Get Mystery Box with random crypto!

ወይዘሮ አዳነች የተጠየቁት ጥያቄ አድስ አበባ ከተማ ውስጥ ከኦሮሞ ውጭ ያሉት ሁሉም ተማሪወች የሚዘ | TOP MEREJA

ወይዘሮ አዳነች የተጠየቁት ጥያቄ አድስ አበባ ከተማ ውስጥ ከኦሮሞ ውጭ ያሉት ሁሉም ተማሪወች የሚዘምሩት የኢትዮጵያን ህዝብ መዝሙር ሲሆን የሚሰቅሉትም የሚያውቁትም ባንድራ የኢትዮጵያን ባንድራ ነው ነገር ግን የኦሮሞ ዘር ናቸው የተባሉት ተነጥለው ለምንድነው የኢትዮጵያን መዝሙር ትተው የኢትዮጵያን ህዝብ ባንድራ ትተው የኦሮሚያ ክልልን መዝሙር እንድዘምሩ ተፈለገ። እነሱም ይዘምሩ ሌሎች ኦሮምኛ የማይችሉ ኦሮሞ ያልሆኑ ተማሪወችን በማስገደድ የኦሮሞን ባንድራና መዝሙር ማዘመሩና ማሰቀሉ ችግር እየፈጠረ ነው ጥያቄው። ወይዘሮ አዳነች እንዳሉት ከሆነ የሁሉም ክልል ተማሪወች የኢትዮጵያን ህዝብ መዝሙርም ሆነ ባንድራ ጥለው የክልላቸውን መዝሙር ቢዘምሩ ችግር አይፈጥሞይ ነው።
ምንም ወደ ጎን መረገጥ አያስፈልግም አድስ አበባ የኦሮሞ ብቻ ነች ከኦሮሞ ውጭ ዘር ያለው ቦታ የለውም ነው ነገሩ። በርግጥ በቅርቡ በወለጋ የተካሄደው አይነት ጭፍጨፋ በ አድስ አበባ ኦሮሞ ባልሆኑ ነዋሪወች ላይ የሚፈጸም ይሆናል። በጋራ ቁሙ በጋራ ታገሉ ሁሉም ኦሮሞውም ትግሬም አማራውም ደቡቡም ሁሉም በጋራ በሰላም የሚኖርበትን አየር መፍጠር ያስፈልጋል። የኦሮሞ ፖለቲከኞች አካሄድ በጣም በጣም አጥፊና አፍራሽ ነው