Get Mystery Box with random crypto!

ቀንህ ካልሆነ በተለያየ አጋጣሚ አድርጎ ጌታ ያድንሀል! አሁን ጠዋት 2ሰዓት ላይ ሁሉም ወደ ት/ቤ | የዛሬ መረጃ ®

ቀንህ ካልሆነ በተለያየ አጋጣሚ አድርጎ ጌታ ያድንሀል!

አሁን ጠዋት 2ሰዓት ላይ ሁሉም ወደ ት/ቤትና ወደ ስራ ለመግባት እየተጣደፈ ነው!እኔም ከደቂቃዎች በፊት ወደ ቢሮ ደርሻለሁ!

ይህ የምታዩት የፖሊስ መኪና ኮልፌ18 ከትክክለኛ መንገዱ በተቃራኒ ተሻግሮ አስፓልቱን አልፎ ወደኛ ቢሮ ሲገሰግስ ቆሞ የነበረው ጥበቃ እየጮኸ ሲያመልጥ ሹፌሩም አዙሮ የቆሙ መኪናዎችን እየጠራረገ ከጎን ካለው ባንክ ጄኔሬተሩ ጋር ተላትሞ ወደ መንገድ እንደገና ገብቶ ያገኘውን የተወሰነ መኪናና ሰው ገጭቶ በተዓምር ቆመ!!

በግርግሩና በለቅሶው መሀል አንዲት ዩኒፎርም የለበሰች እየተሻገረች የነበረች ህፃን ተማሪ ወደኔ መጥታ ወዲያው የጠየቀችኝ "እናቴ ጋር ደውልልኝ" የሚል ነበር!ምንም ባትሆንም መንገዷ ስለሆነ እናቷ ስትሰማ እንዳትጨነቅ በማሰብ ደህና መሆኗን ለመንገር ነው!

አንድ ወንድሜ atm ለማውጣት ባንኩ በር ላይ ቆሞ ካርዱን እየነከሰ እያስቸገረው ትንሽ ቆይቶ ሲመለስ ሊገባባት የነበረው ያቆመውን መኪና አሽቀንጥሮታል! "ውስጥ ሆኜ ብሆን እኮ አልተርፍም ነበር ተመስገን"ብሎ በመትረፉ አምላኩን አመስግኗል!

አንዲት የባንኩ ሰራተኛም መኪናዋን አቁማ ወደ ውሰጥ እንደገባች በሰከንዶች ልዩነት ውስጥ ነበር መኪናዋ ቢጎዳም እሷም ከሞትና ከከፋ አደጋ ተርፋለች!
ታክሲዎቹ ውስጥም ከሹፌሮቹ ውጪ ሰው ስላልነበር አደጋው አሰቃቂ እንዳይሆን አድርጎታል!!

ለተጎዱት እህቶቼ አምላክ ቀላል ያድርግላችሁ ሹፌሮች ሆይ የሰው ህይወት በእጃችሁ ነውና እባካችሁ በቻላችሁት ሁሉ እየተጠነቀቃችሁ ንዱ
#በሰላም_ዋሉ ከክፉ አደጋ ይጠብቃችሁ
Via: ሄኖክ ፍቃዱ