Get Mystery Box with random crypto!

' ዓምደ - ሀገር ሼህ ዓሊ ጎንደር ' የተሰኘው የኸድር ታጁ መጽሐፍ ሽያጭ ላይ ነን :: የኢት | ጦማር መጻሕፍት አቅራቢ📚📖📚

" ዓምደ - ሀገር ሼህ ዓሊ ጎንደር " የተሰኘው የኸድር ታጁ መጽሐፍ ሽያጭ ላይ ነን ::

የኢትዮጵያን ታሪክ የጻፉ ሊህቃን፣ ከጎንደሮች ክፍለ-ዘመን(1558-1769) የቀጠለውን እና እስከ 1855 ዓ.ል የቆየውን ጊዜ ‹ዘመነ-መሣፍንት(1769-1855)› ይሉታል፡፡ ‹ዘመነ-የጁ›ም ይባላል፡፡

ሼህ ዓሊ-ጎንደር - ከ18ኛው አጋማሽ እስከ 19ኛው ክ/ዘመን አጋማሽ ነበር የኖሩ፡፡ ወሎ ተወልደው፣ ዓለምን ዙረው፣ በጎንደር ታጠሩ፡፡ በመማር ማስተማር፣ በሥነ-ጽሁፍ፣ በኪነ-ጥበብ፣ በንግድ፣ በሥነ-ምህንድስና፣ በፍልስፍና፣ በምንፍሥና፣ በሥነ-ምድር እና በሥነ-ተፈጥሮ ምርምር፣ በውትድርና እና በአስተዳደር፣ በሌሎች መስኮች ተጨባጭ ዓለማቀፋዊና ሀገራቀፋዊ ትሩፋት አበርክተዋል፡፡ መሠረታቸው ጠብቆ፣ ልህቀታቸው ርቆ ከ፬፻(አራት-መቶ) በላይ የዓለም መዲናዎችን ጎብኝተዋል፡፡ ከሱዳን፣ ከግብጽ፣ ከቱርክ ነገሥታት ጋር ግልጽ(ነጻ) ግንኙነት ፈጥረዋል፡፡ የእንግሊዝን ንግሥት፣ የህንድን መንግሥት፣ የሱዳንን ምስለኔ በአማካሪነት አግዘዋል፡፡ ፋናቸውን በከፊል የኤሮጳና የኤዥያ አህጉራዊ ግዛቶች አዝልቀው አነጥበዋል፡፡

ለኢትዮጵያ መሣፍንትና ንጉሦች ሥነ-መንግሥታዊ ትምህርት በመስጠት፣ ገንቢ ተሞክሮና ምክር፣ ድልብ ዕውቀትና ልምድ በማካፈል ክህሎታትን አበልጽገዋል፡፡ የእርስ-በርስ ግጭቶችን በዕርቅ በማቃለል ደሚቅ አሻራ አሳርፈዋል፡፡ በአጤ ዮሐንስ-፫ኛ፣ በእቴጌ መነን፣ በራስ ዓሊ(ትንሹ/አስጘር)፣ በደጃች ጎሹ እና በአጤ ቴወድሮስ ላይ በጎ አበርክቶ አትመዋል፡፡ በሐበሻ ክርስቲያኖች መካከል “የጸጋ ልጅ”፣ “ቅባት” እና “ተዋህዶ” ተሰኝተው የተከሰቱ ልዩነቶች የእርስ-በርስ እልቂት ከማስከተላቸው በፊት፣ ጣልቃ በመግባት አሸማግለዋል፡፡ የእሥልምና ሊቃውንትን ሕብረትና አስተሳሰብ በአግራሞታዊ የተሀድሶ ሥርዓት አበልጽገዋል፡፡
--------------------------------
#ጦማር_መጻሕፍት_አቅራቢ መጽሐፉን ከልዩ ቅናሽ ጋር እርስዎ ያሉበት ቦታ ድረስ ለማቅረብ ዝግጁ ነው። ለማድረሻም ተጨማሪ ክፍያ አንጠይቅም።
ከኢትዮጵያ ውጪ በየትኛውም ክፍለ ዓለም ላሉም በፖስታ ቤት በኩል እንልካለን።

ለማዘዝ #ይደውሉ_ 0985406069
ወይም በ https://t.me/Tomarbooks ያናግሩን።

~ በዚህ ሊንክ https://t.me/Tomarbooksdelivery የቴሌግራም ቻናላችንንም ይቀላቀሉ።
።።።።።።።።።።። መጻሕፍትን ከወዳጆቻቸው ጋር እናገናኛለን ።።።።።።።።።።።