Get Mystery Box with random crypto!

አንዳንድ የአማራ አክቲቪስቶች ዶክተር ሃንጋሳ ልናዘዝ ብለው የተናገሩትን ለሴራ ነው የተናገረው ከሸ | TOP MEREJA

አንዳንድ የአማራ አክቲቪስቶች ዶክተር ሃንጋሳ ልናዘዝ ብለው የተናገሩትን ለሴራ ነው የተናገረው ከሸኔ ጋር ግንኙነት ስላለው ነው የመንግስትን ስም ለማጥፋት ነው ወዘተረፈ ሲሉ እሰማለሁ።
ሰውየው የተናገሩበትን ምክንያት ፈጣሪ ያውቃል። ነገር ግን ሸኔ የሚሉት 2 ግሩፕ እንዳለ ብዙው የኦሮሞ ምሁራንና ህዝብ ያውቃሉ በሚስጥርም ያወራሉ። በዚህ ቻናል ላይም ከ3 ወር በፊት 2 ሸኔ እንዳለ ፅፌላችሁ ነበር። አሁን ላይ ሳስበው ግን 3 ሸኔም ሳይኖር አይቀርም
1. ሸኔ (ኦነግ) ታላቅ ኦሮሚያ እመሰርታለሁ የሚለው አካል

2. በፌደራሉና ኦሮሚያ ክልል የተደራጀ የታጠቀ ሃይል (የኦነግ ልብስ ለብሶ በተለያዩ የአማራና አንዳንድ ክልሎች በከባድ መሳሪያ ግድያ የሚፈፅም በመንግስት የታጠቀ ቡድን
3. በዞኖች የተደራጀ የወጣቶች ዘረኛ መንጋ ይህ መንጋ የሚኒሻወችና ወጣቶች ስብስብ ሲሆን በአብዘሃኛው በቀበሌወች እየተጠራሩ ኦሮሞ ያልሆኑትን ይገላሉ

እበዚህ ያሉ ይመስለኛል።
የመጀመሪያወቹ ሁለቱ እንዳሉ ግን ብዙው የኦሮሞ ህዝብ ያውቃል።

ሰሞኑን የአደጋ ስጋትና ስራ አመራሩን ጨምረው በኢንፎርሜሽንና መረብ ደህንነት ያሉ ሰወችን በማፈን ላይ ይገኛሉ። ይህም ምናልባትም እንደ ሃንጋስስ መረጃ እንዳያወጡ በሚል ይመስለኛል።