Get Mystery Box with random crypto!

#KotebeUniversityOfEducation ኮተቤ የትምህርት ዩኒቨርሲቲ የተቋሙን አዲስ ሎጎ | Ministry of education®

#KotebeUniversityOfEducation

ኮተቤ የትምህርት ዩኒቨርሲቲ የተቋሙን አዲስ ሎጎ በይፋ አስመርቋል።

አዲሱ አርማ ተቋሙ ወደ አዲስ ምዕራፍ መሸጋገሩን የሚያመለክት መሆኑን የዩኒቨርሲቲው ፕሬዝዳንት ብርሃነመስቀል ጠና (ዶ/ር) ተናግረዋል።

የየራሳቸው ትርጓሜ ያላቸው ጸሐይ፣ ደረጃዎች፣ መፅሀፍ እና የዲግሪ ቆብ ምልክቶች በአርማው ላይ ሰፍረዋል።

በተጨማሪም የዩኒቨርሲቲው መዝሙር በአርቲስት ሙሉ ገበየሁ በአዲስ መልክ ተሰርቶ መጠናቀቁም ተገልጿል።

የዩኒቨርሲቲውን መዋቅር ጨምሮ በርካታ አስተዳደራዊ ጉዳዮች እየተሰሩ እንደሆነ የጠቆሙት ፕሬዝዳንቱ፤ የአራት አዳዲስ ህንፃዎች ግንባታ መጀመሩንም ገልጸዋል።

ለጓደኛዎ ሼር ያድርጉ

@TMIHIRT_MINISTER
@TMIHIRT_MINISTER