Get Mystery Box with random crypto!

📖አስተማሪ ታሪኮች እና የአበው 🖊ምክሮች

የቴሌግራም ቻናል አርማ trufatnatanim — 📖አስተማሪ ታሪኮች እና የአበው 🖊ምክሮች አ
የቴሌግራም ቻናል አርማ trufatnatanim — 📖አስተማሪ ታሪኮች እና የአበው 🖊ምክሮች
የሰርጥ አድራሻ: @trufatnatanim
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 1.11K
የሰርጥ መግለጫ

እዚህ ቻናል ላይ አስተማሪ የኦርቶዶክስ ታሪኮች እና ምክሮች ያገኛሉ

Ratings & Reviews

4.00

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

1

4 stars

1

3 stars

1

2 stars

0

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች

2022-01-31 20:59:01
"የህይወት እናት ድንግል ማርያም ሆይ ትንሳኤሽ ሳይሆን ሞትሽ ይደንቀኛል፤ እርገትሽ ሳይሆን ወደ መቃብር መውረድሽ ይገርመኛል።

የብርሃን እናት ድንግል ማርያም ሆይ ትወጂኛለሽን? ብየ አልጠይቅሽም ፍቅርን የወለድሽ አንቺ ለአለሙ ሁሉ ፍቅርሽ የበዛ ነውና፤ አትናፍቂኝምን? ብየም አልጠይቅሽም ዘወትር እኔን ለመጠበቅ ከጎኔ እንደማትለይ አውቃለሁኝና፤ ሆኖም እመቤቴ ሆይ፦ እንደ ቶማስ አይሽ ዘንድ በእጅጉ እጓጓለሁ የቶማስ ንፅህናና ቅድስና ግን የለኝም እንደ ዮሃንስ ከጎንሽ ልሆን እጓጓለሁ የዮሃንስ ፀጋ ግን የለኝም።

እናቴ ሆይ፦ እንደ ኤልሳዕ የልቦናዬ አይን በርቶ ሰማያዊ ክብርሽን ላይ አልተቻለኝምና አዝናለሁ ኤልሳዕ በፀሎት ሃይል የግያዝን አይን እንዳበራ አንቺም አይኔን ታበሪልኝ ዘንድ ሃይልሽን በእኔ ላይ አበርቺ፡፡

ድንግል ሆይ፦ ይህን የምል የእምነት ማረጋገጫ ፈልጌ አይደለም በልጅሽ መሰረትነት የታነፅኩኝ በልጅሽ ስምም የተጠመቅኩኝ ነኝና፤ ነገር ግን ስለምትናፍቂኝ ይህን አልኩኝ ስለዚህም ነይ ነይ እምየ ማርያም እያልኩኝ እንደ እናቶቼም እለምንሻለሁ፡፡ የብርሃን ልብስሽን ለብሰሽ ነይ የክብር አክሊልሽን ደፍተሽ ነይ አንቺ ሱላማጢስ ሆይ ነይ እናይሽ ዘንድ ነይ፡፡"
1.2K viewsBantegize 19, 17:59
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-01-25 21:40:15
1.1K viewsBantegize 19, 18:40
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-01-22 22:11:53 በሞት የሚበዛው አስከሬን ብቻ ነው!
=============
ዘመኑ ለእኛ ለኦርቶዶክሳውያን ምን ያህል ጨለማ እንደሆነ ብዙ ማለት አይጠበቀብኝም። መገፋትንና መሰደድን፣ መገረፍና መገደልን በዓይናችን አይተናል። በአራት ዓመታት ውስጥ ብዙ ወገኖቻችን ያለ ዕድሜያቸው ተቀጥፈዋል፤ በርካታ ይዞታዎቻችን ተነጥቀዋል። መከራው ከቀን ቀን እየከፋ መጭውን ጊዜ ጨለማ አድርጎታል። በስንፍናችንና በመርሕ አልባነታችን ተንቀናል፤ ተዋርደናል።
ባለ መርሕ ሆነን በሰይፍ የመጣውን በሰይፍ በመመለስ ፋንታ "ስንሞት እንበዛለን" በሚል የሞኝ ሐሳብ ተበልተናል። ለገዳዮቹ ተኝቶ አንገቱን የሰጠ፣ ያለ ተጋድሎ ሕይወቱን ያጣ አብነት የለንም። የአባቶችና የእናቶች ታሪክ የሚነግረን ይህንን ነው። ከቅዱስ ጊዮርጊስ እስከ ቅዱስ መርቆሬዎስ፣ ከቅዱስ ገላውዴዎስ እስከ ቅዱስ መርምሕናም ያየነው ሞትን ፊት ለፊት ተጋፍጦ አረምን ነቅሎ ጊዜው ሲደርስ የሰማዕትነትን ፅዋ መቀበል እንጂ በየሄዱበት መሞትን አይደለም።
በታሪክ ያነበብነው፣ እንደዋዛ የሰማነው የመከራ ዘመን በእኛ ዘመን ተከሥቷል። እንደዜጋ ቆጥሮ መጠበቁ ቀርቶ፣ መንግሥት ራሱ ገዳይ ሆኖ ደማችንን ሲያፈሰው አይተናል። በቅርብ ጊዜ ሁለት ወንድሞቻችንን በፀጥታ ኃይል አጣን ዝም አልን። አሁን ደግሞ ታቦት አጅበው ወጥተው ሦስት ወንድሞቻችን እንደወጡ ቀርተዋል። ከእነዚህ አንዱ የሥጋ ወንድማችን እንዲሆን አንጠብቅ፤ ከሥጋ በላይ ያስተሣሠረን ጠንካራ ማተብ አለንና።
ወደድንም ጠላንም መንግሥት ዘምቶብናል፤ በሞታችን ተሣልቆብናል። ይገድሉንና የፌዝ መግለጫ ያወጣሉ። በእርሱ ያዘናጉንና ዝም ስንል ደግመው ይገድሉናል። በዚህ መንግሥት ውስጥ የተሰገሰጉ አፅራረ ቤተ ክርስቲያን ካላጠፉን የሚያርፉ አይመስሉም። ከመንግሥት አካላት እስከ ሚዲያዎቻቸው ዘምተውብናል። የሚበጀን አንድ ሆኖ ራስን መከላከል ነው። ራስን መከላከል ሃይማኖታዊ ግዴታና ዲሞክራሲያዊ መብት ነው። ማንም ራሳችንን ስለተከላከልን የመጠየቅ መብት የለውም። ቢጠይቀን እንኳን ተኝቶ ከመሞት አይበልጥም። "ስንሞት እንበዛለን" ከሚል የሰነፍ ጥቅስ እናውጣ። ሞት ሲደጋገም የሚበዛው አስከሬን እንጂ ሕይወት አይደለም።
ራስን ለመከላከል የማንንም መምጣት አንጠብቅም። በጉጉት የሚጠበቀው የክርስቶስ መምጣት እንጂ የሰው መምጣት አይደለም። በሰላም ጊዜ ቁርጠኛ የሆነው ሁሉ በመከራ ጊዜ ያደፍጣል። ማንንም ሳንጠብቅ በየአካባቢያችን ከተደራጀን ሁሉ ሰላም ይሆናል። በፍቅር ካልተከበርን በጉልበታችን ተፈርተን ልንከበር ይገባል። ይህንን እስካላደረግን ድረስ የመዳኛ በር የለንም። ብቸኛው መዳኛችን ተደራጅቶ ራስን መከላከል ብቻ ነው።
...ታደለ ሲሳይ..
...በቴሌግራም ያግኙኝ...
https፡//t.me/orthotobia
1.1K viewsBantegize 19, 19:11
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-01-17 21:25:21
እንኳን ለከተራ በዓል በሰላም አደረሳችሁ!

፨ ከተራ_ምንድን_ነው?
ÂŻÂŻÂŻÂŻÂŻÂŻÂŻÂŻÂŻÂŻÂŻÂŻÂŻÂŻÂŻÂŻÂŻÂŻÂŻ
ከተራ ' #ከበበ ' ካለው የግእዝ ግሥ የወጣ ነው፡፡ ፍችው ውኃ መከተር ፣ መገደብ ማለት ነው፡፡

፨በጥምቀት ዋዜማ ታቦተ ሕጉ ወረደ ወልድ እምሰማያት ውስተ ምቅማቃት እየተባለ ከቤተ መቅደስ ወጥቶ ውኃ ባለበት አካባቢ ስለሚያድር የየአጥቢያው ሕዝብ እየተሰበሰቡ በወንዝ ዳር ወይም በምንጭ አካባቢ ድንኳን ይተከላሉ፡፡ ድንኳንም ከሌለ ዳስ ሲጥሉ ይውላሉ፡፡ የምንጮች ውኃ እንዲጠራቀም ይከተራሉ ( ይገድባሉ ) ጉድጓድ እየተቆፈረ ውኃው እንዳይሄድ በመገደብ ለመጠመቂያ ( ለጥር 11 ) ዝግጁ የሚያደርጉበት ዕለት ነው፡፡

፨ በተጨማሪ በአቅራቢያ የሚገኙት ቤተክርስቲያናት ተሰብስበው ከዚሁ ከተቆፈረው ገንዳ ወይም ከተገደበው ጅረት አጠገብ ባለው ዳስ ወይም ድንኳን ታቦቶቻቸውን ያሳድራሉ ሊቃውንቱም በዚያው እግዚአብሔርን በማህሌት ሲያመሰግኑ ያድራሉ።

በበዓለ ጥምቀት የታቦታቱ ወደ ወንዝ መውረድ መድኃኔ ዓለም ክርስቶስ በእደ ዮሐንስ ለመጠመቅ ከገሊላ ወደ ዮርዳኖስ በዋዜማው የመሄዱ ምሳሌ ነው፡፡ ታቦቱ የጌታችን፣ ምሳሌ ሲሆኑ ካህናቱ የመጥምቁ ዮሐንስ ምሳሌ ናቸው፡፡ መዘምራኑና ሕዝቡ ደግሞ ዮሐንስ ያጠመቃቸው ሕዝቦች ምሳሌዎች ናቸው፡፡

...በመሆኑም የልደትና የጥምቀት ዋዜማ ምን ጊዜም ይጾማል።
በመሆኑም ዕረቡ የምናከብረው ጥምቀት ዋዜማው ነገ ማክሰኞ ነው ስለዚህ ነገ ማክሰኞ ጾም ነው ማለት ነው።

የገሀድ ጾም ሊቃውንት እንደሚያስተምሩት የሚጾመው የሰዓቱ ብዛት 18 ሰዓት ነው።
ነገር ግን እስከምንችለው ሰዓት መጾም እንችላለን፤የሚቆርብ ግን ግዴታ 18 ሰዓት መጾም አለበት።

መልካም_የከተራ_በዓል

ዲ/ን Y.b (ዘፍኖተ ቅዱሳን)
1.1K viewsBantegize 19, 18:25
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-01-11 22:50:20 "… መልእክቱ የሚሠራው አይተው ለሚያሾፉት፣ ለሚቀልዱት፣ አይደለም። ለሚጠቀሙበት ነው። ይህን መልእክት በወረቀት አባዝታችሁ ላልሰማ አሰሙ። ላላየም አሳዩ። በቤተሰብ ደረጃ ተሰብስባችሁ አንብቡት። ተወያዩ፣ የማታ ጸሎት በቤተሰብ ደረጃ አሁኑኑ ጀምሩ። ጭፈራ፣ ሲጋራ፣ ዝሙት፣ ስካርና ጫት፣ ሀሺሽም፣ አባካኝነትንም አስወግዱ። ተረዳዱ፣ ተመካከሩ። አንዱ ስለአንዱ ግድ ይበለው። ወጣቶች በእናት በአባታችሁ ተመረቁ። አካላዊ እንቅስቃሴ አድርጉ፣ ስገዱ፣ ጹሙ፣ ጸልዩ። እንደ ርግብ የዋሕ፣ ልባም፣ እንደ እባብም ብልህ ሁኑ። ተከባበሩ፣ ተረዳዱ፣ ተፋቀሩ። ንስሐ ግቡ፣ በትዳራችሁ ጽኑ፣ አግቡ፣ ውለዱ፣ ዘራችሁን አብዙ። ሰንበትን አስቀድሱ፣ ፀበልም ተጠመቁ። ቁረቡ።

"…በቃላችሁ፣ በንግግራችሁ፣ በወጋችሁ ውስጥ ሁሉ የፍርሃት ቃልን አትጠቀሙ። ክርስቲያን አሸናፊ ነው። ዐማራ ሃገር አቅኚ ነው። ኦርቶዶክስ የኢትዮጵያ እንጀራዋ፣ ጌጥ መገለጫዋ ነው። እናም አትፍሩ። በወሎ እንዳሉት፣ በጎንደርም፣ በሸዋና በጎጃም ካሉት ሙስሊም ወንድሞቻችሁ ጋርም ኅብረት አንድነቱን ፍጠሩ። የትግሬ እልሁ ስላልበረደለት፣ ስላደነዘዙትም ብዙም በሱ ላይ አትድከሙ። ተደራጁ፣ ተሰባሰቡ፣ ማንም ተበተን ሲላችሁ አትበተኑ። ቀበሌ፣ ወረዳ፣ ምክር ቤቶቹን ሁሉ ወንበሩን ሙሉ። ለመገዛት ብቻ፣ ለመሰደብ፣ ለመረገጥ ብቻ አትኑሩ። ለምን? በሉ። ጠይቁ የደቡብ ኦርቶዶክሶች ህመም የኦሮሞ ኦርቶዶክሶችም ህመም ይሁን፣ በየትም ስፍራ ኦርቶዶክስ ስትጠቃ በአንድነት ተነሡ። በወታደር ብዛት የሚያሸንፍ አገዛዝ የለም። ምንጊዜም አሸናዊ ህዝብ ነው። ከድንዛዜ የነቃ ህዝብ ያሸንፋል። አሁን ያልነቃው የሻአቢያ፣ የኦነግና የህወሓት ዱላ ሲበዛበት ይባንናል። እናንተ ግን በጸሎት ጭምር በርቱም ተብላችኋል። ጎንደሮችም መከራው ቢቀንስ ያን የተለመደ ምህላችሁን ጀምሩት ተብላችኋል።

"… በመጨረሻም "የመኾኒ ትንቢትም" ወደ መቋጫው ተቃርቧል። ፍጻሜውንም ያገኛል። በመሆኒ ምን ይሆናልኩት ብዬ ለጠየቅኩት ጥያቄ በመሆኒና በርብ ወንዝ ስለሚከወነው ጊዜው ሲደርስ እንነግርሃለን ብለዋል።

"… ኡፍፍፎይ…  ጨረስኩ… ተፈጸመ።
946 viewsBantegize 19, 19:50
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-01-11 22:50:20 "…ቀጥሎ ከበድ ያለ ስደትና ከፍተኛ መከራም በዘንድሮው የዐብይ ጾምም ጠብቁ ተብሏል። በመለስ ዜናዊ ተገፍቶ የነበረው አርከበ እቁባይ የሚመራው የብልፅግና መንግሥት ሻአቢያ አሠልጥኖ ወደ ኢትዮጵያ በላከውና አሁን የኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት በሆነው ኦነግ አማካኝነት የስብሀት ነጋ ሥርወ መንግሥቱ ደብረ ጽዮን የሚመራው አዲሱ የትግራይ ትውልድ ለዳግም ጥፋት በዐማራ ላይ ተፈትቶ ይለቀቃል። በመከራው ጽናት የተነሣ ጾሙ እንኳ እስከመስተጓገል ሊደርስ ይችላልም ነው የሚሉት በረኸኞቹ። መፍትሄው አለመደንገጥ፣ በቶሎ መባነን፣ አለመረበሽ፣ በጽናት፣ በጸሎት፣ በንስሀ ራስን ለካህን በማስመርመር እንደ ሳምሶን ኃይልን ከአርያም ለማግኘት መትጋትና መዘጋጀት ብቻ ነውም የሚሉት። እግዚአብሔርን በንፁሕ ልብ የሚማጸን ይሻገረዋል። አባ ገዳዎቹም በገዳ ሥርዓት መሠረት ኦሮሞ ሆኖ እስላም ያልሆነ ሁሉ እንዲወገድ ከመግባባት ደርሰዋል። ለዚህ ነው እየሆነ ባለው ነገር ኦሮሞ ክርስቲያኖች እየታረዱ እንኳን ትንፍሽ የማይሉት።

"…መላው ሃገሪቱን የሚያካልልም ፅኑ ረሃብ ከወርሀ ሚያዝያ አካባቢ ጀምሮ በሰፊው ይጠበቃል። እሱን ተከትሎም የታዘዘው መቅሰፍት አጣዳፊው ወረርሽኝም ይከተላል። ወረርሽኙ መታወቂያ አይቶ አያዳላም። ሃይማኖት መርጦ አይምርም። ጉልበት፣ ጠመንጃ የያዘንም አይፈራም። ገንዘብ ስላለህም አይታለልም። በፎቅ፣ በምድር ውስጥ፣ በቤተመንግሥት፣ በዋሻና በጫካ የትም ብትገባ አይምርህም። መቅሰፍት ነው። ከእግዚአብሔር የታዘዘ መቅሰፍት። መድኃኒቱም ጾም፣ ጸሎት፣ ንስሀ እና ሥጋወደሙ ናቸው።

"…የዐውሬው አማኝ ከሆኑት መሪዎቹ ራሱን ያላራቀ፣ በወንድሙ ጥላቻ እንዲቀውስ የተሰበከው ትግሬ፣ በአውሬ ፖለቲከኞች እጅ የወደቀውንና ከዐማራ ህዝብ ጋር ተገናኝቶ እንዳይገለበጥባቸው በሰጉ በእነዚያው በድሮዎቹ ዐውሬዎች የሚታዘዘው ውስጡንም ያላጸዳው የትግሬ ነገድ በተለይም ኦርቶዶክሱ አማኙ ክፍል በጦርነት፣ በረሃብና በበሽታ እንደ ቅጠል ይረግፋል። አሁንም በቀን በሺህ የሚቆጠሩ ትግሬዎች በየቀኑ እየረገፉ ነው። ዋናው የሚፈለገውም ኦርቶዶክሱን የትግሬና የዐማራን ነገድ ከኢትዮጵያ ምድር ማጽዳት ነው። እሱ በሰፊው ይቀጥላል።

"…ዐማራም ዙሪያውን በአህዛብ ይከበባል። በአህዛብ ሰይፍ፣ በመናፍቃንም ሴራና እሳትም ይጠበሳል። ምዝገባው አልቋል። ወያኔ ቀደም ብላ በአለቆቿ በታዘዘችው መሠረት የቤት ሥራዋን ጨርሳ ለሚመጣው እና ለመጣው አህዛባዊ አካል አመቻችታ አሳልፋ ሰነዱ ደጉሳ ሰጥታ አልፋለች። ማን ምን እንደሆነ፣ ዘሩ፣ ነገዱን፣ ሃይማኖቱ ጭምር ከየመዝገብ ቤቱ ተለቅሞ የእያንዳንዱ ሰው መረጃ በጠላት መዝገብ ውስጥ ሰፍሮ በዝርዝር ተይዟል። የሚጠበቀው የነጋሪቱ መመታት፣ የመለከቱና የፊሽካው መነፋትና ጀምሩ የሚለው ትእዛዝ ብቻ ነው።

ክፍል ፫ ይቀጥላል…
812 viewsBantegize 19, 19:50
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-01-11 22:50:20 “የበረኸኞቹ መልእክት”

"…አክሊለ ገብርኤል፤ አይ እንግዲህ አትልመጥመጥ፣ አትታሽ፣ ንገር የተባልከውን ንገር። ሰሞኑን አየሆነ ያለውን ሁሉ ቀድመህ ንገር ያልንህ መልእክት ላይ የተቀመጠ አልነበረምን? የዕርቁ ወሬ፣ የአውሬዎቹ የመፈታትም ሴራ አስቀድመን የነገርንህ አይደለምን? ስለምን ታዘገየዋለህ? የዐቢይ ኢሳይያስ፣ የስብሐትን ሴራ ቶሎ መግለጥ ነው። …አሁንም ይሄን መልእክት በቶሎ ልቀቀው። አስታውስ "የኢትዮጵያን ትንሣኤ ታበሥር ዘንድ ተመርጠህስ እንደሆን ማን ያውቃል? ዘወትር ራስህን መመርመርህንም አትርሳ…!

"…በእናቱ እቅፍ ሳለ ዋይ! ዋይ! ዋይ! ምርርር ብሎ የሚያለቅስ ህጻን ለምን እንዳለቀሰ የምታውቅ እናቱ ጡቷን አውጥታ ትሰጠዋለች። ህጻኑም ዝም ይላል። የጩኸቱን፣ የልቅሶውን መልስ ስላገኘ ዝም ይላል። እግዚአብሔርም እንዲሁ ነው። ልጆቹ አምርረው በፊቱ የሚያለቅሱ፣ በሰጊድ፣ በጾም፣ በጸሎት፣ በንስሀ በፊቱ የሚንበረከኩ፣ የወልደ አብ ወልደ ማርያምን የጌታችንና የመድኃኒታችንን የኢየሱስ ክርስቶስን ቅዱስ ሥጋውና ክቡር ደሙንም የሚበሉ የሚጠጡትንም ሁሉ ባለቀሱበት ጊዜ ይሰማቸዋል። ጎዶሎአቸውን ሞልቶ፣ ከታዘዘ መቅሰፍትና መከራም ይሰውራቸዋል።

"…አሁን በቅዱሳኑ ላይ አድሮ ሲነገር የቆየውና ሲጠበቅ የነበረው ሁሉ ወደ ፍጻሜው ያመራል። እንኳን የሰው የእንጨት ጠማማ አይኖርም የተባለውም ትንቢት ይፈጸማል። በዐማራ ግዛት ሰው፣ እንስሳትና እጸዋት ተረሽነዋል። ዘንድሮ በመናፍቃኑ አመቻችነት፣ በእኛዎቹ ባንዳነት፣ የአህዛብ ወረራም በኢትዮጵያ በአራቱም አቅጣጫዎች ይፈጸማል። ዝግጅታቸውም ከባድ ነው። በሰማዕትነት እያለፈ ያለውም እጅግ ብዙ ነው። ስፍር ቁጥርም የለውም። ኦርቶዶክሱን የማጥፋት፣ ዐማራውን የማጽዳት፣ ትግሬውንም የማስወገዱ ተግባር ተጠናክሮ ይቀጥላል። አርከበ ዕቁባይ የዐቢይ አለቃ ነው። የስብሐት ነጋና የኢሳያስ አፈወርቂ ቡድን የመለስ ዜናዊን ቡድን መረብ ለመበጣጠስ ሲል ብልጽግናን ፈጥሮ ድርሰት በመድረስ ዐቢይን በተዋናይነት እያጫወቱት ያለው ድራማም በቅርቡ ፍጻሜውን ያገኛል። የመለስ ቡድን ፀድቷል። እግረ መንገዱንም የስብሐት ነጋ ቡድን በዐቢይ ኢሳይያስ መሪነት የመለስን የቀደመ የወታደራዊም የኢኮነሚ አጋዥ ቡድን አድቅቆ ከጫወታ ውጪ አድርጓል። እነ ስዩም፣ ዓባይ፣ አስመላሽ በሻአቢያና በህወሓት ተረሽነዋል። ጌታቸው አሰፋ ከአዲስ አበባ ሳይወጣ ነው የተበላው። ከመለስ ዜናዊ ኔትወርክ የቀረም የለም።

"…ኢሳይያስ አፈወርቂ ከስብሐት ነጋ በላይ የሚያምነው የለም። ኦነግ አስመራ ሰልጥኖ በትግራይ በኩል ሲያልፍ የተረከበው ስብሐት ነጋ ነው። ኦነግን ተከትለው የሸአቢያና የህወሓት ታማኝ ጦሮች ኢትዮጵያ ገብተዋል። በኦሮሚያ ዐማራን የሚያጸዳው ይሄ ጽንፈኝነትን ኤርትራ ሰልጥኖ የመጣ ኃይል ነው። በቀጣይ የኢትዮጵያ መከላከያ የሚሆነውም ይሄው ሰይጣናዊ አረመኔ ተደርጎ ሲሰለጥን የከረመው ኃይል ነው።

"…በኦሮሚያ ጫካዎች፣ በቤኒሻንጉል ደኖች፣ በሸዋ ግዛቶች አሁንም በአክራሪው ጽንፈኛ የኦሮሞ እስላሞችና በጴንጤ ተባባሪዎቹ፣ እስላም ክርስቲያኑ ዐማራ እየታረደ ነው። የኦሮሞ ጫካዎች በኦርቶዶክስ ካህናት አስከሬን ተሞልተዋል። ከላኪዎቻቸው ተልዕኮውን ተቀብለው ሥልጣን ላይ ያሉት ከምንግዜውም በላይ ከባድ ጥፋት ለመፈጸም ዝግጅታቸውን ፈጽመዋል። ከአውሮጳም፣ ከምዕራቡ ዓለምም ይህን ጥፋት ለመፈጸም ተጠራርተው ወደ ሃገር ቤትም በሕጋዊ መንገድ መንግሥቱ ዕያወቃቸው ገብተዋል። በየጫካው ለሚገኘው አራጅ ቡድን ስንቅና ትጥቅም በገፍ በመቅረብ ላይ ነው የሚገኙት። እና አሁን ዐማራው እየነቃ ሲመጣ በኢትዮጵያ ከባድ ጥፋትና ውድመትም ይከሰታል። በዚህ መሃል የሚጸዳው ሁሉ ይጸዳል። ጽዳቱም በተለይ ከቤተ መቅደሱ ሹመኞች ይጀምራል። ለኃአጥአን የታዘዘው መቅሰፍትም ለጻድቃንም ሁሉ ይተርፋል። የታጠቀ፣ የተዘጋጀ፣ ቀድሞ የነቃውም ራሱም ተርፎ ብዙውንም ያተርፋል፣ አሳባቂው፣ አውደልዳዩ፣ ቧልተኛው፣ በሙሉ ግን ዓይኑ እያየ ጆሮውም እየሰማ የእርሱ ከሆኑቱ ሁሉ ጋር ይጠረጋል። በመጨረሻም ካህኑ ህዝቅያስ ለሚጠበቀው መንገድ ጠርጎ በኢትዮጵያ አሸናፊነት ጨዋታው ይጠናቀቃል። 

"…ከነገድ ዐማራውን፣ ከእምነት ባለማዕተቡን በማጥፋት እነሱ ተርፈው ምድሪቱን ይወርሱ የመሰላቸው ሞኞች የወራሪዎቹ ሰይፍ ያልፋቸው ዘንድ ልዩ ልዩ ምስጢራዊ ኮድ ተለዋውጠው ጨርሰዋል። ጃዋር ሲታሰር ፀጥታ የሰፈነው በምስጢራዊ ኮዱ ምክንያት ነው። ጽንፈኞቹ በሙሉ፣ መከላከያውን፣ ፌደራልና የክልል ፖሊሱን፣ የአዲስ አበባን የጸጥታ ክፍል በሙሉ ተቆጣጥረዋል። ከጎረቤትህ የመታረጃህ ሰይፍ ተስሎ ተቀምጧል። እነርሱ በየቤተ እምነታቸው ሰብከው፣ ነክረው ወስነው ጨርሰዋል። በማጥፋት ለመውረስ ቋምጠዋል። ከባለማዕተቡ ወገን ለሆዱ ያደረውን እንደ ባርያ ስለሚጭኑት ፍርሃት አይሰማቸውም። በየመጋዘናቸው፣ በየጫካው፣ በየዱሩ፣ በየቤታቸውም ጭምር ድምጽ ያለውንም፣ ድምጽ አልባውንም መሣሪያ ከዝነው አዘጋጅተዋል። ክርስቲያኑን መሳሪያህን አስመዝግብ ብለው ማን ማን ጋር መሣሪያ እንዳለ አስቀድመው መዝግበው ጨርሰዋል። ቀኑ እስኪደርስም አላደርስ ብሏቸው አቁነጥንጧቸዋል። (ጴንጤቆስጤ እንኳ በተዋሕዶ ላይ መዛት መፎከር የጀመረው ያየውን አይቶ፣ የሰማውንም ሰምቶ ነው።) እናም የመለስን ኔትወርክ ለመበጣጠስ ሲባል በምክክር የተጀመረው ግፍና ጭካኔ ዐማራና ትግሬን እሳትና ጭድ በማድረግ ደም በማቃባት ወደ ፍጻሜው እየቀረበ ነው። ከህወሓት ወገን ያሉት የመለስ ኔትወርኮች በሙሉ ጸድተዋል። የኢሳያስ ስብሐት ጭካኔ መለስን ለመበቀል ሲሉ መቃብሩን ከቅድስት ሥላሴ ጠርገው ለመጣል ካቴድራሉን በዕድሳት ሰበብ እስከመዝጋት ደርሰዋል።

"…በቀጣይ ጦርነቱን ወደ ሃይማኖት ያመጡታል። ከሊባኖስ ያስገቡትን አህባሽ፣ የሳውዲውን ወሃቢይ ከአዲሱ የምዕራባውያኑ የመናፍቃን ቡድን ጋር በማጣመር በአንድነት ትንኮሳ ይጀምራሉ። መሃል ሃገር ያለው ዐማራ ስላልተሰበረ እሱን ለመስበር ከሃይማኖት ትንኮሳ የተሻለ ስለሌለ ለዚህ ትንኮሳ የተመረጡት የኦሮሞና የደቡብ አክራሪ ጴንጤዎችና እስላሞች ወደፊት እንዲመጡ ተደርጓል። እናም በቅርቡ ኦርቶዶክሳውያንን በማስቆጣት በዋናነት አዲስ አበባና በኦሮሚያ፣ በደቡብ፣ በድሬደዋና በሐረሬ የሚገኙ ኦርቶዶክሳውያን ላይ የቅጣት በትራቸውን ለመምዘዝ ወስነው ጨርሰዋል።

"…በተለይ በአዲስ አበባ በሚደረገው ጭፍጨፋ እነሱም በጅምላ አብረው እንዳይጠፉ ምስጢራዊ ምልክቶች በቤታቸው በራፍ ላይ እንዲያስቀምጡም ተነግሯቸዋል። እስራኤላውያን በግብፅ ሳሉ ቀሳፊው መልአክ እንዳይጎበኛቸው በቤታቸው ጉበን ላይ የበግ ደም ቀብተው እንዲጠብቁ እንደታዘዙት ሁሉ ኦሮሞዎቹም ከወዲሁ የቤታቸውን በራፍ በዋቃ ጉራቻ፣ በጥቁሩ አምላክ በጨለማው ንጉሥ መልክ ጥቁር ቀለም በራፋቸውን እንዲቀቡም መመሪያው ወርዶላቸዋል። ጴንጤ የሚቀባው፣ ዋቄፈታና እስላሞችም የሚቀቡትም ዲዛይኑ የተለያየ እንዲሆን ነው የተነገራቸው። ይሄን በራፍን ጥቁር ቀለም የመቀባቱን ተግባርም በተለይ በአዲስ አበባ ከተማ በሰፊው ተጀምሯል። (ይሄ ከተነገረኝ በኋላ እኔም ራሴ አረጋግጫለሁ። የብዙ የኦሮሞ እስላሞች እና ፕሮቴስታንቶች የውጭ በር ጥቁር ቀለም ተቀብቷል። ጉለሌ አካባቢ እኔም የብዙ ኦሮሞዎችን ደጃፍ ፎቶ አስነሥቼ ይዤዋለሁ። እናንተም ማረጋገጥ ትችላላችሁ) ይሄ ግን ማንንም አያድንም።

ክፍል ፪
762 viewsBantegize 19, 19:50
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-12-21 22:35:31


የማይጠገበው የአባቶቻችን የቅዱሳን ትምህርትና ምክር !


በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሀዱ አምላክ አሜን !

[ ፍኖተ ሕይወት - ፻፳፰ - ]



[ ትዕግሥትን በተመለከተ ]


"ወዳጄ ሆይ ስለ ጌታ ብለህ አገልግሎትህን በትዕግሥት መፈጸም ሲገባህ እንደ መዋረድ የምታስብ ከሆነ ከአንተ ይልቅ ንጉሥ ሆኖ ሳለ ራሱን ዝቅ በማድረግ እኛን ማገልገሉን እንደ ስድብ መቍጠር ያለበት እርሱ ጌታችን መድኀኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ነበር፡፡

አንተ ይህን ለእርሱ ማገልገልን ከንቱ ድካም ነው አልህ፡፡ በዚህ ተግባርህም ሃኬተኞችን መሰልህ፡፡ ለኃጢአተኞችና ለሃኬተኞች ወዮላቸው። ስለ ጌታችን ብለን መከራን መታገሥ ካልቻልን ስለምን ታዲያ ከዚህ ዓለም ተለየን ?

ተወዳጆች ሆይ ! ስለ ጌታችን ብሎ መከራን የማይታገሥ ማን ነው? ተወዳጆች ሆይ ከእናንተ የሚጠበቀው ጥቂት እንደሆነ የምታገኙት ግን ታላቅ እንደሆነ ልብ በሉ፡፡ እኛ ትዕግሥትን ገንዘብ አድርገን የእግዚአብሔርን ፈቃድ ስንፈጽም እርሱ ለእኛ የገባውን ቃል ኪዳን ይጠብቃል፡፡ "እስከ መጨረሻው የሚጸና እርሱ ይድናል" ይላልና ቃሉ መዳናችንን በትዕግሥት እንፈጽም፡፡"




[ ቅዱስ ኤፍሬም ሶርያዊ ]


829 viewsBantegize 19, 19:35
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-12-09 18:48:31
"መንግሥተ ሰማያት ቀርባለችና ንስሐ ግቡ::" /ማቴ ፫:፫/

"ፍቅር ያጌብረኒ ከመ እንግር ዜናሆሙ ለቅዱሳን"::አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ /መጽሐፈ ምሥጢር/
https://t.me/zikirekdusn
862 viewsBantegize 19, 15:48
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-11-30 22:18:38 ለምንድን ነው የምንጾመው?

እንደ አንድ ክርስቲያን [በግልም በአዋጅም] በመደበኛነት እንድንጾም ታዝዘናል፡፡ ኾኖም እስኪ ጥያቄ እናንሣ! ለምንድን ነው የምንጾመው? በመራባችን ምክንያት እግዚአብሔር ደስ ይሰኛልን? በየቀኑ እግዚአ ብሔርን ለማገልገል በቂ ነው የሚባል ምግብ ልናገኝ እንደሚገባን የታ ወቀ የተረዳ ነው፡፡ ታዲያ በዚህ [በመጾማችን - በመራባችን] ውስጥ ያለው ምሥጢርና እግዚአብሔር ከዚያ ውስጥ የሚፈልግብን ፍሬ ምንድን ነው?

በልብ መታሰቡ፣ በቃል መነገሩ፣ በቅዱሳት መጻሕፍትም መዘከሩ ይክበር ይመስገንና ጌታችንና መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስም በመጾ ማቸው ምክንያት የሚገበዙትን እጅግ ወቅሷቸዋል፡፡ ጾም የሚያስታብይ አይደለም ሲላቸው ነው፡፡
ስለዚህ እግዚአብሔር እንድንጾም የሚፈልገው ስለ ኹለት ዋና ዋና ምክንያቶች ነው፡-

#አንደኛው፥ ራሳችንን ከዚህ ዓለም ነገሮች - ከእነርሱ ዋናውም ከምግብ - አርቀን ወደ መንፈሳዊ ነገሮች እንድናቀርብ ስለሚፈልግ ነው፡፡ በየጊዜው በየሰዓቱ ስንበላ ሥጋችን ተድላ ደስታ ያደርጋልና፡፡ በመሠረቱ ምግብ በልቶ ደስ መሰኘት በራሱ ነውር ኾኖ አይደለም፡፡ ነገር ግን እግዚአብሔር የአማናዊ ተድላና ደስታ ምንጩ መንፈሳዊ ተግባር እንደ ኾነ እናስብ ዘንድ ይሻል፡፡ ስለዚህ እንድንጾም የሚፈልገ ውና በዚያውም ውስጥ እንድናስተውለው የሚፈልገው የመጀመሪያው ምክንያት ይኸው ነው፡፡

#ኹለተኛው ምክንያት ደግሞ ማጣት ዘወትር እንዲራቡ ከሚያደርጋቸ ው ሰዎች ጋር አንድነትና ኅብረት እንዲኖረን ስለሚሻ ነው፡፡ ሥርዓተ ቤተ ክርስቲያንን ተከትለን በየጊዜው ልንጾም እንችላለን፡፡ ይህ ሥርዓተ ቤተ ክርስቲያን አስገድዶአቸው ሳይኾን እጦት አስገድዶአቸው ያለማቋ ረጥ ዘወትር የሚጾሙ ሰዎች ግን አሉ፡፡ እግዚአብሔር ደግሞ ለእነዚህ ሰዎች እውነተኛ ፍቅር እንድናሳይ ይፈልጋል፡፡ አጥቶ የመራብ ትር ጕሙ ምን ማለት እንደ ኾነ እኛው ራሳችን በተግባር እንድናይ ይሻል፡፡ በጾማችን ውስጥ እንድናፈራው የሚፈልገው አንዱ ፍሬ ይኼ ነው፡፡ ጾም የፍቅረ ቢጽ እናት ነች የምንለውም ለዚህ ነው፡፡

ስለዚህ ጾማችን እግዚአብሔር የሚፈልገውና የሚቀበለው እንዲኾንልን በጾማችን ወቅት ወጪአችንን መቆጠብ ሳይኾን እነዚህን ድኾች እንድ ናስብ ያስፈልጋል፡፡

#አምስቱ_የንስሐ_መንገዶች፣ በቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ፣ ገጽ 71-72
#ገብረ_እግዚአብሔር_ኪደ እንደተረጎመው

ማወቅ መልካም ነው ያወቁትን ማሳወቅ ደግሞ ፍፁም በጎነት ነው ። በምድር ላይ የምናደርጋቸው መልካም ነገሮች ሁሉ በሰማይ ላይ የዘላለም ደመወዝ ሆነው ይከፈሉናል ።
........@TrufatNatanim
@TrufatNatanim
@TrufatNatanim
ለጓደኞቻችሁ ቻናሉን እንዲቀላቀሉ እንድትጋብዙልን በእግዚአብሄር ስም እንጠይቃለን!!!
1.1K viewsBantegize 19, 19:18
ክፈት / አስተያየት ይስጡ