Get Mystery Box with random crypto!

ወደ ት/ቤት በመሄድ ላይ የነበረችን ልጅ አስገድዶ የደፈረው ግለሰብ በ8 አመት ፅኑ እስራት ተቀጣ፡ | Ministry of education®

ወደ ት/ቤት በመሄድ ላይ የነበረችን ልጅ አስገድዶ የደፈረው ግለሰብ በ8 አመት ፅኑ እስራት ተቀጣ፡፡

ደቡብ ጎንደር ዞን ደራ ወረዳ በአንበሳሜ ከተማ ህዳር 19 ቀን 2015 ዓ.ም ከቀኑ 7፡00 ሰዓት ላይ ተማሪ አበባይቱ አራጋው ወደ አንበሳሜ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ለመማር በመሄድ ላይ እያለች ተፈራ ማሬ ካሳ የተባለ ግለሰብ አስፈራርቶ በመያዝ አስገድዶ ሲደፍራት በአካባቢው የጸጥታ ሀይል ይያዛል።

በዚህም ወንጀለኛው ላይ ምርመራው በማድረግ አቃቢ ህግ ክስ መስርቶበት የወረዳው ፍ/ቤትም መዝገቡን መርምሮ ጥፋተኛ መሆኑን በማስረጃ በማረጋገጥ ህዳር 27 ቀን 2015 ዓ.ም በዋለው ችሎት በ8 አመት ፅኑ እስራት የተቀጣ መሆኑን ተገልጿል፡፡

መረጃው፦ የደራ ወረዳ ኮሚኒኬሽን ነው

መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት ቴሌግራም ገፃችንን JOIN እና ሼር ያድርጉ!

@TMIHIRT_MINISTER
@TMIHIRT_MINISTER