Get Mystery Box with random crypto!

. ▬▬▬▬▬▬ #ፋኖነት ውድ ወገኖቼ፣ በ428 ገጾች፣ በ6 ክፍሎች፣ በ26 ምዕራፎች የተዋቀረው | ጦማር መጻሕፍት አቅራቢ📚📖📚

. ▬▬▬▬▬▬ #ፋኖነት

ውድ ወገኖቼ፣ በ428 ገጾች፣ በ6 ክፍሎች፣ በ26 ምዕራፎች የተዋቀረው እና “ፋኖነት በምስጢራዊው ጉባኤ” የተሰኘው መጽሐፌ እንደ እግዚሐብሄር ፈቃድ ተጀምሮ እንደ እርሱ ቸርነት ከቀናት በፊት ለንባብ በቅቷል፡፡ ከራሱ በላይ ስለወገንና ሀገሩ ስለሚጨነቀው፣ የሀገር ፍቅር ስሜት ውስጡ ስለሚንቦገቦገው፣ በንዋይ ጋጋታ ለማይለወጠው፣ በጭብጨባ ብዛት ልቡ ለማይቀልጠው፣ በቃላት ጋጋታ ለማይበለጠው ፋኖ ብዕሬን እንዳነሳ፣ ለሰፊው ህዝብና ለሚኖሩለት ዓላማ ታማኝ ሆነው ላለፉ፣ እየኖሩ ላሉና ለሚኖሩ ወገኖቸ መታሰቢያነት ይሆን ዘንድ “ፋኖነት በምስጢራዊው ጉባኤ” በሚል የውስጤን ሃሳብ እንዳጋራ የፈቀደልኝ አምላክ ክብሩን ይውሰድ፡፡

በፋኖነት መጽሐፍ፣ በተለይም የአማራ ህዝብ ከትናንት እስከ ዛሬ የተደቀነበትን ብርቱ ፈተና፣ ከልጅ እስከ አዋቂ ለሀገር ኖሮ ለሀገር መሞትን፤ የባንዳነት፣ ሆዳደርነት እና ዓላማ ቢስ ጉዞ መጨረሻ እና የትውልዱን አደራ ለማመለከት ተሞክሯል፡፡ ይህ እንዲሆን ላበረታታችሁኝ ሀገር ውስጥም ሆነ በውጭ ሀገር ለምትኖሩ ወገኖቼ በታላቅ ትህትና ምስጋናየን አቀርባለሁ፡፡

ጌትነት ይርሳው
ሀገራችን ኢትዮጵያ ሰላም ትሆንልን ዘንድ እመኛለሁ!
ፋኖነት በምስጢራዊው ጉባኤ! መልካም ንባብ!
--------------------------------
#ጦማር_መጻሕፍት_አቅራቢ መጽሐፉን ከልዩ ቅናሽ ጋር እርስዎ ያሉበት ቦታ ድረስ ለማቅረብ ዝግጁ ነው። ለማድረሻም ተጨማሪ ክፍያ አንጠይቅም።
ከኢትዮጵያ ውጪ በየትኛውም ክፍለ ዓለም ላሉም በፖስታ ቤት በኩል እንልካለን።

ለማዘዝ #ይደውሉ_ 0985406069
ወይም በ https://t.me/Tomarbooks ያናግሩን።

~ በዚህ ሊንክ https://t.me/Tomarbooksdelivery የቴሌግራም ቻናላችንንም ይቀላቀሉ።
።።።።።።።።።።። መጻሕፍትን ከወዳጆቻቸው ጋር እናገናኛለን ።።።።።።።።።።።