Get Mystery Box with random crypto!

በአዲስ አበባ ወንዝ ዉስጥ የገባው የ45 ዓመት ሰዉ አስከሬን ከ2 ሰዓታት ፍለጋ በኃላ ተገኘ | የዛሬ መረጃ ®

በአዲስ አበባ ወንዝ ዉስጥ የገባው የ45 ዓመት ሰዉ አስከሬን ከ2 ሰዓታት ፍለጋ በኃላ ተገኘ

አንበሳ ጋራዥ ላይ በደረሰ የእሳት አደጋ አራት አዉቶቢሶች ተቃጥለዋል


ማክሰኞ ሰኔ 6 ቀን 2015 (አዲስ ማለዳ) ትላንት ሰኔ 5/2015 በአዲስ አበባ ከተማ፣ አቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ ወረዳ 5 ልዩ ቦታዉ ተባበር በርታ እየተባለ በሚጠራዉ አካባቢ በሚገኝ ወንዝ ዉስጥ እድሜዉ 45 ዓመት የተገመተ ሰዉ ሕይወቱ አልፎ መገኘቱን የእሳትና አደጋ ስጋት ሥራ አመራር ኮሚሽን አስታውቋል።

የኮሚሽን መ/ቤቱ ጠላቂ ዋናተኞች ከኹለት ሰዓት ፍለጋ በኋላ ከምሽቱ 12:00 ሰዓት ሲሆን አስከሬኑን አግኝተዉ ለፖሊስ ማስረከባቸው ተገልጿል።

በሌላ በኩል፤ በዚያዉ በአቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተ ወረዳ 5 አንበሳ ጋራዥ ላይ በደረሰ የእሳት አደጋ አራት አዉቶቢሶች መቃጠላቸውን ኮሚሽኑ አስታውቋል።

የእሳት አደጋዉ የአጋጠመዉ የአንበሳ አዉቶቢስ የተሽከርካሪዎች ጥገና ጋራዥና የነዳጅ መቅጃ ማዕከል ላይ ሲሆን፤ የተቃጠሉት አዉቶቢሶች ከቅጥር ጊቢ ዉጭ ቆመዉ የነበሩ ናቸዉ ተብሏል።

የእሳት አደጋዉን ለመቆጣጠር አምስት የእሳት አደጋ መቆጣጠር ተሽከርካሪ እና 31 የአደጋ ጊዜ ሰራተኞች መሰማራታው የተነገረ ሲሆን፤ የእሳት አደጋዉ ወደ ነዳጅ ታንከርና ጋራዡ ላይ ተሳፋፍቶ ተጨማሪ ጉዳት ሳይደርስ መቆጣጠር መቻሉ ተገልጿል።

የእሳት አደጋዉን ለመቆጣጠር 1:30 ሰዓት የፈጀ ሲሆን በሰዉ ላይ የደረሰ ጉዳት አለመኖሩንም ኮሚሽኑ አስታውቋል።
____
ትክክለኛውን የአዲስ ማለዳ ሶሻል ሚዲያ በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑ
@TodayNewsEthiopia
@TodayNewsEthiopia