Get Mystery Box with random crypto!

የተከበራችሁ ውድ የፀደይ ባንክ አመራሮች፤ እንደ ወርቅ በእሳት ተፈትናችሁ አብረቅራቂ ወርቅ የሆና | ፀደይ ባንክ Tsedey Bank S.C.

የተከበራችሁ ውድ የፀደይ ባንክ አመራሮች፤

እንደ ወርቅ በእሳት ተፈትናችሁ አብረቅራቂ ወርቅ የሆናችሁ፤ከገጠር ብድር፣አብቁተ ከእዚያም ፀደይ ባንክ ያደረሳችሁ በእውነቱ ልትመሰገኑ ይገባል። ይህ ሁሉ አልጋ በአልጋ እንዳልመጣ ሁላችንም የምናውቀው ሃቅ ነው። እንዳሁኑ መቀመጫ ወንበር እንኳን በሌለበት በድንጋይ ላይ ተቀምጣችሁ ለዚህ ማድረሳችሁ ምነኛ ታታሪና ታማኞች እንደሆናችሁ ሁነኛ ማሳያ ነው። ይህ ሁሉ በእናንተ ፅናትና ታማኝነት የመጣ ለውጥ መሆኑን ሁላችንም እንረዳለን፤አሁን ላይ በአመራር ደረጃ ሁናችሁ የአመራር ብስለትና ብቃትም በእጅጉ የምትደነቁ ናችሁና ልትኮሩ ይገባል።
ይሁን እንጂ አሁን ላይ የቀድሞው አብቁተ ለአሁኑ ፀደይ ባንክ ሽግግሩን አስረክቦ በክብር ተሸኝቷል። ስለዚህ ፀደይ ባንክ በሁሉም ፋሲሊቲዎች ከአብቁተ ተሽሎና ከፍ ብሎ ካሉት የባንክ የፋይናንስ ተቋማት ጋር ለመወዳደር በቴክኖሎጅ(ኮር ባንኪንግ) የተሻለ ሁኖ መገኘትና የተሻለ ተወዳዳሪ ለመሆን ያስችላልና በእጅጉ ሊታሰብበትና ወደ ስራ ሊገባ ያስፈልጋል የሚል ሃሳብ አለኝ። እንዲሁም ከመቼውም ጊዜ በበለጠ በአሁኑ ሰዓት የኑሮ ውድነቱ ጣራ የነካና ለመኖር ፈታኝ ከመሆኑ የተነሳ ፀደይ ባንክ ችግራችንን ይፈታዋል ከሚል እሳቤ የተቋሙ ስራ ወዳዱንና ታታሪው ሰራተኛ በጉጉት ስንጠብቀው የቆየነው ሃቅ ነው። ስለሆነም አሁን የተደረገው የደመወዝ እና የጥቅማጥቅም ጭማሪ ይበል የሚያስብል ቢሆንም ካለው የኑሮ ሁኔታና ከጠበቅነው ጋር ግን በእጅጉ ያነሰ ነው። ስለሆነም ይሄን እና መሰል ጉዳዮችን ተቀራርበን ለመፍታት ይቻል ዘንድ ሁሉንም ያማከሉ የተለያዩ የውይይት መድረኮች ቢመቻቹልን የበለጠ ክፍተቶችን ለመሙላት የተሻለና ተገቢነት ያለው ይመስለኛል።ስለሆነም ሁሉንም በብስለት እንደገና ታዩልን ዘንድ በአክብሮት ለማሳሰብ እወዳለሁ።

የተከበራችሁ ውድ የፀደይ ባንክ ሰራተኞች፤

እናንተ የምንጊዜም ታታሪዎችና ታማኞች ናችሁና በዚሁ ወደር የለሽ ስራችሁ ልትኮሩ እና ልትቀጥሉበት ይገባል። እናንተ በሁሉም የተለያችሁ ውዶች ናችሁና ከምንም በላይ አሁን ለፀደይ አስፈላጊ ናችሁ፤ፀደይ ባንክ አሁን በበሳል አመራሮቻችንና በእኛ በትጉ ሰራተኞች ስራና የአመራር ጥበብ ዓለም አቀፍ ባንክ እንደምናደርገው ማንም ጤነኛ የሆነ ሰው ሁሉ ራዕዩ ሊያደርገው የሚገባ ጉዳይ ነው። ስለሆነም ሰሞኑን የተለያዩ ሃሳቦች ይነሳሉ፣ቅሬታዎችም እንዳሉ እሙን ነው። ይህን ደግሞ የሚገባንን ደመወዝና ጥቅማጥቅም እንደየ ስራ መደባችን የተሰጠን ቢሆንም ወቅቱን ያላገናዘበ ነው የሚል በሰፊው እየተነሳ ያለ አጀንዳ ነው።ይሁን እንጂ ቅሬታው አግባብነት የሚኖረው እኛ በምንታወቀው በታታሪነትና ስራ ወዳድነታችን ሁኖ ተገቢውን ሁሉ የማግኘት መብታችን እንዲከበርልን ሰራተኛው በአቋቋመው የሰራተኛ ማህበሩ አመራሮች ቢቀርብ የበለጠ ተደማጭ ይሆናል።ስለዚህ ይሄን ደግሞ ማህበሩ ዘንግቶታል ለማለት ግን አይቻልም።ሰራተኛው የሚያቀርበውን ቅሬታ የሰራተኛ ማህበሩ ተረድቶና ተገንዝቦ ለበላይ አመራሮች ያቀርበዋል፤ውጤቱንም ይከታተላል ማለት ነው። ስለዚህ ሁሉም ሰራተኛ ከትላንቱ ዛሬን ከዛሬ ነገን የተሻለ በማየት ከመቼውም ጊዜ በላይ ጠንክሮ እንዲሰራ በምንወደው ተቋም ስም አደራ ለማለት እወዳለሁ።
መቼም ቢሆን የማይደረስ መንገድ እንዴለለ ሁሉ የማይፈታ ችግርም ሊኖር አይችልም!

ከፀደይ ባንክ ጋር ወደፊት!
ፀደይ ባንክ፤የሁሉም ባንክ!!ፀደይ ባንክ (ACSI አብቁተ) (Channel)
https://t.me/tsedey_bank_office
ፀደይ ባንክ (ACSI አብቁተ) (Group)
https://t.me/+dUlUVoLKoohlYjQ0
ፀደይ ባንክ (ACSI አብቁተ) (Bot)
@backtube_bot
ፀደይ ባንክ (ACSI አብቁተ) (Page)
https://www.facebook.com/ACSI-%E1%8A%A0%E1%89%A5%E1%89%81%E1%89%B0-299921343703425/
ፀደይ ባንክ (ACSI አብቁተ) (FB Group)
https://facebook.com/groups/2563603037297331/ ፀደይ ባንክ (ACSI አብቁተ) (You Tube) https://youtube.com/channel/UCMQR6irb_HcaF5K8FYqw9YQፀደይ ባንክ (ACSI አብቁተ) (TIK TOK) http://tiktok.com/@tsedeybank