Get Mystery Box with random crypto!

ቶኔቶር

የቴሌግራም ቻናል አርማ tonetor24 — ቶኔቶር
የቴሌግራም ቻናል አርማ tonetor24 — ቶኔቶር
የሰርጥ አድራሻ: @tonetor24
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 227
የሰርጥ መግለጫ

የተለያዩ የተዋህዶ ስእሎች እና ጥቅሶችን ለማግኘት
እንዲሁም ስንክሳር ዘዘወትር እና ትምህርተ ወንጌል
የተዋህዶ መዝሙሮች እና መንፈሣዊ ቪዲዮዎችን

እንዲሁም አስተማሪ ፅሁፎችን ያገኙበታል
@Tonetor24 ለጓደኞቾ ያጋሩ እና
ግሩፓችን@Tewahido24 ማግኘት ይችላሉ
አስተያየት ካለዎት @Napi_7 ላይ ያድርሱልን

Ratings & Reviews

3.50

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

1

3 stars

1

2 stars

0

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች

2022-07-14 18:17:33
47 views15:17
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-14 18:17:25


በስመ አብ ፡ ወወልድ ፡ ወመንፈስ ቅዱስ አሀዱ አምላክ አሜን፡፡



"የቅድስት ሥላሴ ዕምነት የሃይማኖት መጨረሻ ናት፡፡ የሥላሴ ዕምነት መግቢያ በር ወልድ ዋህድ ብሎ ማመን ነው፡፡

የኦርቶዶክስ ሃይማኖት ሥርዓት በዚህ የሥላሴ አርአያ ተመሠረተ፡፡ ይህ ግሩም የሆነ የሥላሴ ስም ለታመኑ የሕይወት መታወቂያ ማኅተም ነው ለዝንጉዎች ግን የጥፋታቸው ቁልፍ ነው፡፡

ይህ ግሩም የሆነ የሥላሴ ስም የሕሙማን መፈወሻ የክፉዎች አጋንንት ማባረሪያ ነው፡፡

ይህ ግሩም የሆነ የሥላሴ ስም የአስማተኞችን ወይም የጠንቋዮችን ጥበብ የሚያጠፋና የሟርተኞችን መርዝ የሚያበርስ [ የሚያከሽፍ ] ነው፡፡

ይህ ግሩም የሥላሴ ስም የበሽተኞች መድኃኒት የሙታን ትንሣኤያቸው ነው፡፡ ይህ ግሩም የሆነ የሥላሴ ስም አሸናፊ የሆኑ የሰማዕታት የገድላቸው ሞገስ የብሩካን ጻድቃን የጸሎታቸው የመልካም መዓዛ ሽታ ነው፡፡

ይህ ግሩም የሆነ የሥላሴ ስም የረከሱትን የሚቀድሳቸው የተዳደፉትን የሚያነጻቸው ነው፡፡ይህ ግሩም የሆነ የሥላሴ ስም እንደ መጎናጸፊያ እጎናጸፈዋለሁ ከእንቁ እንደተሰራ እንደ እራስ ወርቅም እቀዳጀዋለሁ፡፡

በዚህ ግሩም በሆነ የሥላሴ ስም እታመናለሁ በመጎንበስም እሰግድለታለሁ፡፡ ለዚህ ግሩም አስፈሪና አስደንጋጭ ለሆነ የሥላሴ ስም በፊቱ ተንበርክኬ በደስታ እሰግዳለሁ፡፡"

[ ሰይፈ ሥላሴ ]


╭══•: |❀:✧๑♡๑✧:❀| :•══╮


"ከመዝ ሥላሴ" [ ሥላሴ እንዲህ ነው ]

[ ቅዱስ ሳዊርያኖስ ]

[ በርዕሰ ሊቃውንት አባ ገብረ ኪዳን ግርማ ]


▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬


46 views15:17
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-14 15:50:26
44 views12:50
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-14 15:50:23


ድንቅ ስጦታ ለኦርቶዶክሳውያንና በሰውነት ለሚያምኑ ሁሉ !


" ሥዝም ሰብአዊነት "


የሰው ጥንተ ተፈጥሮና የምዕራቡ ዓለም ኦርቶዶክስ ጠል የሉላዊነትና የሴኩላሪዝም እሳቤዎች በአስደናቂ ሁኔታ የተብራሩበት መጽሐፍ !


[ እጅግ በሚወደዱ በሊቀ ልሳናት ፋንታሁን ዋቄ ]



▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬


47 views12:50
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-14 00:26:29
74 views21:26
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-14 00:26:27


† እንኩዋን ለአጋእዝተ ዓለም ሥላሴ እና ለቅዱሳን አበው አብርሃም: አባ ሲኖዳ እና አባ ጊዮርጊስ ዘጋሥጫ ዓመታዊ በዓል በሰላም አደረሳችሁ †


† ሥሉስ ቅዱስ †


በአንድነቱ ምንታዌ [ሁለትነት] : በሦስትነቱ ርባዔ [አራትነት] የሌለበት የዘለዓለም አምላክ: የፍጥረታት ሁሉ ፈጣሪ እግዚአብሔር ነው:: አብ : ወልድ : መንፈስ ቅዱስ በስም: በአካል: በግብር ሦስትነት: በባሕርይ: በሕልውናና በፈቃድ አንድነት የጸኑ ናቸው:: በዚህ ጊዜ ተገኙ: በዚህ ጊዜ ያልፋሉ አይባሉም:: መጀመሪያም መጨረሻም እነርሱ ናቸውና::

ርሕሩሐን ናቸውና በእናት ሥርዓት " ቅድስት_ሥላሴ " እንላቸዋለን:: የሚጠላቸው [የማያምንባቸውን] አይጠሉም:: የሚወዳቸውን ግን እጽፍ ድርብ ይወዱታል:: በቤቱም መጥተው ያድራሉ::

ከፍጥረታት ወገን ከእመቤታችን ቀጥሎ የአብርሃምን ያህል በሥላሴ ዘንድ የተወደደ ፍጡር የለም:: አባታችን ቅዱስ አብርሃም የደግነት ሁሉ አባት ነውና በኬብሮን በመምሬ ዛፍ ሥር ሥላሴን ተቀብሎ አስተናግዷል:: ሥላሴ አኀዜ ዓለም [ዓለምን በእጁ የያዘ] ነው:: ነገር ግን በፍቅር ለሚሻው በፍቅር ይመጣል::

አባታችን አብርሃም በ፺፱ [99] ዓመቱ: እናታችን ሣራ በ፹፱ [89] ዓመቷ ሥላሴን በድንኩዋናቸው አስተናገዱ:: አብርሃም እግራቸውን አጠበ:: [ወይ መታደል!] በጀርባውም አዘላቸው:: [ድንቅ አባት!] ምሳቸውንም አቀረበላቸው:: እንደሚበሉ ሆኑለት:: በዚያው ዕለትም የይስሐቅን መወለድ አበሠሩት:: ቅድስት ሣራ ሳቀች:: እንደ ዘንድሮ ወገኖቻችን የማሾፍ አይደለም:: ደስታና ጉጉት የፈጠረው እንጂ:: ሥላሴ "ምንት አስሐቃ ለሣራ በባሕቲታ" ብለው ነበርና በዚህም ምክንያት ነው "ይስሐቅ" የተባለው::

ሥላሴን ያስተናገደች ድንኩዋን [ሐይመት] የድንግል እመቤታችን ማርያም ምሳሌ ናት:: በድንግል ላይ አብ ለአጽንኦ: መንፈስ ቅዱስ ለአንጽሖ: ወልድ በተለየ አካሉ ለሥጋዌ በእርሷ ላይ አርፈዋል / አድረዋልና::


† ታላቁ አባ ሲኖዳ †


የባሕታውን ሁሉ አለቃቸው ታላቁ ቅዱስ ሲኖዳ :-

¤ በ፬ [4] ኛው መቶ ክ/ዘመን የተወለደ
¤ በእናቱ ማሕጸን ሳለ መላእክት በሰይፈ እሳት ይጠብቁት የነበረ
¤ የታላቅነት ትንቢት የተነገረለት
¤ ገና ሳይወለድ ሥውራን አበው የሰገዱለት
¤ በሕጻን ሰውነቱ ጾምና ጸሎትን የጀመረ
¤ የልጅነት ቁርስና ምሳውን ለነዳያን ያካፍል የነበረ
¤ በ፱ [9] ዓመቱ ወደ በርሃ የመነነ
¤ የአባ አብጐል ደቀ መዝሙር የሆነ አባት ነው::

ሲመነኩስም በእግዚአብሔር ትእዛዝ የሠለስቱ_ደቂቅ አስኬማ: የኤልያስ ቆብዕ እና የመጥምቁ ዮሐንስ ቅናትን [መታጠቂያ] ከያሉበት መላእክት አምጥተውለት የመነኮሰ
¤ ዓለምን በሙሉ በጸሎቱ ይጠብቅ የነበረ
¤ የግብፅን በርሃ በብርሃን የሞላ
¤ በርካታ ድርሰቶችን የደረሰ
¤ ያለ ማቇረጥ በየቀኑ ከ፻ [100] ዓመታት በላይ ከጌታችን ክርስቶስ ጋር የተነጋገረ
¤ ደመናትን ተጭኖ ይሔድ የነበረና
¤ ያለ ዕረፍት ለ፩፻፲፩ [111] ዓመታት ከ፪ [2] ወራት ፈጣሪውን ያገለገለ አባት ነው::

በዚህም ምክንያት አንድ ቀን ገዳማውያን ሁሉ እየሰሙ እንዲህ የሚል ቃል ከሰማይ መጣ:: "ሲኖዳ ተሠይመ አርሲመትሪዳ "[ሲኖዳ አርሲመትሪዳ ሆኗል:: ማለትም ለባሕታውያን ሁሉ አለቃ ሁኖ ተመርጧል ማለት ነው::]

ቅዱሱ የጌታችንን እግር እያጠበም ይጠጣ ነበር:: በዚህች ዕለት በ፩፻፳ [120] ዓመቱ ጌታችን ወርዶ ሲያሳርገው አቡነ ኪሮስ "ታላቅ ምሰሶ [ታላቅ ዛፍ] ወደቀ" ብለው አልቅሰዋል:: ሲኖዳ ማለት "ደግ ሰው" ማለት ነው::

† አባ_ጊዮርጊስ_ዘጋስጫ †
[GIYORGIS_OF_SEGLA]


ታላቁ ኢትዮዽያዊ ሊቅና ጻድቅ የተወለደው ወሎ ጋስጫ ውስጥ በ1358 ዓ/ም ነው:: ከልጅነቱ ትምሕርት አልገባሕ ቢለውም በልቡናው ግን ቅን እና ታዛዥ ነበር:: መምሕሩ "ትምሕርት አይገባውምና ውሰዱት" ቢላቸው "የእግዚአብሔር ነውና ያገልግላችሁ" ብለው መለሱት:: መገፋቱን የተመለከተ አባ ጊዮርጊስ እመቤታታችንን ከልቡ ይወዳት ነበረና ይማጸናት ገባ::

ቀን ቀን ገዳሙን ሲረዳ: እሕል ሲፈጭና ሲከካ: ላቡንም ሲያፈስ ውሎ ሌሊት ደግሞ ሲጸልይ ያነጋ ነበር:: ድንግል እመቤታችን ጸሎቱን ሰምታለችና ቅዱስ_ዑራኤልን አስከትላ መጣችለት:: በንጹሐት እጆቿ ባርካው ምሥጢርንም ነገረችው:: "ወነገረቶ ሐምስተ ቃላተ" እንዲል:: ጽዋዐ ልቡናን አጠጥታው ተሠወረችው::

ከዚህች ሰዓት ጀምሮ አባ ጊዮርጊስ ፍጹም ተለወጠ:: በጽድቁ ላይ የሊቅነትን ካባ ደረበ:: ቅዱሳት መጻሕፍትን ይተነትናቸው: መናፍቃንንም ምላሽ ያሳጣቸው ገባ:: የተረጐማቸውና ያተታቸውን ሳይጨምር ፵፩ [41] ድርሰቶችን ደረሰ:: [መጽሐፈ ሰዓታት: መጽሐፈ ምሥጢር: አርጋኖን: ኆኅተ ብርሃን: ውዳሴ መስቀል: ወዘተ . . . የእርሱ ድርሰቶች ነበሩ]

ስለ ሃይማኖትም ጠበቃ ነበር:: ስለ ቅድስናውና ውለታው የኢ/ኦ/ተ/ቤ እንዲህ ትጠራዋለች :-

፩. ሊቀ_ሊቃውንት
፪. በላዔ_መጻሕፍት
፫. ዓምደ_ሃይማኖት
፬. ዳግማዊ_ቄርሎስ
፭. ጠቢብ_ወማዕምር

ጻድቁ ሊቅ በተወለደ በ፷ [60] ዓመቱ በ፲፻፬፻፲፰ [1418] ዓ/ም በዚህች ቀን ዐርፏል:: አባ ጊዮርጊስ የተወለደውም ያረፈውም ሐምሌ ፯ [7] ቀን ነው::

የሥላሴ ቸርነት: የአብርሃም ደግነት: የአበው አባ ጊዮርጊስና አባ ሲኖዳ በረከት ከሁላችን ጋር ይሁን::



ሐምሌ ፯ [7] ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት

፩. ቅዱሳን አብርሃምና ሣራ [ሥላሴን ያስተናገዱ]
፪. ብሥራተ ልደተ ይስሐቅ
፫. ታላቁ አባ ሲኖዳ [የባሕታውያን ሁሉ አለቃ]
፬. አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ [ሊቀ ሊቃውንት: ኢትዮዽያዊ
የሃይማኖት ምሰሶ]
፭.ቅዱስ አግናጥዮስ ዘአንጾኪያ [ምጥው ለአንበሳ]
፮. አባ መቃቢስ
፯. አባ አግራጥስ

ወርሐዊ በዓላት

፩. አባ ዳንኤል ዘገዳመ ሲሐት
፪. አባ ባውላ ገዳማዊ
፫. ቅዱስ አትናቴዎስ ሐዋርያዊ

"እግዚአብሔርም ለአብርሃም ተስፋ በሰጠው ጊዜ :- 'በእውነት እየባረክሁ እባርክሃለሁ:: እያበዛሁም አበዛሃለሁ' ብሎ ከእርሱ በሚበልጥ በማንም ሊምል ስላልቻለ በራሱ ማለ:: እንዲሁም እርሱ ከታገሠ በሁዋላ ተስፋውን አገኘ:: " [ዕብ.፮፥፲፫] (6:13)

የጌታ የኢየሱስ ክርስቶስ ጸጋ: የእግዚአብሔርም ፍቅር: የመንፈስ ቅዱስም ሕብረት ከሁላችሁ ጋር ይሁን:: አሜን::" [ቆሮ.፲፫፥፲፬] (13:14)


† ወስብሐት ለእግዚአብሔር †


" ፍቅር ያጌብረኒ ከመ እንግር ዜናሆሙ ለቅዱሳን":: /የቅዱሳንን ዜና [ታሪክ] እንድመሰክር ፍቅር ያስገድደኛል:: አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ /መጽሐፈ ምሥጢር/


[ ዲ/ን ዮርዳኖስ አበበ ]

▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬


66 views21:26
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-13 20:35:57

እንኩዋን ለአጋእዝተ ዓለም ሥላሴ እና ለቅዱሳን አበው አብርሃም ፥ አባ ሲኖዳ እና አባ ጊዮርጊስ ዘጋሥጫ ዓመታዊ በዓል በሰላም አደረሳችሁ።

76 views17:35
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-13 19:30:37
76 views16:30
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-13 19:30:34 ▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬


ሐሳዊ አጥማቅያን እና የአጋንንት ምስክርነት !


[ ክፍል አሥራ አምስት ]

▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬

" በአጋንንት ምትሃት የተታለሉ ሰዎች ! "

---------------------------------------------------

"ከበረሐውያን ሕይወትና አንደበት" በተሰኘው የዲ/ን ያረጋል አበጋዝ መጽሐፍ የአበው ገዳማዊ የክርስትና ሕይወትን የሚያሳዩ ድንቅ ብሂሎች ፣ ትምሕርቶችና ታሪኮች ቀርበውበታል። ከተካተቱት ታሪኮች መካከል ከዚህ ካነሳነው ርዕስ ጋር ለትምህርት የሚጠቅም በመሆኑ የአጋንንት ምትሐትንና በዚህም የተታለሉትን በተመለከተ አቅርበነዋል።

---------------------------------------------------

" በበረሃው ውስጥ በጣም ጽኑና ከባድ በሆነ ትኅምርት የሚጋደልና በአስጨናቂ ገድል የሚኖር አብራሚዮስ የሚባል ግብጻዊ ነበር። በሕሊናው ምትሀት ተጫወተበትና ወደ ቤተ ክርስቲያን ሄዶ ፦ "ዛሬ ሌሊት በራሱ በክርስቶስ ካህን ተደርጌያለሁና እንደ ቄስ እንድቀድስ ተቀበሉኝ" እያለ ከካህናቱ ጋር መወዛገብ ጀመረ።

አባቶችም ከነበረበት በረሃ አስወጥተው ብዙም አስጨናቂ ለሆነ መጠነኛ ገድልና በተረጋጋ ሕይወት እንዲኖር አደረጉት። ቀስ በቀስም አጋንንት በተንኮላቸው ከተጫወቱበት ምትሀትና ከነበረበት ቅዠት አውጥተው ድካሙን እንዲያውቅና ከሕመሙ እንዲያገግም አደረጉት።

---------------------------------------------------

ሄሮን የሚባል ጥሩ ተሰጥዖ የነበረውና ሕይወቱ ንጹሕ የሆነ ደግ ወጣት ነበር። ከብዙ ድካምና ተጋድሎ በኋላ ግን በትዕቢት ጾር ተጠቃና ችግር ላይ ወደቀ። አባቶችን መሳደብና መምህራነ ቤተ ክርስቲያንን መንቀፍ ጀመረ።

ቅዱሳት ምስጢራትንም ለመሳተፍ ፈቃደኛ አልሆነም። ቀድሞ በጣም ሲበዛ ጸዋሚና ተኃራሚ ነበር ከቅዱስ ምስጢር በመሳተፍና ከዚያ በኋላ በበረሃው የሚያገኘውን ማንኛውንም ቅጠላ ቅጠል በመቅመስ ብቻ ምግብ ሳይበላ ለሦስት ወራት ያህል በተደጋጋሚ ይቆይ ነበር።

አንድ ወቅት ከሌሎች ወንድሞች ጋር መንገድ ሲሄድ ወደሚሄዱበት እስኪደርሱ ድረስ ሌሎቹ ወንድሞች ሁለት ጊዜ ሲመገቡና ሦስት ጊዜ ውኃ ሲጠጡ እርሱ ግን ምንም ነገር አልቀመሰም ፣ እንዲያ ምንም ሳይቀምስ ግን ከመዝሙረ ዳዊት [አሥራ አምስት መዝሙራትንና ከዚያም መዝሙር] ፲፰ን ፣ የዕብራውያን መልእክትን ፣ ኢሳይያስንና ኤርምያስን በከፊል ፣ ከዚያም ወንጌለ ሉቃስን ፣ እንዲሁም መጽሐፈ ምሳሌን በልቡ ጸለየ፡፡ እንዲህ ሁሉ ሆኖም ሲራመድ ሌሎቹ ወንድሞች በቀላሉ አይደርሱበትም ነበር።

ኋላ ግን ከበኣቱ ወጥቶ ወደ እስክንድርያ ቴያትርና የጨዋታ ቦታዎችን ከማዘውተሩና ቅጥ ባጣ ሁኔታ መብልና መጠጥን ከመውደዱ የተነሣ ከአንዲት ዘፋኝ ጋር ተቀራረበና በኃጢአት ወደቀ ከዚያም በስውር አካሉ ጽኑ ሕመም አደረበትና ለስድስት ወር ያህል በጽኑ ሁኔታ ተሰቃየ፡፡

ኋላ ላይ ከታመመው አካሉ ውጭ እርሱ ተረፈና ዳነ ፣ ወደ ልቡም ተመልሶ ወደ አረጋውያን መጣና ይህን ሁሉ ተናዘዘ በአስገዳጅ ሁኔታ ምክንያት ወደ ድኅነት ተመለሰ፡፡ ከጥቂት ቀናት በኋላ ወደ ጥንት ተግባሩ ከመመለሱ በፊት ዐረፈ።

---------------------------------------------------

ፕቶለሚ የሚባል ለመግለጽ እንኳ በሚከብድ ጽኑ በሆነ አኗኗር የሚኖር ሌላ መነኲሴ ነበር፡፡ የሚኖረው ከአስቄጥስ ራቅ ብሎ ክሊዝማ ከሚባል ቦታ ሲሆን ቦታው የራቀ ስለ ነበር ማንም ሊኖርበት የማይችል በጣም አስቸጋሪ ቦታ ነበር።

እርሱ ግን ብዙ መቅጃዎችን በአንድ ጊዜ ተሸክሞ ይሄድና በታኅሣስና በጥር ወራት የሚወርደውን ጤዛ ከዓለቶቹ ላይ በመምጠጫ /ስፖንጅ/ እያደረገ ያጠራቅምና ይጠቀማል። እዚያ በኖረበት አሥራ አምስት ዓመት ሁሉ እንዲህ እያደረገ ኖረ።

ሆኖም ግን ከቅዱሳን አባቶች ትምህርትና ከእነርሱ ከሚገኘው ምክርና በቁዔት፣ እንዲሁም ከቅዱሳት ምስጢራት ራሱን አርቆ ይኖር ነበር። ኋላ ላይ ግን “እነዚህ ምሥጢራት ምንም አይደሉም” እስኪል ድረስ ከእውነተኛ መንገድ ወጣ። በትዕቢቱ እየተነፋ ሄደና በኣቱን ትቶ ወጥቶ በግብጽ የሚዞር ሆነ ፣ ራሱንም ለሆዳምነትና ለጠጪነት አስገዛ "ወዘሰ እለ አልቦሙ ኃዳፍ ይወድቁ ከመ ቆጽል ፥ መምህራን የሌላቸው ሰዎች እንደ ቅጠል ይወድቃሉ" የተባለው ደረሰበት።

---------------------------------------------------

ቫሌንስ የሚባል አንድ ፍልስጥዔማዊ ነበር ወደ በረሃ ሄዶ ለብዙ ዓመታት ኖረ ፤ ሆኖም አጋንንት ተጫወቱበትና ቀስ በቀስ "መላእክት ተገለጡልኝ" ወደሚል ትዕቢት አደረሱት።

አንድ ቀን በጨለማ ሲሰፋበት የነበረው መርፌ አመለጠውና ወደቀበት ፣ ፈልጎ ባጣው ጊዜ ጋኔኑ መብራት አበራለት ፣ መርፌውንም አገኘው::

በዚህም የበለጠ እየታበየ በመሄድ ምሥጢራትን [ምሥጢረ ቁርባንንና ሌሎችንም] ይነቅፍና ያቃልል ጀመር። አንድ ወቅት እንግዶች ወደ ገዳሙ ሲመጡ ለበረከት ያመጡትን ምግብ ካህኑ አባት መቃርዮስ ተቀበላቸውና ለአኃው በየበኣታቸው ላከላቸው ፤ ለቫሌንስም እንዲሁ:: ቫሌንስ ግን የተላከውን ሰው ባየ ጊዜ ሰደበው ፣ መታውም ፣ "ሂድና መቃርዮስን ፣ አንተ ለእኔ በረከት የምትልክልኝ እኔ ካንተ በምን አንሳለሁና ነው? በለው" አለው።

ጋኔኑም ይኽ ሰው ሙሉ በሙሉ በእርሱ ተንኮል እንደ ተታለለ ስላወቀ ራሱን መድኃኒታችንን አስመሰለና መብራት ከያዙ ከብዙ መላእክት ጋር በመሆን መድኃኒታችን እንደ ተገለጠለት በማስመሰል ሆኖ ሌሊት በራእይ ታየው።

ከመካከላቸውም አንዱ ከሌሎቹ ፊት መጣና "ክርስቶስ ስለ ተጋድሎህና ስለ ሕይወትህ ነጻነት ወዶሃል። ስለዚህ ከበኣትህ ውጣ ፣ ሌላ ምንም ነገር ላድርግ ሳትል ፊቱን ብቻ ከርቀት ተመልከት ፣ አጎንብሰህም ስገድ ፣ ከዚያም ወደ በኣትህ ተመለስ" አለው:: እርሱም ወጣና መብራት ይዘው ብዙ ሆነው በየረድፋቸውና ደረጃቸው ሆነው ፥ ጸረ ክርስቶስ የሆነውን አስመሳይ ዲያብሎስንም ትንሽ እልፍ ብሎ አየው ፣ ወድቆም ሰገደለት።

ከዚያም በሚቀጥለው ቀን ወደ ቤተ ክርስቲያን ገብቶ በተሰበሰቡት ወንድሞች መካከል እኔ ቁርባን አያስፈልገኝም ፣ ዛሬ ሌሊት ክርስቶስን አይቸዋለሁና” እስኪል ድረስ ወደ እብደት አደረሰው::

አባቶችም የሆነውን ስለ ተገነዘቡ ያዙትና ለአንድ ዓመት ያህል አሰሩት ፣ የዕብሪተኝነቱን ደዌ በጸሎታቸውና በምክራቸው በማከምና ለዘብ ወዳለ ሕይወት በማምጣት ከሕማሙ እንዲፈወስ አደረጉት።"

---------------------------------------------------

" ወዳጆች ሆይ ፥ መንፈስን ሁሉ አትመኑ ፥ ነገር ግን መናፍስት ከእግዚአብሔር ሆነው እንደ ሆነ መርምሩ ፤ ብዙዎች ሐሰተኞች ነቢያት ወደ ዓለም ወጥተዋልና።" [፩ዮሐ.፬፥፩]


ከሐሰተኛ አጥማቂያንና የአጋንንትን ትምህርት ከሚያስተምሩ ግለሰቦች እንጠበቅ። የጸጋ ሁሉ ምንጭ ከሆነች ከቅድስት ቤተክርስቲያን ዕቅፍ አንራቅ። ዘወትር በመቅደሱ ጸንተው ከሚያገለግሉት ከእውነተኞቹ አባቶቻችን ካህናት አንለይ።

▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬


82 views16:30
ክፈት / አስተያየት ይስጡ