስ እንደቀደዱ ይቆጠራል፡፡

ሊቁ ቅዱስ አውግስጢኖስ ደግሞ የጌታችንን ልብስ አለመቀደድ ቤተ ክርስቲያንን ለሚከፋፍሉ ሰዎች ማስተማሪያ አድርጎ ተጠቅሞበታል፡፡ እንደ ሊቁ ትምህርት ያልተቀደደችውና ከላይ ጀምሮ ወጥ የሆነችው ቀሚስ ከዚህ ዓለም ያልሆነችው የቅድስት ቤተ ክርስቲያን ምሳሌ ናት፡፡ ለአራት የተከፈለው ደግሞ የምታስተምረው ወንጌል ነው፡፡ ወንጌል ሊከፋፈልና ለዓለም ሁሉ ሊዳረስ ይችላል፡፡ ወንጌል በዘር በቋንቋ በሀገር አይገደብምና የክርስቶስ ወታደሮች የሆኑ ካህናትና መምህራነ ቤተ ክርስቲያን ወንጌልን ተከፋፍለው ለዓለም ማከፋፈል አለባቸው፡፡

አብያተ ክርስቲያናት በየሀገራቱ ቢቋቋሙ ፣ አህጉረ ስብከቶች ቢስፋፉ ፣ ሊቃነ ጳጳሳት ፣ ካህናት ፣ ዲያቆናት ፣ ሊቃውንት ፣ ሰባክያን በቁጥር በዝተው ፣ በቦታም ተከፋፍለው ቢያገለግሉ እጅግ መልካም ነው፡፡ ቅዱስ ጳውሎስ ‹‹በሁሉ ጎዳና … ክርስቶስ ይሰበካል ስለዚህም ደስ ብሎኛል›› እንዳለ የመምህራን መብዛት የወንጌል መስፋፋት እጅግ ደስ የሚያሰኝ ነው፡፡ (ፊል. ፩፥፲፰)

ቀሚሱ የተባለችን ቤተ ክርስቲያንን ከተቃደዷት ግን አደጋ አለው ፤ ‹የሐዋርያት በሆነች በአንዲት ቤተ ክርስቲያን እናምናለን› ብለን የምንናገርላት ቤተ ክርስቲያን የክርስቶስ ቀሚሱ ናት፡፡ በሰው እጅ ያልተሰፋች ፣ ማንምም ሊሠፋት የማይችል ቀሚስ ናት ፤ ከላይ ጀምሮ ወጥ ሆና በመሠራቷም አትከፋፈልም፡፡ ቤተ ክርስቲያንን ሊከፋፍሏት የሚፈልጉ ሰዎችን ሊቁ አውግስጢኖስ እንዲህ ሲል ይጠይቃቸዋል ፡- ‹‹ሮማውያን እንኳን ያልቀደዱትን የክርስቶስን ልብስ እናንተ ስለምን ትቀድዱታላችሁ?››

ዲያቆን ሄኖክ ኃይሌ
deaconhenokhaile@gmail.com

የዩቲዩብ ቻናላችንን ይቀላቀሉ






175 views07:01
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-29 10:01:15 +++ የኢየሱስን ልብስ ከላዩ ላይ ገፈፉት ±++

በወንጌል የምናውቃቸው ጌታችን የለበሳቸው ልብሶች አራት ሲሆኑ ሦስቱ ከዕለተ ዓርብ በኋላ የለበሳቸው ናቸው፡፡ የመጀመሪያው ከመያዙ በፊት ለብሶት የነበረው የራሱ ልብስ ነው ፣ ሁለተኛው ሄሮድስ ለመዘበት ያለበሰው የጌጥ ልብስ ነው ፤ ሦስተኛው ወታደሮቹ ያለበሱት ቀይ ልብስ (ከለሜዳ) ነው ፤ አራተኛው ከትንሣኤው በኋላ ሲገለጥ ለብሶ የታየውና ከየት እንደመጣ የሚያጠያይቀው ነጭ ልብስ ነው፡፡ ጌታችንን መስቀል አሸክመው ከጎልጎታ ኮረብታ ካደረሱት በኋላ ለብሷት የኖራትን ልብሱን ገፈፉት፡፡

‹‹ልብሶቹን ወስደው ለእያንዳንዱ ጭፍራ አንድ ክፍል በአራት አከፋፈሉት ፤ እጀ ጠባቡም ከላይ ጀምሮ ወጥ ሆኖ የተሠራ ነበር እንጂ የተሠፋ አልነበረም፡፡ ስለዚህ እርስ በእርሳቸው ፡- ለማን እንዲሆን በእርሱ ዕጣ እንጣጣልበት እንጂ አንቅደደው ተባባሉ፡፡ ይህም ፡- ልብሴን እርስ በእርሳቸው ተከፋፈሉ ፤ በቀሚሴም ላይ ዕጣ ተጣጣሉ የሚለው የመጽሐፍ ቃል ይፈጸም ዘንድ ነው›› (ዮሐ. ፲፱፥፳፫‐፳፬ መዝ.፳፩፥፲፰)

የጌታችንን ልብስ የገፈፉት ዕርቃኑን ለመስቀል ሲሆን ልብሱን የተከፋፈሉት ደግሞ ሌላ የሚወደው ሰው መጥቶ ልብሱን እንዳይወስደው ነበር፡፡ አብረውት የተሰቀሉትን ወንበዴዎች ልብሶች እንዲህ እንዳደረጉ አልተጻፈም ፤ ይህም ትንቢት የተነገረለት እርሱ ስለሆነና የሚረዳው የሌለ ያማረ ልብስ የማይለብስ ደሃ ነው ብለው በእርሱ ለመሳለቅ እንዲመቻቸው ነበር፡፡

የጌታችን ልብስ ግን እነርሱ እንዳዩት ተራ ልብስ አልነበረም፡፡ ወታደሮቹ አላወቁም እንጂ ከላዩ ገፍፈው በእጃቸው የያዙት ልብስ በታቦር ተራራ እንደ ብርሃን ነጭ የሆነውን ልብሱን ነበር፡፡ (ማቴ. ፲፯፥፪) ይህ ልብስ ከዓሥራ ሁለት ዓመት ጀምሮ ደም ይፈስሳት የነበረችውና ገንዘብዋን ከስራ ልትድን ያልቻለችው ሴት ‹‹የዳሰስሁት እንደሆነ እድናለሁ›› ያለችው ልብስ ነው፡፡ ይህ ልብስ የዚህችን ሴት የደምዋን ምንጭ ያደረቀላት ልብስ ነው፡፡ ጌታችን ሴቲቱን ከፈወሳት በኋላ ‹‹አንድ ሰው ዳስሶኛል ኃይል ከእኔ እንደ ወጣ አውቃለሁ›› ብሎ የተናገረበት ስለዚህ ልብስ ነበር፡፡ (ሉቃ. ፰፥፵፫‐፵፮) ስለዚህ ልብስ ‹‹በገባበት ስፍራ ሁሉ መንደርም ከተማም ገጠርም ቢሆን በገበያ ድውዮችን ያኖሩ ነበር ፤ የልብሱንም ጫፍ እንኳን ሊዳስሱ ይለምኑት ነበር ፤ የዳሰሱትም ሁሉ ዳኑ›› ተብሎ ተጽፎአል፡፡ (ማር. ፮፥፶፮)

ይህንን ተአምረኛ ልብስ የሮም ወታደሮች ተከፋፍለው በእጃቸው ቢይዙትም ደም ይፈስሳት እንደነበረችው ሴት በእምነት ሆነው አልዳሰሱትምና አንዳች ተአምር አላዩም ፤ ‹‹ምንም ተአምር ከልብሱ አላገኙም ፤ ክርስቶስ የማይነገረውን ኃይሉን ገድቦ ነበርና›› ይላል አፈወርቅ፡፡

ሮማውያን ወታደሮች ጌታችን ልብሱን ገፍፈው በአደባባይ ዕርቃኑን አቆሙት ፤ ምድርን በአበባ የሚያስጌጣትን አምላክ ፤ ሰሎሞን እንኳን በክብሩ ለብሶት የማያውቀውን ልብስ ለሜዳ አበቦች የሚያለብሳቸውን አምላክ ልብሱን ገፍፈው ዕርቃኑን አቆሙት፡፡ ‹‹እንደ ሸላቾች ልብሱን ከላዩ ላይ ሁለት ጊዜ ገፈፉት ፤ እርሱም በሸላቾቹ ፊት ዝም እንደሚል በግ ዝም አለ፡፡ ዕርቃናቸውን ከገነት የወጡትን አዳምና ሔዋንን ለማልበስ ልብሱን ተገፈፈ፡፡ እርሱ በመዋረድ ውስጥ ሆኖ በልብሶቹ ዕርቃናቸውን አለበሰ፡፡ የእርሱ ልብሶች ለተዋረዱት አዳምና ሔዋን እንደሚበቁ ያውቅ ነበርና›› ይላል ቅዱስ ያዕቆብ ዘሥሩግ፡፡

በዚህ ሊቅ ምክንያት እስቲ ለአፍታ አዳምና ሔዋን ከገነት ወደ ወጡባት ቅጽበት እንመለስ፡፡ አዳምና ሔዋን ዕርቃናቸውን ለመሸፈን ቅጠል ባገለደሙ ጊዜ ከገነት ሲወጡ ‹‹እግዚአብሔርም ለአዳምና ሔዋን የቁርበት ልብስን አደረገላቸው አለበሳቸውም›› ይላል፡፡ (ዘፍ. ፫፥፳፩)

እግዚአብሔር ከሌላ ዓይነት ልብስ ይልቅ ስለምን የቆዳ ልብስን ሊያደርግላቸው ወደደ? ብለን ስንጠይቅ ወደ ዕለተ ዓርብ ይመራናል፡፡ እንደሚታወቀው ቁርበት የሚገኘው ከእንስሳ ነው፡፡ አንድ ቁርበት ልብስ እንዲሆን በመጀመሪያ እንስሳው ይታረዳል ፣ ደሙ ይፈስሳል ፤ ቆዳው ይገፈፋል ፣ እንዲደርቅ በእንጨት ላይ ተወጥሮ ይሰጣል ፣ በላዩ ላይ ያለው ነገር እስከሚነጻ ድረስ ይለፋል፡፡ ከዚህ ሁሉ ሒደት በኋላ ልብስ ሊሆን ይችላል፡፡

ይህንን ልብስ በገነት ያለበሳቸው አምላክም የእንስሳ ደሙ እንደሚፈስስ ደሙን አፍስሶ ፣ቆዳው እንደሚገፈፍ ቆዳው አልቆ አጥንቱ እስከሚታይ ተገርፎ ፣ ቆዳ እንደሚወጠር በመስቀል ላይ እንደ ቆዳ ተወጥሮ በዕርቃኑ ዕርቃናችንን ሸፈነልን ፤ እርሱም ለእኛ ልብሳችን ሆነልን፡፡ ‹‹የተጠመቃችሁ ሁሉ ክርስቶስን ለብሳችኋል›› እንዳለ ሐዋርያው (ገላ. ፫፥፳፯)

ወታደሮቹ የጌታችንን ልብስ ለአራት ክፍል ተከፋፈሉ፡፡ ቀሚሱ ግን ከላይ ጀምሮ ወጥ ሆኖ የተሠራ ነበርና አንቅደደው ተባብለው ዕጣ ተጣጣሉበት፡፡ እነዚህ ወታደሮች ለቀሚሱ ሳስተው ባለመቅደዳቸው ሳያውቁት ትልቅ ምስክርነት መሰከሩ፡፡ ጌታችን ብዙ መንገላታት ሲደርስበት ባደረው በጨለማው ፍርድ ቤት በአይሁድ ሸንጎ ውስጥ ሊቀ ካህናቱ ቀያፋ ከሕግ ውጪ ልብሱን ቀድዶ እንደነበር ይታወሳል፡፡ በዚህም ሥራው ሊቀ ካህናት ልብሱ ሊቀደድ እንደማይገባውና ልብሱን መቅደዱም ሊቀ ካህናትነቱ ማለፍዋን የሚያመለክት እንደሆነ በሥፍራው ተመልክተን ነበር፡፡ እነዚህ ወታደሮች የጌታችንን ቀሚስ ባለመቅደዳቸው የሐዲስ ኪዳን ሊቀ ካህናት ክርስቶስ መሆኑንና ልብሱም ፈጽሞ ሊቀደድ እንደማይገባው የሚያሳይ ታላቅ ምሥጢር ተፈጸመ፡፡

ያልተቀደደችውን የመድኃኔ ዓለም ክርስቶስን ቀሚስና ለአራት የተከፋፈለውን ልብሱን ሊቃውንተ ቤተ ክርስቲያን ብዙ አስተምረውበታል፡፡ ‹ከላይ ጀምሮ ወጥ ሆኖ የተሠራ› የሚለው ቃል ክርስቶስ ‹ሰው ብቻ ሳይሆን ከላይ የመጣ መለኮት መሆኑን ያመለክታል› ብሎ ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ አብራርቶታል፡፡ ሶርያዊው ቅዱስ ኤፍሬምም ቀሚስ የተባለ መለኮቱ ሊቀደድ (ከሥጋው ተለይቶ ሊከፈል) አይችልም ፤ ለአራት የተከፈለው ልብሱ ግን አራት ሆና የተጻፈችውና በአራቱም ማዕዘን የምትዳረሰው ወንጌል ምሳሌ ናት ሲል ተርጉሞታል፡፡

ይህ የሊቃውንቱ ትርጓሜ ከእግዚአብሔር መንፈስ የተገኘ መሆኑም በቤተ ክርስቲያን ታሪክም ተረጋግጧል፡፡ ዐሥራ ሰባተኛው የእስክንድርያ ፓትርያርክ ተፍጻሜተ ሰማዕት ቅዱስ ጴጥሮስ አርዮስ የተባለውን በኩረ መናፍቃን ካወገዘው በኋላ የተፈጸመው ነገር ይህን ግልጥ አድርጎ ያሳያል፡፡ አርዮስ ከውግዘቱ በኋላ በፓትርያርኩ ላይና በቤተ ክርስቲያኒቷ ላይ ከንጉሥ መክስምያኖስ ጋር ሴራን ተብትቦ ቅዱስ ጴጥሮስን አሳስሮት ነበር፡፡ ከዚያም አርዮስ ፓትርያርኩ ጴጥሮስ ሊገደል እንደሚችል ሲረዳ እንዳወገዘው እንዳይሞት የዋሃን ካህናትን አማላጅ አድርጎ ምሕረት ሊያስለምነው ሞከረ፡፡ ፓትርያርኩም ለአርዮስ አማላጆች ሆነው ለመጡት ካህናት አርዮስን ከውግዘቱ መፍታት እንዳይችል ያደረገውን ራእይ እንዲህ ሲል ነገራቸው፡-
152 views07:01
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-28 20:27:50 " ትሑት ነፍስ ምስጉን ናት። ጌታ ይወዳታልና። እመ አምላክ ከኹሉም የምትበልጥ ትሕት ናት፤ ስለዚህም በምድር ላይ የሰው ልጆች በሙሉ ያመሰግኗታል፥ ሰማያውያን ኃይላትም ያገለግሏታል።  ጌታ የተመሰገነች እናቱን ለእኛ ጠባቂና ረዳት አድርጎ ሰጠን።" (St. Silouan the Athonite, Writings III.14) በእርግጥ እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም የትሕትና ትምህርት ቤት ናት። ለእርሷ ያለን ፍቅር የሚገለጠውም እርሷ የምትወደውን ትሕትና ገንዘብ ስናደርገው ነው። ትሕትናን ገንዘብ ለማድረግ በየዕለቱ እስካልተጋን ድረስ ደርሶ የሚገኝ ጸጋ አይደለም።  በእመቤታችን ዕለት ከእርሷ ጋር መኾናችን አንዱ የሚረጋገጠው ትሕትና ያለን እንደ ኾነ ነው።  በትዕቢት እየተቃጠልን ሺህ ጊዜ ለእመቤታችን ፍቅር አለን፤ ማርያም ማርያም ብንል ምን ጥቅም አለው? ዋናው ጉዳይ ለራሳችን በፈቃዳችን ጥመት ያለበስነውን ትዕቢት ክፉ መኾኑን አምነን በማውገዝ ወደ ትሕትና ወደ ለመድረስ እንትጋ እንጂ!



209 viewsedited  17:27
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-28 18:31:42

207 views15:31
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-28 11:11:56

44 views08:11
ክፈት / አስተያየት ይስጡ