Get Mystery Box with random crypto!

'… መልእክቱ የሚሠራው አይተው ለሚያሾፉት፣ ለሚቀልዱት፣ አይደለም። ለሚጠቀሙበት ነው። ይህን መልእ | 📖አስተማሪ ታሪኮች እና የአበው 🖊ምክሮች

"… መልእክቱ የሚሠራው አይተው ለሚያሾፉት፣ ለሚቀልዱት፣ አይደለም። ለሚጠቀሙበት ነው። ይህን መልእክት በወረቀት አባዝታችሁ ላልሰማ አሰሙ። ላላየም አሳዩ። በቤተሰብ ደረጃ ተሰብስባችሁ አንብቡት። ተወያዩ፣ የማታ ጸሎት በቤተሰብ ደረጃ አሁኑኑ ጀምሩ። ጭፈራ፣ ሲጋራ፣ ዝሙት፣ ስካርና ጫት፣ ሀሺሽም፣ አባካኝነትንም አስወግዱ። ተረዳዱ፣ ተመካከሩ። አንዱ ስለአንዱ ግድ ይበለው። ወጣቶች በእናት በአባታችሁ ተመረቁ። አካላዊ እንቅስቃሴ አድርጉ፣ ስገዱ፣ ጹሙ፣ ጸልዩ። እንደ ርግብ የዋሕ፣ ልባም፣ እንደ እባብም ብልህ ሁኑ። ተከባበሩ፣ ተረዳዱ፣ ተፋቀሩ። ንስሐ ግቡ፣ በትዳራችሁ ጽኑ፣ አግቡ፣ ውለዱ፣ ዘራችሁን አብዙ። ሰንበትን አስቀድሱ፣ ፀበልም ተጠመቁ። ቁረቡ።

"…በቃላችሁ፣ በንግግራችሁ፣ በወጋችሁ ውስጥ ሁሉ የፍርሃት ቃልን አትጠቀሙ። ክርስቲያን አሸናፊ ነው። ዐማራ ሃገር አቅኚ ነው። ኦርቶዶክስ የኢትዮጵያ እንጀራዋ፣ ጌጥ መገለጫዋ ነው። እናም አትፍሩ። በወሎ እንዳሉት፣ በጎንደርም፣ በሸዋና በጎጃም ካሉት ሙስሊም ወንድሞቻችሁ ጋርም ኅብረት አንድነቱን ፍጠሩ። የትግሬ እልሁ ስላልበረደለት፣ ስላደነዘዙትም ብዙም በሱ ላይ አትድከሙ። ተደራጁ፣ ተሰባሰቡ፣ ማንም ተበተን ሲላችሁ አትበተኑ። ቀበሌ፣ ወረዳ፣ ምክር ቤቶቹን ሁሉ ወንበሩን ሙሉ። ለመገዛት ብቻ፣ ለመሰደብ፣ ለመረገጥ ብቻ አትኑሩ። ለምን? በሉ። ጠይቁ የደቡብ ኦርቶዶክሶች ህመም የኦሮሞ ኦርቶዶክሶችም ህመም ይሁን፣ በየትም ስፍራ ኦርቶዶክስ ስትጠቃ በአንድነት ተነሡ። በወታደር ብዛት የሚያሸንፍ አገዛዝ የለም። ምንጊዜም አሸናዊ ህዝብ ነው። ከድንዛዜ የነቃ ህዝብ ያሸንፋል። አሁን ያልነቃው የሻአቢያ፣ የኦነግና የህወሓት ዱላ ሲበዛበት ይባንናል። እናንተ ግን በጸሎት ጭምር በርቱም ተብላችኋል። ጎንደሮችም መከራው ቢቀንስ ያን የተለመደ ምህላችሁን ጀምሩት ተብላችኋል።

"… በመጨረሻም "የመኾኒ ትንቢትም" ወደ መቋጫው ተቃርቧል። ፍጻሜውንም ያገኛል። በመሆኒ ምን ይሆናልኩት ብዬ ለጠየቅኩት ጥያቄ በመሆኒና በርብ ወንዝ ስለሚከወነው ጊዜው ሲደርስ እንነግርሃለን ብለዋል።

"… ኡፍፍፎይ…  ጨረስኩ… ተፈጸመ።