Get Mystery Box with random crypto!

#MoE • መውጫ ፈተና በመጪው ሰኔ ወር በተመሳሳይ ጊዜ ይሰጣል። • 200, 000  ተማሪዎች | Ministry of education®

#MoE

• መውጫ ፈተና በመጪው ሰኔ ወር በተመሳሳይ ጊዜ ይሰጣል።

• 200, 000  ተማሪዎች ፈተናውን ይወስዳሉ።

መውጫ ፈተና በሁሉም ዩኒቨርስቲዎች ለሚገኙ  ተማሪዎች በአንድ ጊዜ እንደሚሰጥ የከፍተኛ ትምህርት የአካዳሚክ ጉዳዮች መሪ ስራ አስፈጻሚ ገልጸዋል ።

መሪ ስራ አስፈጻሚው ኤባ ሚጀና ( ዶ/ር )  በጉዳዩ ዙሪያ በተዘጋጀ አውደጥናት ላይ  እንደገለጹት  መውጫ ፈተና በመጪው ሰኔ  ወር ለሁሉም  ቅድመ መደበኛ ተማሪዎች  በአንድ ጊዜ  ይሰጣል።

የመጀመሪያው ፈተና በሰኔ  ወር ከተሰጠ በኋላ ቀጣዩ  የመውጫ ፈተና ከ6 ወራት  በኋላ እንደሚሰጥም ዶክተር ኤባ  አስረድተዋል።

የከፍተኛ ትምህርት ጥራትና ብቃት  ዴስክ ኃላፊ አቶ ሰይድ መሀመድ በበኩላቸው ፈተናውን   ለ200, 000 የመንግስትና የግል ዩኒቨርስቲ ተማሪዎች   ለመስጠት ዝግጅት እየተደረገ መሆኑን ተናግረዋል።

ፈተናው ለሁሉም ተማሪዎች  በኦንላይን እንደሚሰጥ የጠቀሱት  አቶ ሰይድ ይህም የፈተና ስርቆትን ለመከላከል የተሻለ አማራጭ  በመሆኑ ነው ብለዋል።

የከፍተኛ ትምህርት ተቋማቱም ሆኑ ተፈታኝ  ተማሪዎች ፈተናው በተመሳሳይ ጊዜ በኦንላይን እንደሚሰጥ አውቀው ከወዲሁ ዝግጅት እንዲያደርጉም አቶ ሰይድ አሳስበዋል።

በመውጫ ፈተና ብቃትና የፈተና ኮርሶች ልየታና የተገቢነት ማረጋገጥ ዙሪያ በተዘጋጀው አውደጥናት ከሁሉም ዩኒቨርስቲዎች የተውጣጡ ጉዳዩ የሚመለከታቸው መምህራን ተሳታፊ መሆናቸውም ትምህርት ሚኒስቴር አሳውቋል።

(ትምህርት ሚኒስቴር)

መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት ቴሌግራም ገፃችንን JOIN እና ሼር ያድርጉ!

@TMIHIRT_MINISTER
@TMIHIRT_MINISTER