Get Mystery Box with random crypto!

🇹 🇴 🇲 t҈ u҈ b҈ e҈ 

የቴሌግራም ቻናል አርማ tom_abe — 🇹 🇴 🇲 t҈ u҈ b҈ e҈ 
የቴሌግራም ቻናል አርማ tom_abe — 🇹 🇴 🇲 t҈ u҈ b҈ e҈ 
የሰርጥ አድራሻ: @tom_abe
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 2.34K
የሰርጥ መግለጫ

🔰Welcome To Tom Abe TG Channel.🔰
We Sharing All types of information, refer n earning apps/software...if u like to than join our channel
➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖
© 2022
➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖

💪Powered By @tom_abe

Ratings & Reviews

3.00

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

1

4 stars

0

3 stars

0

2 stars

0

1 stars

1


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 3

2022-07-07 13:43:49
"ሰው እየሞተ የሞተበት ቦታ ችግኝ እንተክላለን ቢያንስ አስከሬኑ ጥላ እንዲኖረው፡፡"
ይህን የተናገሩት የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚንስትር አብይ አህመድ ናቸው!


@tom_abe
166 viewsτємєѕgєи αϐєϐє τοм, edited  10:43
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-06 20:05:14
"ሰዎች አንዳንድ ጊዜ ስለአውሬዎች ጭካኔ ይናገራሉ፤ ነገር ግን ይሄ መናገር ለማይችሉት አውሬዎች ሚዛናዊ ያልሆነ ዘለፋ ነው። አውሬዎች ልክ እንደሰው በጣም በረቀቀና ጣፋጭ ስሜትን በሚያሳይ ሁኔታ በመጨከን በፍፁም የሰውን ያህል ጨካኝ መሆን አይችሉም። ነብር ያደነውን እንሰሳ ይቦጫጭቅና ያኝከዋል…ሊያደርግ የሚችለው ይሄን ብቻ ነው። ማድረግ ቢችል እንኳ፣ የሰዎችን ጆሮዎች አጥር ላይ በሚስማር መትቶ ለማሳደር በፍፁም አያስብም።"

•••

"ካራማዞቭ" በፊዮዶር ዶስቶቭስኪ፤ ትርጉም በመክብብ አበበ (268)

@tom_abe
239 viewsτємєѕgєи αϐєϐє τοм, edited  17:05
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-05 20:52:12
ሎሚ ለብ ባለ ውሃ ውስጥ ጨምሮ መጠቀም በርካታ የጤና ጥቅሞች እንዳሉት ይነገራል።

በተለይም በባዶ ሆድ ለብ ያለ ውሃ ውስጥ ሎሚ ጨምቆ ዘወትር መጠጣት ÷ ጉበትን ከመርዛማ ነገሮች ያፀዳል፣ በውሃው ውስጥ የሎሚውን ልጣጭ በመጨመር የሚጠጡ ከሆነ ደግሞ የደረጃ 2 የጉበት ፀር የሆነውን መርዝ ማስወገድ ያስችላል።

ከዚህ ባለፈም ጉበት ሐሞት እንዲያመነጭ በማበረታታት ቅባት የበዛባቸውን ምግቦችን ሰውነት እንዲፈጭ ይረዳል፣ ሎሚ ከፍተኛ አንቲ ኦክሲደንት ባህሪ ስላለው ሕዋሳት እንዳይጎዱ ይጠብቃቸዋል፣ በሎሚ ውስጥ ያለው አንቲ- ኦክሲደንት እና ፌቶኬሚካልስ የጉበት ሕዋሳት እንዲታደሱ ይረዳል።
በተጨማሪም በሎሚ ውስጥ ያለው ሲትሪክ አሲድ የምግብ ስርዓተ ልመትን ያፋጥናል እንዲሁም የኩላሊት ጠጠርን ያሟሟል።

ሎሚ ከሰውነት ውጭ አሲድ ሲሆን በሰውነት ውስጥ አልካላይን በመሆኑ በሰውነት ውስጥ ያለውን የፒ ኤች ደረጃ ሚዛናዊ እንዲሆን ይረዳል፣ በሽታን ይከላከላል፣ በሎሚ ውስጥ ያለው ከፍተኛ የቫይታሚን ሲ ንጥረ ነገር ጠንካራ የተፈጥሮ በሽታ የመከላከል አቅም እንዲኖር ያስችላል።

ሎሚ የደም ቅባትን በመሰባበር በርካታ ሰዎች የሚያጋጥማቸውን የሀሞት ድንጋይ በሰውነት ውስጥ እንዳይፈጥር ያግዛል፣ የዩሪክ አሲድ መጠንን በመቀነስ ሰዎች በሪህ እና በአጥንት አንጓ ብግነት እንዳይጠቁ ያግዛል።

እንዲሁም ራስን ከአንዳንድ የካንስር በሽታ አይነቶች ለመከላከል እንደሚረዳ የሃኪም ቤት መረጃ ያመላክታል፡፡

ምንጭ: ፋና

@tom_abe
312 viewsτємєѕgєи αϐєϐє τοм, edited  17:52
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-04 13:20:05
10 በርካታ ቋንቋ ያላቸው አገራት

በዓለማችን ከሰባት ሺሕ በላይ ቋንቋዎች እንዳሉ ጥናቶች ይጠቅሳሉ። ቋንቋ ካለው የመወለድ፣ የማደግ እና የመሞት ባህሪ የተነሳም ቁጥራቸው በየጊዜው እንደሚጨምር ይታመናል። በዛው መጠን ግን ከዘመናዊነት መምጣትና መስፋፋት ጋር ተያይዞ ከእነዚህ ቋንቋዎች ውስጥ አንድ ሦስተኛ የሚሆኑት የመጥፋት አደጋ እንደተጋረጠባቸው የቋንቋ ዘርፍ ጥናት ባለሞያዎች በተለያየ ጊዜ ሲናገሩ ይሰማል።

@tom_abe
358 viewsτємєѕgєи αϐєϐє τοм, edited  10:20
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-04 13:17:45 ጥቂት ውሳኔ ብዙውን ለውጥ ያመጣል!

ህይወታችን ላይ ትልቁን ለውጥ የሚፈጥረው ትልቁ ውሳኔ አይደለም! እያንዳንዷ በየደቂቃው የምንወስናትና የምናከናውናት ጥቃቅኗ ውሳኔያችንና ተግባራችን ነው እንጂ!

@tom_abe
342 viewsτємєѕgєи αϐєϐє τοм, 10:17
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-02 18:06:11 ሰላም ሰላም ውድ የ Tom Tube ተከታታዮች ምርጥ ምርጥ ቦቶችን ዛሬ እንጦቁማቹ።

@ChelpBot -ይሄ ቦት ለቻናላቹህ ጠቃሚ ነው የፈለጋቹን ይሰራል።

@getmediabot - ከ #Facebook #YouTube #Instagram ላይ ቪድዮ ማውርድ ከፈለጋቹ ይህን ቦት ተጠቀሙ። ከናንተ ሚጠበቀው የቪዲዮውን ሊንክ ለቦቱ መላክ ብቻ ነው።

@apkdl_bot - ፕሌይስቶር ላይ የሚገኙ አፓችን እና ፕሌይስቶር አልሰራ ላላችሁ እሂን ቦት በመጠቀም እዚሁ ቴሌግራም ላይ ማንኛውንም አፕ ማውረድ ትችላላችሁ

@ThemerBot - ይህ ቦት የፈለጋቹትን የ ቴሌግራም Themer መስራት የሚያስችል ነው።

@PhotosetterBot - ይሄ ቦት እንደ scanner ነው Text picture ወደ Text ቀይሮ ይልካል።

መረጃዎችን ለወዳጅዎ ያጋሩ።

@tom_abe
455 viewsτємєѕgєи αϐєϐє τοм, 15:06
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-02 17:53:30 10 ዋና ዋና የእንቁላል ጥቅሞች

እንቁላል ለሰው ልጅ በጣም ተስማሚ ከሆኑ የምግብ አይነቶች ውስጥ ዋነኛዉ ነው ። ሰዎች በቀን 3 እንቁላል እንዲመገቡ ይመከራል። እንቁላል ለአዘገጃጀት ቀላልና ከማንኛውም ምግብ ጋር አብሮ ሊዘጋጅ የሚችል ነው ። በጣእሙም ከማንኛውም ምግብ ጋር ሊወዳደር የሚችል ነው ።

እንቁላል ለሰው ልጅ ብዙ ጥቅም አለው። 10 የእንቁላል ዋና ዋና ጥቅሞች እንደሚከተለው ቀርበዋል ።

ለወዳጅዎ ያጋሩ። እንቁላልን አዘውትረው ይመገቡ ።

1.እንቁላል የአልሚ ምግብ ምንጭ ነው

እንቁላል የሰው ልጅ የሚያስፈልገውን አልሚ ምግብ ሙሉ በሙሉ ሊባል በሚችል ደረጃ ይዟል።

2.እንቁላል ጤናማ የኮሌስትሮል ምንጭ ነው

እንቁላል በውስጡ የበዛ ኮሌስትሮል የያዘ ቢሆንም በደም ውስጥ የሚኖረውን የኮሌስትሮል መጠን ለአብዛኛው ሰው አይጨምርም።

3.እንቁላል የልብ ህመምንና ስትሮክን ይከላከላል

HDL(High Density Lipo Protein) የተባለውን የኮሌስትሮል መጠን በመጨመር ሰዎችን ከልብ በሽታ ይከላከላል ። ጥናቶች እንደሚያመለክቱት 2 እንቁላል በየቀኑ ለ6 ሳምንታት መጠቀም የHDL መጠንን በ10% ይጨምራል ።

4. እንቁላል የኮሊን(Choline)ንጥረ ምግብ ምንጭ ነው

ኮሊን የሴል ሜምብሬን ለመስራት የሚያገለግል ንጥረ ነገር ነው።

ኮሊን ከቪ ቫይታሚን ምንጭ ውስጥ ይመደባል።ከእንቁላል ውጭ በሌሎች የምግብ አይነቶች ውስጥ በብዛት አይገኝም።

5.እንቁላል የአይን ህመምን ይከላከላል

እንቁላል Lutein እና Zeaxanthin የተባሉ ንጥረ ነገሮችን ይዟል ። በተለይም የእንቁላል አስኳል በሁለቱ ንጥረ ነገሮች የበለፀገ ነው። ለእንቁላልን መጠቀም ከአይን ህመም እራሳችንን ለመጠበቅ ያግዘናል ።

6.እንቁላል የቫይታሚን ኤ ምንጭ ነው

በአለም ላይ ለአይነ መታወር ከሚዳርጉ ዋነኛ ምክንያቶች አንዱ የቫይታሚን ኤ እጥረት ነው ። እንቁላል በበቂ መጠን የቫይታሚን ኤ ምንጭ ነው ።

7.እንቁላል የኦሜጋ 3 ፋቲ አሲድ ምንጭ ነው

ኦሜጋ 3 ፋቲ አሲድ በደም ውስጥ የሚገኝ Triglyrcerides የተባለ ንጥረነገር በመቀነስ የልብ ህመምን ይከላከላል ።

8. እንቁላል የፕሮቲን ምንጭ ነው

የሰው ልጅ የተሰራው ገንቢ ምግብ (ፕሮቲን ) ከተባለ ነገር ነው ። እንቁላል በውስጡ ለሰው ልጅ አስፈላጊ የተባሉትን አሚኖ አሲድ በሙሉ የያዘ ነው ። ፕሮቲን የሰውን ሴልና ቲሹን ለመስራት ይጠቅማል።

9.እንቁላል ክብደት ለመቀነስ ይጠቅማል

እንቁላል በትንሹ በመመገብ ከሚያጠግቡን ምግቦች መካከል አንዱ ነው። ይህም ክብደት ለመቀነስ ይጠቁማል።

10.እንቁላል የአጥንትንና ፀጉርን ጤና ለመጠበቅ ይጠቀማል


ለወዳጅዎ ያጋሩ። እንቁላልን አዘውትረው ይመገቡ ምንጭ- healthline

@tom_abe
414 viewsτємєѕgєи αϐєϐє τοм, 14:53
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-01 21:10:23
#ስጋቶች የሚመጡት የምናደርገውን ካለማወቅ የተነሳ ነው። ይለናል ዋርን ቡፌት

የምናደርገውን በደንብና ጥርት ባለመልኩ እንወቅ... ማወቃችን የምንሄድበት መንገድን ግራ ከመጋባት ይቀንሳል። ስጋትንም ይቀንሳል... ሲቀጥልም ስጋትን የመቀበል ትከሻ ይኖረናል።
የማናውቃቸው ብዙ ነገሮች አሉ... ግን ቢያንስ የምናደርገውን እንወቅ... እንደመጣልንና በዘፈቀደ አናድርግ።
የሆነ ክፍት መንገድ ስለተገኘ አንግባ...
የሆነ ብር እጃችን ላይ ስላለ ግዴታ ወደስራ መዋል አለበት አንበል
የምናደርገው ምን እንደሆነ እንረዳ... #በችኮላ_አድርገን_ምን_እንደምናደርግ_ሳናውቅ_የተደረገ_ነገር_አንዳችም_ጠብ_አይልም።

መልካም ምሽት

@tom_abe
477 viewsτємєѕgєи αϐєϐє τοм, edited  18:10
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-01 19:58:50 ትዕግስተኛ ሰው ውሃን በወንፊት መያዝ ይችላል ፡፡ ዋናው ነገር ውሃው ወደ በረዶ እሲኪቀየር መታገሱ ላይ ነው ፡፡

አንተም ህይወቴ አሁን ተቦክቶ ፤ አሁን ኩፍ ብሎ ፤ አሁን ተጋግር ፤ አሁን ካልቆረስኩት ሙቼ እገኛለው አትበል ፡፡ ሁሉም ነገር የሂደትና የትዕግስት (የመጠበቅ) ጉዳይ ነው ፡፡

ከእንቁላል ጫጬት እንደሚገኝ የታወቀ ነው ፡፡ ነገር ግን ጫጬቱ እንቁላሉን ሰብሮ ሳይወጣ ተቻኩለክ አንተ ብትሰብረው የምታገኘው ሁለት እግር ያለው ጫጬት ሳይሆን ፈሰሽ አስኳልን ነው ፡፡

የአብዛኞቻችን ችግር ምን እንደሆነ ታውቃለክ ወዳጄ ? መጠበቅ ሚባል ነገር አንወድም! አዎ ትዕግስት ብሎ ነገር አልፈጠረብንም ፡፡ ለማንኛውም መልካምና ታጋሽ ሁናችሁ ዋሉ ፡፡ የረጋ ወተት ቅቤ ይወጠዋል ይላሉ አበው ሲተርቱ እኔም ቀበል አድርጌ ረጋ እንበል እላለሁ ፡፡

በመረጋጋት ውስጥ ልምድ መውሰድ ፣ በመረጋጋት ውስጥ ያሉንን አማራጮች ማየት ፣ በመረጋጋት ውስጥ መብሰል አለና እንረጋጋ እላለሁ ፡፡

@tom_be
395 viewsτємєѕgєи αϐєϐє τοм, 16:58
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-01 19:57:16 ትዕግስተኛ ሰው ውሃን በወንፊት መያዝ ይችላል ፡፡ ዋናው ነገር ውሃው ወደ በረዶ እሲኪቀየር መታገሱ ላይ ነው ፡፡

አንተም ህይወቴ አሁን ተቦክቶ ፤ አሁን ኩፍ ብሎ ፤ አሁን ተጋግር ፤ አሁን ካልቆረስኩት ሙቼ እገኛለው አትበል ፡፡ ሁሉም ነገር የሂደትና የትዕግስት (የመጠበቅ) ጉዳይ ነው ፡፡

ከእንቁላል ጫጬት እንደሚገኝ የታወቀ ነው ፡፡ ነገር ግን ጫጬቱ እንቁላሉን ሰብሮ ሳይወጣ ተቻኩለክ አንተ ብትሰብረው የምታገኘው ሁለት እግር ያለው ጫጬት ሳይሆን ፈሰሽ አስኳልን ነው ፡፡

የአብዛኞቻችን ችግር ምን እንደሆነ ታውቃለክ ወዳጄ ? መጠበቅ ሚባል ነገር አንወድም! አዎ ትዕግስት ብሎ ነገር አልፈጠረብንም ፡፡ ለማንኛውም መልካምና ታጋሽ ሁናችሁ ዋሉ ፡፡ የረጋ ወተት ቅቤ ይወጠዋል ይላሉ አበው ሲተርቱ እኔም ቀበል አድርጌ ረጋ እንበል እላለሁ ፡፡

በመረጋጋት ውስጥ ልምድ መውሰድ ፣ በመረጋጋት ውስጥ ያሉንን አማራጮች ማየት ፣ በመረጋጋት ውስጥ መብሰል አለና እንረጋጋ እላለሁ ፡፡

@tom_abe
376 viewsτємєѕgєи αϐєϐє τοм, 16:57
ክፈት / አስተያየት ይስጡ