Get Mystery Box with random crypto!

🇹 🇴 🇲 t҈ u҈ b҈ e҈ 

የቴሌግራም ቻናል አርማ tom_abe — 🇹 🇴 🇲 t҈ u҈ b҈ e҈ 
የቴሌግራም ቻናል አርማ tom_abe — 🇹 🇴 🇲 t҈ u҈ b҈ e҈ 
የሰርጥ አድራሻ: @tom_abe
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 2.34K
የሰርጥ መግለጫ

🔰Welcome To Tom Abe TG Channel.🔰
We Sharing All types of information, refer n earning apps/software...if u like to than join our channel
➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖
© 2022
➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖

💪Powered By @tom_abe

Ratings & Reviews

3.00

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

1

4 stars

0

3 stars

0

2 stars

0

1 stars

1


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 2

2022-08-01 19:20:13 ትላንት አልፏል!

ፈጣሪ ጊዜን ከፈጠረበት አንዱ ምክንያት 'ድሮ' የሚባል ላጠፋሀቸው ጥፋቶች ሁሉ መቀበሪያ ጉድጓድ ለማዘጋጀት ነው። ታዲያ እዛ የመቃብር ስፍራ ምን ታረጋለህ ወዳጄ? ለምን ስለትላንት እያሰብክ ራስህን ታስጨንቃለህ?! ወዳጄ አሁንን መኖር ጀምር! አጠገብህ ያለውን በረከት እይና ተመስገን በል፤ ተደሰት!

ውብ ምሽት ይሁንላችሁ

@tom_abe
795 viewsτємєѕgєи αϐєϐє τοм, 16:20
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-01 19:19:41 ፈጣሪ መቼም አይተወንም!


ብዙ ሰዎች ቃል ሊገቡልን ይችላሉ ! አንተ ብቻ ተመረቅ እንጂ በበነጋታው ነው ስራ የማስገባህ ከሚለው አንስቶ እስከ ትልልቅ ነገሮች እኔ አደርግልሀለው፣ አሳካልሀለው፣ አስተካክልካለው እያሉ ብዙ ተስፋ ይሰጡሀል ከዚያ ግን በጣም በፈለግካቸውና ቃል የገቡልህ ሰዐት በደረሰ ግዜ ከጎንህ የሉም ያኔ ምን ይሰማሀል? አምነትህን ሙሉ ለሙሉ የጣልክባቸውን ሰዎች ምንም ሊያረጉልህ እንደማይችሉ ስታውቅ ተስፋ ትቆርጣለህ? ሁሉን ነገር ታቆማለህ? በፍፁም እንዳታደርገው ! የሰው ልጅ ትልቁ ተስፋ ፈጣሪው ብቻ ነው ስለዚህ ቃል የገቡልህ ያመንካቸው እነሱን ተንተርሰህ መንገድ የጀመርክባቸው ድንገት ቢሸሹህ የሚያስጨርስህ እና የሚያሳካልህ የሚያግዝህ ፈጣሪ እንዳለህ አስታውስ !

@tom_abe
688 viewsτємєѕgєи αϐєϐє τοм, 16:19
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-30 20:30:43 ብቻህን ተደብቀህ አትታገል !

ምንም አይነት ስሜት ለይ ብትሆን ቢከፋህ ቢደብርህ ያለመቻል የመሸነፍ ስሜት ቢሰማህ በርህን ዘግተህ አትተኛ ፣ አትደበቅ ፣ ብቻህን ቁጭ ብለህ አትከፋ! ተነሳ ፣ ተታጠብ ፣ ልብስህን ቀይር ራስህን አስተካክል ከዛም ውጣ አካባቢህን በዙሪያህ ያሉትን ሁሉ ተመልከት እንቅስቃሴ አድርግ ሮጥ ሮጥ በል ከሠዎች ጋር ተወያይ ከዚያ ያ የነበረክ ስሜት ሁሉ ከላይህ ላይ እርግፍ ብሎ ሲለቅህ ታየዋለህ በአዲስ ሀሳብ በተሻለ ማንነት ትሞላለህ!

@tom_abe
667 viewsτємєѕgєи αϐєϐє τοм, 17:30
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-25 20:28:30 አስደናቂ እውነታዎች – Amazing Facts

አይጥና ፈረስ አያስመልሳቸውም

የሲጋራ መለኮሻ (ላይተር) ከክብሪት ቀድሞ ነው የተፈጠረው

አዞ ምላሱን ማውጣትም ሆነ ምግብ ማኘክ አይችልም

በሰውነታችን ውስጥ ካሉት አተሞች ውስጥ 98 በመቶዎቹ በየአመቱ ራሳቸውን ይተካሉ

ድምፅ ከአየር ይልቅ በብረት ውስጥ በ15 እጥፍ ይጓዛል

ጎሪላዎች በቀን ለ14 ሰዓታት ይተኛሉ

የአንድ ሰው ልብ በቀን 100ሺህ ጊዜ ይመታል

ወሲብን ለመደሰቻ የሚጠቀሙበት የሰው ልጅና ዶልፊን ብቻ ናቸው

የእጅ ጥፍራችን ከእግር ጥፍራችን በአራት እጥፍ ያድጋል

ልክ እንደ እጅ አሻራ ሁሉ የእያንዳንዳችን የምላስ አሻራ የተለያየ ነው ልክ እንደ እጅ አሻራ ሁሉ የእያንዳንዳችን የምላስ አሻራ የተለያየ ነው

@tom_abe
849 viewsτємєѕgєи αϐєϐє τοм, edited  17:28
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-25 10:06:52 ከሁሉ ፍቅር ይቀድማል!

ደስተኛ መሆን ትፈልጋለህ? ፍቅርን ፍጠር አካባቢህን በሙሉ በፍቅር ሙላው ለምታገኘው ሰው ሁሉ ሰላምን ስጥ ከልብህ መውደድን ተማር ! ከልብህ መስጠትን ጀምር ! ምንም ሳትጠብቅ ሁኔታዎችን ሳታይ ካንተ የሚጠበቀውን ብቻ ፈፅም ያኔ ህይወት መልካም ነገሯን በሙሉ ወደ አንተ ትገለብጣለች ደስታህ ወደር አይኖረውም ፤ ፍርሀት ጥርግ ብሎ ከውስጥህ ይጠፋል ፤ እመነኝ በፍቅር ከሆነ ሁሉን ነገር ታሸንፋለህ!

ደስ የሚል ሰኞ ተመኘን

@tom_abe
735 viewsτємєѕgєи αϐєϐє τοм, 07:06
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-23 12:46:44
ይህን ቦት በመጠቀም በ እንግሊዘኛ ፊደላት የተፃፈ አማረኛ መልዕክትን ወደ አማረኛ ፊደላት መቀየር ትችላላችሁ :
- ያለ አማርኛ key board አማርኛ ይፃፉ።
- ለምሳሌ:- Selam New? ሰላም ነዉ?

ፊደላቶችን ብቻ ሳይሆን ቁጥሮችንም ወደ ግእዝ ቁጥር ይቀይራል።
ለምሳሌ:-
- 2 ፪
_ 2013 ፳፻፲፫
- 2021 ፳፻፳፩

ስርአተ ነጥቦችንም ወደ አማረኛ አቻቸዉ ይቀይራል።
ለምሳሌ:-
. ወደ ።
, ወደ ፣
; ወደ ፤

የቦቱ ሊንክ
@hahu_robot
@hahu_robot
@hahu_robot

Share And Support Us.

@tom_abe
770 viewsτємєѕgєи αϐєϐє τοм, edited  09:46
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-21 20:58:59 ፌስቡክዎ መጠለፉን ለማወቅና ከጠለፋ እራስዎን ያውጡ!
1. Setting and Privacy ይግቡ
2. Setting ይንኩ
3. Security
4. Security and login
5. Where you are logged in ከዚህ ውስጥ በምን ሞባይል ወይም ኮምፒውተር፣ የት ቦታና ሀገር፣ በምን ብራውዘር፣ ወይም አፕልኬሽን፣ መቼ ቀን ከዚህ በፊት እንደከፈታችሁት ያሳያችኋል። ነገር ግን ደግሞ Active now በሚል በአረንጓዴ የተጻፈው አሁን የከፈታችሁበትን ይነግራችኋል። ከዚህ በታች የተዘረዘረውን Session ስትመለከቱ የናንተ ካልሆነና የሚያጠራጥር ከሆነ ከታች ላይ Logout All Sessions የሚለውን በመጫን Logout የሚለውን በመጫን እራስዎን ከጠላፋ ማውጣት ይኖርብዎታል።
የተጠለፈ መሆኑ ከተጠራጥሩ በፍጥነት Password መቀየር ይኖርብዎታል።
ከአምስተኛው ተራ ቁጥር በመቀጠል ካለው Step Where you are logged in በታች Login ከሚለው በታች Change password የሚለውን በመጫን current password እና New password በማስገባት Save Changes የሚለውን ይጫኑ።

በተጨማሪም Two factor Authentication On ቢያደርጉት ጥሩ ነው። ይህ On መሆኑ ምንም እንኳን የፊስቡክ አካውንትዎን Password ሰው ቢያውቅብዎ በስልካችሁ የሚላከውን Security code እስካላወቁ ድረስ መክፈትና መጠቀም አይችሉም። ስለዚህ On በማድረግ እንድትጠቀሙ እመክራለሁ። በፈለጋችሁ ሰአት Off ማድረግ የምትችሁ ይሆናል!

እራስዎን ከጠላፊዎች ይከላከሉ!

@tom_abe
684 viewsτємєѕgєи αϐєϐє τοм, 17:58
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-21 12:37:31 ቫይረስ /Virus/  የኮምፒውተር ቫይረስ እራሱን ሌሎች ፋይሎች ላይ በማጣበቅ የሚያባዛ እና ተላላፊ ማልዌር ነው፡፡ ቫይረስ እራሱን ከተለያዩ ሶፍትዌሮች ጋር ባማጠባቅ እንደ ወርድ ዶኩሜንት ሊሆን ይችላል እኛ ፐሮገራሞቹን ስንከፍት እሱም አብሮ በመቀስቀስ የሚራባ ነው፡፡ በተጨማሪም ኔትዎርክ እና አንተርኔትንም ጨምሮ ማለት ነው፤ በፈላሽ ዲስክ፤ሜሞሪ ካርደ እና ሲዲዎችን በመጠቀም ይተላለፋል፡፡
ቫይረስ እንደሌሎቹ ማዌሮችን ኮምውተራችን በመበከል ኮምውተራችን ፍጥነቱን ይቀንሳል፤ ዳታ ያጠፋል ዋይንም ይሰርቃል፡፡ ከበድ ያሉ ቫይረሶች የክፒውተራችንን ሃረድዋር ጭምር ሊጎዱ ይችላሉ፡፡ ለምሳሌ ሃረድ ዲስክን በመጉዳት ኦፐሬቲንግ ሲይሰተማችን ክራሽ እነዲዲርግ ያደርጋሉ፡፡ 
ወርም/Worm/ 
ወርሞች በአብዛኛው ተንሰራፍተው የሚገኙ ማዌሮች ናቸው፡፡ በኔትዎርክ አማካኝነት እራሳቸውን ችለው የኦፐሬቲንግ ሲይስተማችንን ድክመት በመጠቀም የሚባዙ ናቸው፡፡ ብዙ ጊዜ ኔትዎርክን በማጨናነቅ የእንተርኔት ፍጥነት ይቀንሳሉ ፤ የኮምፒውተራችን ፕሮሰሰር በአላስፋለጊ ትዛዞች በማጨናነቅ ኮምውተራችን ቀርፋፋ ያደርጋሉ፡፡
ከቫይረስ ጋር የሚለያቸው ወርሞች የሰዎችን ድጋፍ ሳያስፈልጋቸው እራሳቸውን ማባዛት ከመቻላቸው በላይ በኢሜሎች አታች ተደርገው ወደ ኮምፒውተራችን ሊገብ ይችላሉ፡፡ ቫይረስ ግን ለመባዛት የግድ እኛ የተበከለውን ፍላሽ ዲስክ መክፈት ይንም የተበከለ ወርድ ፋይል መክፈት ይኖርብናል፡፡ 
በማልዌር የተጠቁ ኮምፒውተሮች የሚያሳያቸው ምልክቶች 
ማልዌሮች የሚያደርሱት ጉዳት እና ምልክት እንደ ማልዌሩ አይነት፤እንደ ኮምፒውተሩ አይነት እና እነደ ሚጠቀመው የ ኦፐሬቲንግ ሲሰይሰም ቢለያይም አብዛኛው ጊዜ ግን አንድ ኮምፒውተር በማልዌር ሲጠቃ ከስር የተገለጹትን ምልክቶች ያሳያል
የኮምፒውተር ፍጥነት መቀነስ 
የኢንተረኔት ፍጥነት መቀነስ ( የኢንተርኔ ፍጥነት የቀነሰው ከ ኢንተርኔ አገልግሎት ከሰጠን አካል አለመሆኑን እረግጠኛ መሆን የኖርብናል) 
  የዌብ ብራውሰራችን ማዝገም 
ከእኛ እውቅና ውጪ በተለያየ ስም የተፈጠሩ ፈይሎች ወይን የተደበቁ ፋይሎች 
የማናውቀው አይኮን ዴስክቶፓችን ላይ ሲገኝ 
ፕሮገራሞች ካለእኛ ትዛዝ ሲከፈቱ ወይንም ሲዘጉ 
 እኛ ያላክነው ኢሜይል ተልኮ ከሆነ 
ፌስቡክ ላይ እኛ ፖስት ያላደረግነው እና ካልታወቀ ምንጭ በእኛ ስም ፖስት የሚደረግ ከሆነ 
የዴስክቶፕ ከለር መዛባት 
አንዳድ ፕሮገራሞች አልከፍት ማለት በተለይ ታስክ ማናጀር አልከፈት ካለ ኮምፒውተራችን በማልዌር ተጠቅቶ ሊሆን ሰለሚችል ከተች የተገለጹትን መፍትሄዎች መተግበር ያስፈልጋል
እርምጃዎች እና ጥንቃቄዎች 
ማልዌሮች ኮምፒውተራችንን በመበከል አደጋ ከማድረሳቸው በፊት አስፈላጊውን ጥንቃቄ በማድረግ የሚፈጠረውን ችግር በከፍተኛ መልኩ መቀነስ ይቻላል፡፡ አንዴ ገብተው ጉዳት ካደረሱ በኋላ ግን ወደኋላ መመለስ በጣም አዳጋች ነው የሚሆነው ስለዚህ ቅድመ ጥንቃቅ ማድረገ የተሸለ አማራጭ ነው፡፡ 
ምንጊዜም አንቲቫይረስ መጠቀም 
የምንጠቀምባቸው አንቲቫይረሶች ተአማኝነት ያላቸው መሆኑን ማረጋገጥ ይኖርብናል 
በተቻለን መጠን አንቲቪረሳቻንን አፕቱዴት ማድረግ 
 ቀላል የሆኑ በነጻ ዶወንሎደ አድርገን የምንጠቀምባቸው አንቲቫይረሶቸ 
 McCaffe 
Avira 
Microsoft Security Essential 
 Avast
ዳውንሎድ የምናደርገው ሶፍትዌር በተለይ ቶረንት ፋይሎችን ከመክፈታችን በፊት ስካን ማድረግ ከማናውቀው አካል በኢሜላችን የሚላኩ የተላያዩ ዳውንሎድ ሊንኮችን ከመክፈት መቆጠብ ፤በተወሰነ ጊዜ ልዩነት ኮምፒውተራችንን ፉል ስካን ማድረግ፡፡

@tom_abe
614 viewsτємєѕgєи αϐєϐє τοм, 09:37
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-21 12:36:44 ምክንያታዊ እና ልማዳዊ ;

ፓራዳይም(የልቡና ውቅራችን) በተፈጥሮው ምክንያታዊ ሳይሆን ልማዳዊ ነው ! በምክንያት ህይወትን ለመቀየር መጀመር ይቻላል ያለ ልማድ ግን የፈለገ ብንጥር ጠብ የሚል ነገር የለም ምክንያቱም አእምሮ በምክንያት አይሰራም በድግግሞሽ በተገነባ እምነት እና ልማድ እንጂ።
ምን እፈልጋለው ? ለምን የምፈልገውን አይነት ሰው መሆን አቃተኝ ?
ምክንያታዊነት የሚሰራው ከእርሱ ጋር የሚዛመድ ውቅር ሲኖረን ብቻ ነው። ይህ ደግሞ በተፈጥሮ የሚገኝ ሳይሆን ሆን ብለን እራሳችን ላይ የምንገነባው አስተሳሰብ ፣ እምነት እና ልማድ ድምር ውጤት ነው።
ሆን ብሎ የሚፈልገውን እምነት እና ልማድ የማይገነባ በልጅነቱ በተቀረፀበት እና በዙሪያው በሚከናወነው ክስተቶች ህይወቱን ለመምራት የወሰነ ፍቃደኛ ነው። ብልህነት ግን ከመሻት ጋር የሚጣጣም ማንነትን በምርጫ መገንባት ነው።
"ለእድገት እና ለስኬት መርጠን እንስራ"

ህይወት ምርጫ ፣ ሂደት እና ውብ ናት !!!
ሲሳይ ምህረት

@tom_abe
476 viewsτємєѕgєи αϐєϐє τοм, 09:36
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-21 12:35:49 TRUE CALLER እንዴት ነው ሚሰራው ብላችሁ ራሳችሁን ጠይቃችሁ ታቃላችሁ ?

TRUE CALLER Application ሀከር፣መረጃ የሚሰርቅ አፕልኬሽን ሆኖ አይደለም

ነገሩ እንዲህ ነው......

ለምሳሌ አንድ ሰው ስልኩ ላይ #Truecaller Application ቢጭን ልክ እንደጫነው ስልኩ ላይ ያሉትን ኮንታክት እስከ ቁጥሩ ወደ True caller ሰርቨር ወዲያውኑ ያስተላልፈዋል ።

እንበልና የወንድሜን ስም "ኢትዮጵያ" ብዬ ብመዘግበው True caller ለሁሉም ሰው ኢትዮጵያ ብሎ ያሳያል ማለት ነው። ወንድሜ Truecaller Application ላይ ስሙን እስካልቀረ ድረስ ኢትዮጵያ ብሎ ለሁሉም ያሳያል ማለት ነዉ።

ስለዚህ Truecaller ሁል ጊዜ ትክክለኛ #ስም ያሳያል ብሎ መናገር አይቻልም።

በተጨማሪም አንድ ሰው አዲሰ ሲም ካርድ ገዝቶ ስልኩ ላይ Truecaller ካልጫነ ስሙን አያሳየንም ማለት ነው። ነገር ግን Truecaller ዳታ ቤዙ ላይ ሰርች አድርጎ ቁጥሩ ካለ ስሙን ያሳየናል።

አሁን ላይ Truecaller እንዴት እንደሚሰራ እንደገባችሁ ተስፋ አደርጋለሁ

                 #Share

@tom_abe
517 viewsτємєѕgєи αϐєϐє τοм, 09:35
ክፈት / አስተያየት ይስጡ