Get Mystery Box with random crypto!

ሰላም ውድ የቻናሌ ቤተሰቦች አንደምን ቆያችሁኝ የእግዚአብሔር ሰላም በሁላችንም ላይ አድሮ ይኑር | ✝️(ትምህርተ ግዕዝ)✝️

ሰላም ውድ የቻናሌ ቤተሰቦች አንደምን ቆያችሁኝ
የእግዚአብሔር ሰላም በሁላችንም ላይ
አድሮ ይኑር ።
ያው እንደሚታወቀው በቅርቡ መዝሙሮችን እንዳሉኝና መዝሙር ማውጣት የምትፈልጉ መዝሙሮችን መውሰድ እንደምትችሉ ተናግሬ ነበር።
በዚህም ምክንያት የእግዚአብሔር መልካም ፍቃድ ሁኖ ከብዙ ወንድምና እህቶቼ ጋር ትልቅ ዝምድና እንድፈጥር አድርጎኛል ።
አሁን አሁን ግን ብዙዎች መዝሙር እንፈልጋለን ብለው መተው የመዝሙር ርዕስ ከመረጡ በኋላ ቅድሚያ ክፍያውን ሳይከፍሉ መዝሙሩን እንውሰድ ይላሉ ።ይህ ደሞ የማይሆን ነገር ነው ምክንያቱን በኋላ እመለስበታለሁ።
ለአሁን ግን እነዚህ ሰዎች መጀመሪያ ክፍያ ክፈሉና ሙሉ የመዝሙር ግጥም ና ዜማ መውሰድ ትችላላችሁ በምላቸው ሰአት ቢያንስ አንድ ነጠላ መግዣ እንኳን የማትሞላ ገንዘብ ከፍለው ለመውሰድ ይሞክራሉ ይህ ሳይሳካላቸው ሲቀር የመጨረሻው እድል በመጠቀም አጀንዳቸውን ወደ ሌላ ይቀይራሉ ያማለት ያላዩትን
1 የመዝሙር ግጥም ከሌላ ነው የተወሰደው መዝሙሩ የወጣ ነው ,
2ፍቃድ አምጣ,
ሌሎች ሌሎችንም በጣም እዚህ መለጠፍ የማይችሉ አሳዛኝ ነገሮችን ይልካሉ።
#የመጀመሪያው የኔን መዝሙር ግጥም ሳያዩ ከሌላ ነው የተወሰደው ማለት ምን ማለት እንደሆነ ለናንተ እተወዋለሁ ። እንዴት የመዝሙሩን ግጥም ሳይታይ ከሌላ ጋር ማወዳደር ይቻላል ።
#ሁለተኛው እኔ እስከአሁን ፍቃድ /ካርድ ይቺ ቤተክርስቲያን የሰጠችኝ የድቁና ካርድ ብቻ ነው አሁን በአለሁበት ደረጃ የመዝሙር ግጥም ለመስጠት ፍቃድ ስትሰጥ አላየሁም ምን አልባት ፍቃዱ የውሸት /የዲያቢሎስ ከሆነ ቢቀርብኝ ይሻላል።
እኔ መዝሙር ከመስጠቴ መጀመሪያ ክፍያ ያልኩበት ምክንያት ።
ከዚህ በፊት ለ 2 ሰዎች ብር ሳልቀበል መዝሙሮችን ከሰጠሁ በኋላ እንክዋን ክፍያውን ሊከፍሉ ቀርቶ ሊያወሩኝ እራሱ ፍቃደኛ አልሆኑም ።
ስለዚህ መጀመሪያ መቀበል ተገቢ ስለሆነ ሰላወኩ መጀመሪያ ክፍያውን እቀበላለሁ ከዛ ሙሉ ግጥምና ዜማውን እሰጣለሁ።
በዚህ ሳንስማማ ስንቀር የሰውን ማንነት ሳናውቅ ብዙ ከምናወራ መመርመር ያስፈልጋል።
አሁንም ለወደፊትም እግዚአብሔር በሰጠኝ ትንሿ ስጦታ ቤተክርስቲያን ማገልግ አላቆምም።
ምን አልባች እኔን በአካል ማግኘት ለምትፈልጉ አድራሻየ ደሴ (Dessie) ነው በፈለጋችሁት ሰአት እቴኝ ማግኘት ትችላላችሁ ።
እንዲሁም 0939113584
በቴሌግራም አድራሻ @gtzatwe
እኔን ማግኘት ና ማነጋገር ትችላላችሁ።
ከዚህ ውጪ ግን በማይረባ ንግግር ባንረክስ መልካም ነው እላለሁ።
ሁላችንንም እግዚአብሔር በምህረቱ ይጠብቀን።