Get Mystery Box with random crypto!

የብዕር አሻራ

የቴሌግራም ቻናል አርማ yeberashara — የብዕር አሻራ
የቴሌግራም ቻናል አርማ yeberashara — የብዕር አሻራ
የሰርጥ አድራሻ: @yeberashara
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 1.26K
የሰርጥ መግለጫ

📚🌟እንኳን በደህና መጡ🌟📚
💮"ምርጡ ጓደኛዬ በእኔ ውስጥ ያለውን ምርጥ ማንነት እንዳወጣ የሚረዳኝ ነው" የሄንሪ ፎርድ አባባል ነው።
💮ከምርጥ ጓደኞቻችን መካከል አንዱን መፅሐፍ ብናደርገው ብዙ እናተርፍበታለን።
Cross👉 @Yeberashara_bot
ማንበብ ና መለወጥ ለምትፈልጉ፥ እዚህ ቻናል ላይ የመፅሐፍትን ሙሉ ተዋፅዖዎችን ያገኛሉ።👉 @Yeberashara

Ratings & Reviews

3.67

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

1

4 stars

1

3 stars

0

2 stars

1

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች

2022-05-12 15:19:32 << አፍቃሪን ስለማፍቀሩ ብትነቅፈው
ማፍቀሩን ይጨምራል >>


ፍቅር ቤቱን የሠራበት ልብ የታደለ ነው።
ፍቅር ከአለም ጭንቀት ሁሉ ማረፌያው ነውና ።

ፍቅር የያዘው ሰው ስለራሱ መጨነቅ ያቆማል ።

የተራራ ክምር ለአሱ እንደገለባ ብናኙ ነው። ታዲያ አፍቃሪን ስለ ማፍቀሩ ብትነቅፈው ማፍቀሩ አይጨምርበትም ትላለህ!

═════❥━━━❥═════
መልካም ነገ ይመጣል !
@Yeberashara
@SOL705
2.2K viewsedited  12:19
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-12 15:12:28 " ግን እኮ ደራሲያን ሲባሉ በአብዛኛው እንደዚያ ናቸው »


ሁልጊዜ የሚናገሩት በውስጣቸው ነው፡፡

አካባቢያቸውን ይገልፁታል እንጂ አይኖሩበትም። በማህበራዊ ሕይወታቸው ቀዝቃዛና ሙቀት የለሽ ናቸው።

እያናገራቸው ሰው መኖሩን እስከ መርሳት " እካላቸውን እያሳዩ መንፈሳቸውን ለይተው የትም ይልኩታል..

- የላኩት መንፈስ ተመልሶ እስቲዋሀዳቸው ፍፁም ብቸኛ ይሆናሉ።

ግድየለሽነት ያጠቃቸዋል።

“ታዲያ ወደው አይደለም የድርሰት ዛር ቀፎን ካላስቀረ ጠብታ ማር ስለማይሰራ ነው።


ሰንሰለት!
"ፍቅርተ"
═════❥━━━❥═════
መልካም ነገ ይመጣል !
@Yeberashara
@SOL705
1.6K viewsedited  12:12
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-04-22 18:21:43
ለክርስትና እምነት ተከታዮች በሙሉ መልካም የስቅለት በዓል እንዲሆንላችሁ እንመኛለን።

መልካም በዓል
2.3K views15:21
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-03-27 13:45:01 (የኮከብ መጠሪያ ስም ቶረስ ሴት)

የውልደት ቀን ከሚያዝያ 12 እስከ ግንቦት 12


»» ቶረስ ሴት ትልቅ ሴት ናት፣ በህይወት ጎዳናዋ የሚጋረጥባትን ማናቸውንም ችግር ለመቋቋም የሚያስችል ውስጣዊ ሀይል አላት፣ የምድር ቅመም ናት።

»» እኔ ነኝ ያለውን ወንድ የምታርበደብድ ሀይለኛ ልትሆንም ትችላለች። ግን ያለ በቂ ምክንያት አትገነፍልም፣ ትግስተኛ ናት።

»» ለሷ ሴት መሆን ማለት የግድ ተሽኮርማሚ እና ደካማ መሆን ማለት አይደለም። የቅርብ ጓደኞቿን ትልቅ ትንሽ ብላ አታንገዋልልም፣ ጓደኛዋ ከሆነ ጓደኛዋ ነው፣ በድርጊቱ ብቻ ትፈርጀዋለች። በዛው ልክ ግን አፀፋውን በጣም ትፈልጋለች።

»» ቀጥተኛ፣ ሀቀኛ፣ ታማኝና ቅናት አልባ ነች። የጄሚኒ ተፅኖ ያለባት ከሆነ ግን ትንሽ ቸኮል ትላለች። ፅድት ያለች ስትሆን፣ መጥፎ ጠረን በሀይል ይረብሻታል።

»» ተፈጥሯዊ መኣዛዎች ይመስጧታል፣ ደማቅ ቀለም ይስማማታል፣ ሰማያዊ የሆነ ነገር ሁሉ ወክክ ያደርጋታል። ሮዝና ሃምራዊም ደስ ይላታል። ሙዚቃና ኪነጥበብንም ታደንቃለች።

»» ቶረስ ሴቶች ፣ "ሹራብህ ይቧጥጣል" የሚሉ አይነት ናቸው ። አይናቸውን ጨፍነው በመዳሰስ ብቻ የጨርቅ ቀለም መለየት ይዳዳቸዋል፣ ልስልስ ልብስ ውስጣቸው ነው።

»» ስትወድም ሆነ ስትጠላ ፊት ለፊት ነው፣ ግልፅና ቀጥተኛ ነች። ይቺ ሰው ትችት ስለማትወድ ችግር ይገጥምህ ይሆናል እና በፀባይዋ ተመቻት።

»» ቶረስ ሴት የህመምና የስቃይ ስሜቶችን ለመቋቋም ያላት ችሎታ የሚያስገርምና የስኮርፒዮ ሴትን ቻይነት እንኳን የሚበልጥ ነው።

»» በአጠቃላይ ግን ቶረስ ሴት መጀመሪያ ላይ እንዳልነው ትልቅና አስተዋይ ሴት ናት።
.
.
.የቀጣይ ወር ትንበያ ይቀጥላል....
.
.
.
.
ማንኛውንም አስታየት ሆነ ጥያቄ በ @Yeberashara_bot ማድረስ ትችላላቹ


መልካም ቀን
የብዕር አሻራ
@Yeberashara
@Yeberashara
@Yeberashara
3.1K viewsedited  10:45
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-03-27 13:10:11 (የኮከብ መጠሪያ ስም ኤሪስ ሴት) የውልደት ቀን ከመጋቢት 12 እስከ ሚያዚያ 11 »» ኤሪስ ሴት የቤቷን በር ራሱ ትከፍታዋለች፣ ኮቷን ራሷ ትለብሳለች ፣ችግሯን ራሷ ትወጠዋለች፣ ያለምንም የወንድ እርዳታ። ግንባር ቀደም ለመሆን የቆረጠች ናት። »» በድርጊቷ ሁሉ መጀመሪያ ለመሆን ነው ፍላጎቷ፣ ፍቅርም ላይ እንደዛው ነች ፣ ከኤሪስ ጋ ፍቅር ስትጀምር ርምጃህ ላይ ጠንቃቃ ሁን፣ ፍቅራቹን…
1.7K views10:10
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-03-27 13:00:58
አንዳንድ ጊዜ በራሳችን ላይ ከፈጠርነው ችግር የተነሳ ለመውደቅ እየተፍገመገምን እንኳን እራሳችንን ተመልክተን ለመስተካከልም ሆነ ጥፋታችንን በማረም እርምጃ ለመውሰድ በእጅጉ እንዘገያለን። አልያም ችግሩን አምነን ለመቀበል ረጀም ጊዜ ይወስድብናል።

ይህም በፈተና ውስጥ ስንዳክር ሰበበኛ፣ አልቃሻና ለምን ባይ ያደርገናል።

መልካም ቀን
የብዕር አሻራ
@Yeberashara
@Yeberashara
@Yeberashara
1.7K viewsedited  10:00
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-03-27 12:55:50
ዛሬ በእጃችን መዳፍ ውስጥ ናት የስኬትንና የውድቀትን ካርድ ልንመዝባት እንችላለን፡፡
ዛሬ ባይሳካ ነገ ደግሞ ሌላ ቀን ነው፣ህይወት ሎተሪ ናትና ደጋግመን መሞከር ያስፈልጋል፡፡

የተሻለ ነገን ለማየት ተስፋ ትልቅ ስንቅ ነው፡፡

መልካም ቀን
የብዕር አሻራ
@Yeberashara
@Yeberashara
@Yeberashara
1.5K viewsedited  09:55
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-03-27 12:49:30
ህይወት መቆሚያ የሌለው ትምህርት ቤት ነው። ስለዚህ ፈተና የሚገጥመን በህይወት ስላለንና ከህይወት የተማርነው ትምህርት ምን ያክል እንደሆነ ይታወቅ ዘንድ ነው።

መልካም ቀን
የብዕር አሻራ
@Yeberashara
@Yeberashara
@Yeberashara
1.4K viewsedited  09:49
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-03-22 00:23:51 (የኮከብ መጠሪያ ስም ኤሪስ ሴት)

የውልደት ቀን ከመጋቢት 12 እስከ ሚያዚያ 11


»» ኤሪስ ሴት የቤቷን በር ራሱ ትከፍታዋለች፣ ኮቷን ራሷ ትለብሳለች ፣ችግሯን ራሷ ትወጠዋለች፣ ያለምንም የወንድ እርዳታ። ግንባር ቀደም ለመሆን የቆረጠች ናት።

»» በድርጊቷ ሁሉ መጀመሪያ ለመሆን ነው ፍላጎቷ፣ ፍቅርም ላይ እንደዛው ነች ፣ ከኤሪስ ጋ ፍቅር ስትጀምር ርምጃህ ላይ ጠንቃቃ ሁን፣ ፍቅራቹን መምራት ምትፈልገው እሷ ናት።

»» ከዞዳይኩ የመጀመሪያ ቤተ ባህሪ የሆነችው ኤሪስ ሴትም ከማርስ ጥንካሬና ከችግር ማጥ ተመንጥቆ የመውጣት ችሎታ ጋር የሴትነት ሚናዋን በላቀ ደረጃ ለመጫወት የምትበቃ ጎበዝ ናት።

»» በጥልቅ አፍቃሪ ስለሆነች የፍቅር ስሜቷን ህያው እስካደረክላት ድራስ ታማኝነቷ ወሰን የለውም።

»» ከልክ በላይ idealist የሆነችው ይቺ ሴት ቀኗ ብሩህና ባድናቆት የተሞላ ቢሆንም ሌሊቱን የምታሳልፈው ግን አንድንዴ በናፍቆትና በትካዜ ነው።

»» ይቺ ጎበዝ እንድታፈቅርህ ከፈለክ የምታኮራት ሆነህ መገኘት አለብህ። በፍቅር ረገድ የሷ የሆነ ነገር የሷ ብቻ ነው፣ በተለይ ወደ ፍቅረኛዋ ሲመጡባት በጣም ቁጡ ሆና ቁጭ ትላለች።

»» ፍቅረኛዋንም ተጠራጣሪ ነች፣ አንተ ግን እሷን መጠራጠር የለብህም፣ እሷም አትወድም።

»» ይቺ ሴት ጥልቅ እና ጥብቅ የፍቅር ስሜት እንዲሁም ብሩህ ተስፋን አጣምራ የያዘች ናት። እንደሞኝ እስከ ሚያስቆጥርባት ድራስ በታምር ታምናለች።

»» ከውድቀታቸውም ይማራሉ ማለት ዘበት ነው፣ ልቧ ቢፈልግም ፀባይዋ እሺ አይላትም። ግላዊ ነፃነቷን ምታስደፍርም አይደለችም።

»» ምስጢር ሲደበቃት በፍፁም አትወድም፣ ክብሯን መንካት ወይም የጓጓችለትን ነገር ማንኳሰስም ልቧን ይሰብረዋል። በአጠቃላይ ግን ኤሪስ ሴት ምርጥ ነች።
.
.የቀጣይ ወር ትንበያ ይቀጥላል.....
.
.
.
.
ለቻናላችን እድገት ሼር፣ ጆይን እንዲሁም ጓደኞቻቹን ለመጋበዝ
የብዕር አሻራ
@Yeberashara
@Yeberashara
@Yeberashara
1.7K viewsedited  21:23
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-03-20 18:42:17 ሰላም እንዴት ናችሁልኝ ወዳጆቼ?....

እንግዲህ በነገርኳችሁ መሰረት ዛሬ የመግቢያ ፕሮግራማችን ይሆን ዘን በ Astrology /ስነ ኮከብ / ቆጠራ "ተብሎ በሚታወቀው ተፈጥሮን ከሳይንስ ጋር በማዋቀር በተለያዩ እውቅ ተመራማሪያን ዘንድ ሰፊ ጥናት ተደርጎበት የውልደት ቀንን መሰረት በማድረግ ተፈጥሯዊ ባህሪያቸውን የሚናገረውን ትንበያ ይዤላችሁ ቀርቤያለሁ።
.
.
.
>>>➪ ሕብራተ-ክዋክብት በ12 ይከፈላል ።
የመጀመሪያዉ የzodiac ምልክት ኤሪስ ይባላል ።ብዙዎቹ "the infant" ይሉታል። አንዳነዶች ደግሞ ጠቦቱ እና ወጠጤው በግ ሲሉ ፀበኛ አና ተዋጊ መሆኑን ለመግለፅ ይጠቀሙታል። የኤሪስ የልደት ሰንጠረዥ ከመጋቢት 12- እስከ ሚያዝያ-11 ድረስ የሚቆይ ነው ።

>>>➪ ሌላው ከዚህ ቀጥሎ ያለው የ zodiac ምልክት ቶረስ ሲሆን አንዳንዶቹ ኮራማው "the bull " በማለት ይጠሩታል። በግትርነቱም ይታወቃል። የዚህ ኮከብ የልደት ሰንጠረዥ ከሚያዚያ 12 እስከ ግንቦት 12 ነው ።

>>>➪ ሦስተኛው የ zodiac ምልክት ጀሚናይ ሲሆን መንቲያው "the twins" በማለት ይጠሩታል። በአንድ አካል ውስጥ ሁለት ደማቅ ማንነቶች ይታዩበታል። የዚህ ኮከብ የልደት ሰንጠረዥ ከግንቦት 13 እስከ ሰኔ 13 ነው ።

>>>➪ ከዚህ ቀጥሎ ያለው zodiac ካንሠር በመባል የሚታወቅ ነው። ብዙዎች ይሄን ኮከብ ሸርጣን አሳ ይሉታል በየብስ እና በውሃ የሚኖር እንሰሳ ነወ። በዚህ እንሰሳ የሚመሰለው ኮከብ የልደት ሰንጠረዡ ከሰኔ 14 - ሐምሌ 15 የሚቆይ ነው።

>>>➪ ቀጣዩ የ zodiac ምልክት ሊዮ ነው ። ሊዮ አንበሳው በመባል ይታወቃል። የሊዮ የልደት ሰንጠረዥ ከሐምሌ 16 እስከ ነሐሴ 16 የሚዘልቅ ነው።

>>>➪ በስድስተኛው ረድፍ ያለው ቪርጎ ወይም "ድንግሉ" በመባል የሚታወቅ ሲሆን የቪርጎ የልደት ሰንጠረዡ ከነሐሴ 17 እስከ መስከረም 12 የሚቆይ ነው

ከዚህ ቀጥሎ የሚመጣው ሚዛናዊው ሊብራ ነው። ሊብራ እጅግ በሚዛናዊነቱ የሚታወቅ ነው። የልደት ሰንጠረዡም ከመስከረም 13 እስከ ጥቅምንት 12 የሚቀጥል ነው።

>>>➪ ቀጣዩ ኮከብ ስኮርፒዮ ወይም ጊንጡ በመባል ይታወቃል ። እጅግ አደገኛው ኮከብ ስኮርፒዮ ነው ።የልደት ሰንጠረዡ ከጥቅምት 13 እስከ ህዳር 12 ይቆያል።

>>>➪ ሳጁታሪየስ የተባለው ግማሽ ፈረስ ግማሽ ሠው የሆነው ይህ ኮከብ ከወረሃ ህዳር ከቀን 13 ጀምሮ እስከ ታህሳስ 12 የሚቆይ ነው ።

>>>➪ በመቀጠል የሚመጣው የደጋው ፍየል ካፕሪኮርን ነው ይህ ኮከብ የ zodiac ቆይታው ከታህሳስ 13 እስከ ጥር 11 የሚቆይ ነው ።

>>>➪ አኳሪየስ ከጥር 12 እስከ የካቲት 11 የሚቆይ የ zodiac ምልክት ነው ። ይህ ኮከብ የሀገራችን ኢትዮጵያ..እስራኤል..ኢራን ጭምር ኮከብ ነው ። ያለንበትም ዘመን የአኳሪየስ ዘመን ነው ።

>>>➪ ተከታዩ እና የመጨረሻው የ zodiac ምልክት ፓይሰስ ይባላል ። ፓይሰስ በተለያየ ጎን ሆነው የቆሙ ሁለት አሳዎችን ምልክቱ አድርጎ የሚታይ ነው። ኤሪስ በውልደት ሲመሠል ፓይሰስ በሞት ይመሠላል። ክርስቶስ ጨምሮ በርካታ መንፈሳዊ ሰዎች በፓይሰስ ወር ተወልደዋል ። የፓይሰስ የልደት ሰንጠረዥ ቆይታ ከየካቲት 12 እስከ መጋቢት 11 ነው።
.
.
.
.
የዞዳይክ ትንበያው ይቀጥላል...፣
.
.
.
.
.
.
.
.
ማንኛውንም አስታየት ሆነ ጥያቄ በ @Yeberashara_bot ልታደርሱን ትችላላችሁ


ለቻናላችን እድገት ሼር፣ ጆይን እንዲሁም ጓደኞቻችሁን ለመጋበዝ
የብዕር አሻራ
@Yeberashara
@Yeberashara
@Yeberashara
1.4K viewsedited  15:42
ክፈት / አስተያየት ይስጡ