Get Mystery Box with random crypto!

✝️(ትምህርተ ግዕዝ)✝️

የቴሌግራም ቻናል አርማ tmhrtegeeze — ✝️(ትምህርተ ግዕዝ)✝️
የቴሌግራም ቻናል አርማ tmhrtegeeze — ✝️(ትምህርተ ግዕዝ)✝️
የሰርጥ አድራሻ: @tmhrtegeeze
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 5.13K
የሰርጥ መግለጫ

በዚህ ቻናልየተለያዩ ትምህርቶች ያገኛሉ
ከነዚህም ውስጥ ✝️የግዕዝ ትምህርት
✝️የተለያዩመፅሐፉን
✝️ የተለያዮ መንፈሳዊ ስብከቶች ✝️መንፈሳዊፊ ልሞች ወ.ዘ.ተ ያገኛሉ።

Ratings & Reviews

2.33

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

0

3 stars

1

2 stars

2

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች

2022-09-02 05:00:00
የመስቀል መዝሙሮችን ከነግጥሞቻቸው ቀድመው ለሚያጠኑ ሰንበት ትምህርት ቤት ያቀረበውን ቻናል በመቀላቀል ከታች ያሉትን መዝሙሮች ያጥኑ።


@Orthodox_addis_mezmur
@Orthodox_addis_mezmur
@Orthodox_addis_mezmur


መስቀል አበባ.mp3
መስቀል ተመሬኩዘን.mp3
ደስ ይበለን.mp3
እሰይ እልል በሉ.mp3
ዮም መስቀል.mp3
ቤተከርስቲያን ርእየቶ.mp3
በመስቀሉ ቤዘወነ.mp3
መስቀሉሰ.mp3
መስቀል ብርሃን.mp3
አለው ሞገስ.mp3
መስቀል አብርሃ.mp3
ርዕዩ ዕበዩ.mp3
በኃይለ መስቀሉ.mp3
ተሰኢነነ.mp3
ትቤሎ ዕሌኒ.mp3
ወይቤሎ መስቀል.mp3
ኧኸ በመስቀልከ.mp3
ወበእንተዝ አዘዙነ.mp3
ዝንቱ መስቀል ረድኤት.mp3
ደስ ይበለን.mp3
መስቀል አበራ.mp3


𝒔𝒖𝒃𝒔𝒄𝒓𝒊𝒃𝒆 𝒏𝒐𝒘
@Orthodox_addis_mezmur
@Eotc_Books_By_Pdf
@orthodox_spiritual_poems
@Lesangeez128
𝒔𝒖𝒃𝒔𝒄𝒓𝒊𝒃𝒆 𝒏𝒐𝒘 ‌‌
2 views02:00
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-01 21:17:49
. Elohe Graphics

ለፕሮፋይል ፒክቸር የሚሆኑ ልዩ ኦርቶዶክሳዊ ፎቶዎች
ለ ቴሌግራም የሚሆኑ ፕሮፋይል ፒክቸሮች

የ መፅሃፍ ቅዱስ ጥቅሶች በፎቶ

ለ ስጦታ የሚሆኑ በልዩ ዲዛይን የቀረቡ የፀሎት ቤት እቃዎች

የ ፃድቃን ስዕለ አድኅኖዎች

የ ኦርቶዶክሳዊ ቻናሎች ልዩ ልዩ ሎጎዎች
መንፈሳዊ ፎቶዎችን ማግኘት ይፈልጋሉ
መልሶት አዎ ከሆነ ከስር ያለውን ሊንክ በመጠቀም ማግኘት ይችላሉ ገብታችሁ እዩት በጣም ትደነቁበታላችሁ
ቻናሉን ለመቀላቀል ሰማያዊውን ይጫኑ


https://t.me/+Ci5F1FcleWtlZThk

https://t.me/+Ci5F1FcleWtlZThk

https://t.me/+Ci5F1FcleWtlZThk

81 views18:17
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-17 19:01:43 ​​ቡሄበሉ

ቡሄ በሉ (፪) - - ሆ ልጆች ሁሉ - - ሆ
የኛማ ጌታ - - ሆ የዓለም ፈጣሪ - - ሆ
የሰላም አምላክ - -ሆ ትሁት መሀሪ -ሆ
በደብረ ታቦር - - ሆ የተገለጠው - ሆ
ፊቱ እንደ ፀሐይ - ሆ በርቶ የታየው -ሆ
ልብሱ እንደብርሃን -ሆ ያንፀባረቀው -ሆ

ድምጽህን ሰማና በብህሩ ደመና(፪)
የቡሄው ብርሃን ለኛ መጣልን(፪)

ያዕቆብ ዮሐንስ-ሆ እንዲሁም ጴጥሮስ-ሆ
አምላክን አዩት - - ሆ ሙሴ ኤልያስ - ሆ
አባቱም አለ - - ሆ ልጄን ስሙት - - ሆ
ቃሌ ነውና - - ሆ የወለድኩት - - ሆ

አዝ======

ታቦር አርሞንኤም-ሆ ብርሃን ታየባቸው ሆ
ከቅዱስ ተራራ ሆ ስምህ ደስ አላቸው- ሆ
ሰላም ሰላም - - ሆ የታቦር ተራራ - - ሆ
ብርሀነ መለኮት - ሆ ባንቺ ላይ አበራ -ሆ

አዝ======

ሙሉ መዝሙሩን ለማግኘት ከስር ይጫኑ

▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬
█ ▒ ░✞ 𝑶𝑷𝑬𝑵 ❖ 𝑶𝑷𝑬𝑵 ✞░ ▒ █
█ ▒ ░✞ 𝑶𝑷𝑬𝑵 ❖ 𝑶𝑷𝑬𝑵 ✞░ ▒ █
█ ▒ ░✞ 𝑶𝑷𝑬𝑵 ❖ 𝑶𝑷𝑬𝑵 ✞░ ▒ █
▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬

<< ታቦርና አርሞንኤም በስምህ ደስ ይላቸዋል >>
መዝ፹፰፥፲፪

እንኳን ለደብረ ታቦር / ቡሄ
በሰላም አደረሳችሁ አደረሰን።
1.7K views16:01
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-09 08:33:36 ፲፬. እናትነትን ከአገልጋይነት ጋር /ሉቃ.፩፡፴፰/ ያለሽ እመቤታችን ሆይ! ደስ ይበልሽ፡፡ በክንድሽ የያዝሺውን (የታቀፍሽውን) መላእክት ያመሰግኑታልና፡፡ እሳታውያን የኾኑ ሱራፌልም ሳያቋርጡ ክንፋቸወን ዘርግተው፡- “የክብር ባለቤት ይህ ነው” ይላሉ፡፡ “በቸርነቱ በይቅርታው ብዛት የሰውን ኹሉ ኃጢአት ለማስተሥረይ ሰው የኾነ የክብር ባለቤት ይህ ነው” እያሉ በፍርሐት በረዐድ ኾነው ያመሰግኑታል፡፡ የሰውን ኃጢአት በቸርነቱ ብዛት ከሚያሰተሠርይ ልጅሽ ጽንዕት በድንግልና እመቤታችን ጸጋውን ክብሩን እንዳይነሣን ለምኚልን፡፡

ይህን ሲጨርስ በያዘችው መስቀለ ብርሃን ባርካው ታርጋለች፡፡ እርሱም ተባርኮ እጅ ነሥቶ ይቀራል፡፡


አነሣሥቶ ላስጀመረን ፤ አስጀምሮም ላስፈጸመን ለልዑል እግዚአብሔር ክብር ምስጋና ይግባው አሜን።
https://t.me/tmhrtegeeze
1.5K views05:33
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-20 13:27:21
ገዳማትን እወዳለሁ የጥበብ ምንጭ ናቸው የምህረት መፍለቂያ ናቸው ችዬ ባግዛቸው በአፍ ብቻ መሆን የለበትም ወገኔ ዛሬ ላይ ገዳማት በአረም እየተሸፈኑ ነው ከዚህም ውስጥ አንዱ
መካነ ሕይወት ጮቢ በዓታ ለማርያም ገዳም ነው በትናንትናው ዕለት የወጣው ደብዳቤ ከላይ ተያይዟል ወገኔ ለገዳማት ለአድባራት እንድረስ ካሁን በፊት እርዳታም ሆነ በሌላ ነገር ገዳሙን ማገዝ ያልቻን ጊዜው አሁን ነው ያላችሁ በገንዘብ የሌላችሁ ደሞ ይህን መልእክት ቢያንስ ለአንድ የተዋሕዶ ልጅ ብትልኩለት እሱ መርዳት ይችል ይሆናል እና በገንዘብ መርዳት ካልቻላችሁ አሁንኑ ሼር አድርጉ

የእናንተን እረዳታ ይፈልጋል ከላይ ደብዳቤው እንደተገለጸው የስንዴ ፣ የአተር፣ ባቄላ፣ በተጨማሪ የጤፈ ማስ ጀምረን እራሳችንን ለመቻል እያደረግነው ጥረት በአረም ምክንያት ችግር ወስጥ ልንወድቅ ነው እናም ሰለበዓታ ስትሉ የምትችሉትን እርዱን።

የሚያስፈልገው

36 ፖላስ አረም።

ማጥፊያ የሰንዴና የጤፍ
24ዲ ፎር ዲ የባቄላና አተር አረም ማጥፊያ

ገዝቶ ለማቀበል ለሚፈልግ 0927707000 መጠቀም ይቻላል ወይም @BeGood16 በመጠቀም ሊያወራኝ ይችላሉ
በገንዘብ ለመርዳት ከታች ያለውን account ተጠቀሙ
ንግድ ባንክ
መካነ ሕይወት ጮቢ በዓታ ለማርያም አንድነት ገዳም
1000075836116

አደራ በፍጥነት ለተዋህዶ ልጆች ሼር በማድረግ ለእግዚአብሔር አበድሩ እርሱ ብድርን የማይመልስ አይደለምና

የግእዝ ትምህርት በyoutube
https://youtube.com/channel/UCbuXpsXU7hDaFWELjzHlxdg


𝒔𝒖𝒃𝒔𝒄𝒓𝒊𝒃𝒆  
@Orthodox_Addis_mezmur
@orthodox_spiritual_poems
@Eotc_Books_By_Pdf
@Lesangeez128
𝒔𝒖𝒃𝒔𝒄𝒓𝒊𝒃𝒆
2.6K views10:27
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-09 21:01:08 ሰላም ውድ የቻናሌ ቤተሰቦች አንደምን ቆያችሁኝ
የእግዚአብሔር ሰላም በሁላችንም ላይ
አድሮ ይኑር ።
ያው እንደሚታወቀው በቅርቡ መዝሙሮችን እንዳሉኝና መዝሙር ማውጣት የምትፈልጉ መዝሙሮችን መውሰድ እንደምትችሉ ተናግሬ ነበር።
በዚህም ምክንያት የእግዚአብሔር መልካም ፍቃድ ሁኖ ከብዙ ወንድምና እህቶቼ ጋር ትልቅ ዝምድና እንድፈጥር አድርጎኛል ።
አሁን አሁን ግን ብዙዎች መዝሙር እንፈልጋለን ብለው መተው የመዝሙር ርዕስ ከመረጡ በኋላ ቅድሚያ ክፍያውን ሳይከፍሉ መዝሙሩን እንውሰድ ይላሉ ።ይህ ደሞ የማይሆን ነገር ነው ምክንያቱን በኋላ እመለስበታለሁ።
ለአሁን ግን እነዚህ ሰዎች መጀመሪያ ክፍያ ክፈሉና ሙሉ የመዝሙር ግጥም ና ዜማ መውሰድ ትችላላችሁ በምላቸው ሰአት ቢያንስ አንድ ነጠላ መግዣ እንኳን የማትሞላ ገንዘብ ከፍለው ለመውሰድ ይሞክራሉ ይህ ሳይሳካላቸው ሲቀር የመጨረሻው እድል በመጠቀም አጀንዳቸውን ወደ ሌላ ይቀይራሉ ያማለት ያላዩትን
1 የመዝሙር ግጥም ከሌላ ነው የተወሰደው መዝሙሩ የወጣ ነው ,
2ፍቃድ አምጣ,
ሌሎች ሌሎችንም በጣም እዚህ መለጠፍ የማይችሉ አሳዛኝ ነገሮችን ይልካሉ።
#የመጀመሪያው የኔን መዝሙር ግጥም ሳያዩ ከሌላ ነው የተወሰደው ማለት ምን ማለት እንደሆነ ለናንተ እተወዋለሁ ። እንዴት የመዝሙሩን ግጥም ሳይታይ ከሌላ ጋር ማወዳደር ይቻላል ።
#ሁለተኛው እኔ እስከአሁን ፍቃድ /ካርድ ይቺ ቤተክርስቲያን የሰጠችኝ የድቁና ካርድ ብቻ ነው አሁን በአለሁበት ደረጃ የመዝሙር ግጥም ለመስጠት ፍቃድ ስትሰጥ አላየሁም ምን አልባት ፍቃዱ የውሸት /የዲያቢሎስ ከሆነ ቢቀርብኝ ይሻላል።
እኔ መዝሙር ከመስጠቴ መጀመሪያ ክፍያ ያልኩበት ምክንያት ።
ከዚህ በፊት ለ 2 ሰዎች ብር ሳልቀበል መዝሙሮችን ከሰጠሁ በኋላ እንክዋን ክፍያውን ሊከፍሉ ቀርቶ ሊያወሩኝ እራሱ ፍቃደኛ አልሆኑም ።
ስለዚህ መጀመሪያ መቀበል ተገቢ ስለሆነ ሰላወኩ መጀመሪያ ክፍያውን እቀበላለሁ ከዛ ሙሉ ግጥምና ዜማውን እሰጣለሁ።
በዚህ ሳንስማማ ስንቀር የሰውን ማንነት ሳናውቅ ብዙ ከምናወራ መመርመር ያስፈልጋል።
አሁንም ለወደፊትም እግዚአብሔር በሰጠኝ ትንሿ ስጦታ ቤተክርስቲያን ማገልግ አላቆምም።
ምን አልባች እኔን በአካል ማግኘት ለምትፈልጉ አድራሻየ ደሴ (Dessie) ነው በፈለጋችሁት ሰአት እቴኝ ማግኘት ትችላላችሁ ።
እንዲሁም 0939113584
በቴሌግራም አድራሻ @gtzatwe
እኔን ማግኘት ና ማነጋገር ትችላላችሁ።
ከዚህ ውጪ ግን በማይረባ ንግግር ባንረክስ መልካም ነው እላለሁ።
ሁላችንንም እግዚአብሔር በምህረቱ ይጠብቀን።
2.5K views18:01
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-09 19:08:51 በዚህ ክረምት ሁለቱን ወር የግእዝ ቋንቋን ይሰልጥኑ

|°°|ለጀማሪ የግእዝ ቋንቋ ወዳጆች በሙሉ
ሰላም ጤና ይስጥልን ክቡራት እና ክቡራን የልሳነ ግእዝ ስልጠና በ @lesangeez128 እየሰጠን እንደሆነ ይታወቃል ሆኖም የጀማሪዎች ስልጠና በቅርቡ በonline ስለሚጀመር በዚህ #ዙር ላይ 20 ተማሪዎች ብቻ ስለሚካተቱ ከወዲሁ እንድታዘጋጁና በፍጥነት እንድትመዘገቡ መልእክታችንን እናስተላልፋለን።
#ለሁለት ወር የመማሪያ ክፍያ #200ብር ብቻ ለበለጠ መረጃ በ @asrategabriel ያነጋግሩን አልያም በ +251914946589 ይደውሉልን።

ሰብሕዎ የልሳነ ግእዝ ማሰልጠኛ ተቋም
1.7K views16:08
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-09 18:08:31 እሽ እህቴ
ትልቅ የምስራች ለመላው ኦርቶዶክሳዊያን በሙሉ።
ለዘማሪዎች እንዲሁም አዲስ መዝሙር ለማውጣት የምትፈልጉ።




#መዝሙሮችን_ማውጣት_የምትፈልጉ ።
ሙሉ ግጥምና ዜማ ሁሉም የተዘጋጀ ነው። ነጠላም ከፈለጋችሁ ሙሉ አልበም በፈለጋችሁት ከእኔ ማግኘት ትችላላችሁ።
#እጅግ_በጣም_ተወዳጅ_የሆኑ_ሙሉ_ስራ #ያለቀላቸው_ብዛት_መዝሙሮች_ #ማግኘትት_ችላላችሁ።
#በተላይ_አሁን_ቤተክርስትያን_ያለችበትን_ወቅታዊሁኔታ_የሚያወሱ_መዝሙሮች_አሉኝ።
#እንዲሁም_የኢትዮጵያ_ኦርቶዶክስ_ተዋህዶን ዶግማና_ቀኖና_የጠበቁ #የምስጋና_,የበአላት_,የንስሐ_,እንዲሁም_እንዲሁም የፆም_ወቅትመዝሙሮችን ማግኘት ይችላሉ።

#እጄ_ላይ_ከሚገኙት_መዝሙሮች_በጥቂቱ

ቃልህ የታመነ(መድሀኒአለም)
ፍቅር ነህ አንተ (መድሀኒአለም)
የመስቀሉ ስር ሰጦታየ(ድግል ማርያም)
አንቀፀ ብርሃን (ድግል ማርያም )
የምህረት እናት ናት(ድግል ማርያም)
የፈጠረሽ እሱ (ድግል ማርያም)
እኔ እጠራሻለሁ (ድግል ማርያም)
ሚካኤል ሆይ እርዳን
ሌሎችም ሙሉ ግጥምና ዜማ ያለቀላቸው መዝሙሮችን ያገኛሉ።
በ @gtzatwe ማማናገር ትችላላችሁ።
በስልክ 0939113584 ላይ ማናገር ትችላላችሁ በታማኝነት ሙሉ መዝሙሮችን እንሰጣችኋለን ።
ሙሉ አልበምና ግማሽ አልበም ለምትወስዱ የተለየ ቅናሽ አለን።
ለሌሎችም መልዕክቱን ሼር በማረግ ተባበሩኝ።
https://t.me/DIYAKONAE
1.7K views15:08
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-04 19:26:03 ትልቅ የምስራች ለመላው ኦርቶዶክሳዊያን በሙሉ።
ለዘማሪዎች እንዲሁም አዲስ መዝሙር ለማውጣት የምትፈልጉ።




#መዝሙሮችን_ማውጣት_የምትፈልጉ ።
ሙሉ ግጥምና ዜማ ሁሉም የተዘጋጀ ነው። ነጠላም ከፈለጋችሁ ሙሉ አልበም በፈለጋችሁት ከእኔ ማግኘት ትችላላችሁ።
#እጅግ_በጣም_ተወዳጅ_የሆኑ_ሙሉ_ስራ #ያለቀላቸው_ብዛት_መዝሙሮች_ #ማግኘትት_ችላላችሁ።
#በተላይ_አሁን_ቤተክርስትያን_ያለችበትን_ወቅታዊሁኔታ_የሚያወሱ_መዝሙሮች_አሉኝ።
#እንዲሁም_የኢትዮጵያ_ኦርቶዶክስ_ተዋህዶን ዶግማና_ቀኖና_የጠበቁ #የምስጋና_,የበአላት_,የንስሐ_,እንዲሁም_እንዲሁም የፆም_ወቅትመዝሙሮችን ማግኘት ይችላሉ።

#እጄ_ላይ_ከሚገኙት_መዝሙሮች_በጥቂቱ

ቃልህ የታመነ(መድሀኒአለም)
ፍቅር ነህ አንተ (መድሀኒአለም)
የመስቀሉ ስር ሰጦታየ(ድግል ማርያም)
አንቀፀ ብርሃን (ድግል ማርያም )
የምህረት እናት ናት(ድግል ማርያም)
የፈጠረሽ እሱ (ድግል ማርያም)
እኔ እጠራሻለሁ (ድግል ማርያም)
ሚካኤል ሆይ እርዳን
ሌሎችም ሙሉ ግጥምና ዜማ ያለቀላቸው መዝሙሮችን ያገኛሉ።
በ @gtzatwe ማማናገር ትችላላችሁ።
በስልክ 0939113584 ላይ ማናገር ትችላላችሁ በታማኝነት ሙሉ መዝሙሮችን እንሰጣችኋለን ።
ሙሉ አልበምና ግማሽ አልበም ለምትወስዱ የተለየ ቅናሽ አለን።
ለሌሎችም መልዕክቱን ሼር በማረግ ተባበሩኝ።
https://t.me/DIYAKONAE
1.6K views16:26
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-28 08:53:04 #ሰኔ_21


ዝ ክ ረ - ቅ ዱ ሳ ን


በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ
አሐዱ አምላክ፡፡ አሜን፡፡


እ ን ኳ ን አ ደ ረ ሳ ች ሁ!


ሰኔ 21 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት...

✞ ሰ ኔ ጐ ል ጐ ታ ✞

ቅድስት ድንግል እመቤታችን ማርያም በዚህ ቀን (ሰኔ ፳፩) ልጇን ወዳጇን ጐልጐታ ላይ ለኃጥአን ምሕረትን ለምናዋለች። ጌታችንም "ስምሽን የጠራውን፣ በቃል ኪዳንሽ ያመነውን ሁሉ እምርልሻለሁ።" ብሏታል።

የድንግል እመቤታችን ልመናዋ፣ ክብሯ፣ ጣዕመ ፍቅሯና በረከቷ በሁላችን ላይ ይደርብን።

✣✣✣✣✣✣✣✣✣✣✣✣✣✣✣✣✣✣

ትናንት ለስም አጠራሩ ጌትነት ይሁንና ጌታችንና መድኃኒታችን ኢየሱስ_ክርስቶስ ወደ ሐዋርያት ወረደ። ፊልዽስዩስ በምትባል ሃገር በዼጥሮስ እጅ የመጀመሪያዋን ቤተ_ክርስቲያን አነጸ። በዚህች ዕለት ደግሞ አእላፍ መላዕክትን: ሰማያውያን ቅዱሳንን እና እናቱን ቅድስት ድንግል ማርያምን ይዟት ወረደ።

ሐዋርያቱ አብዛኞቹ እዛው ሲጸልዩ አድረው ነበርና ጌታችን ከቅዳሴው በፊት 2 ነገሮችን አሳየ:-
1. አስቀድሞ ቤተ ክርስቲያኗን በድንግል እናቱ ስም አክብሮ ሥርዓተ ቤተ ክርረስቲያንን አሳየ።
2. ቀጥሎ ደግሞ ሊቀ ሐዋርያት ቅዱስ_ዼጥሮስን ከመካከል አቁሞ "አርሳይሮስ" ሲል ሾመው። ይኼውም የዓለም ሁሉ ሊቀ ዻዻሳት (ፓትርያርክ) ማለት ነው። በዚህ ጊዜ ቅዱሳን መላእክት "አክዮስ" እያሉ 3 ጊዜ አሰምተው ጮሁ። አክዮስ ማለት በግዕዙ "ይደልዎ": በዐማርኛው ደግሞ "ይገባዋል: ያሥምርለት" እንደ ማለት ነው።

ጌታችን ይሕን ከከወነ በኋላ ይቀድስ ዘንድ ጀመረ።
✟ አማናዊት ማሕደሩን ድንግል ማርያምን መንበር አድርጎ:
✟ ቅዱስ ዼጥሮስ እንደ ተራዳኢ ካህን ቆሞ:
✟ ቅዱስ_እስጢፋኖስ ሠራኢ ዲያቆን ሆኖ:
✟ ሐዋርያት ድንግልን ከበው:
✟ መላእክተ ብርሃን በክብራቸው ቁመው ጌታችን ቀድሶ ቅዱስ ሥጋውንና ክቡር ደሙን ለወዳጆቹ አቀበለ።

በዚያች ዕለት በፍጡር አንደበት ተከናውኖ ሊነገር የማይችል ደስታ ተደረገ። ከቅዳሴ በኋላ ጌታችን ሐዋርያትን አዘዛቸው። "ከዚህ ቀን ጀምሮ በመላው ዓለም በእናቴ በማርያም ስም አብያተ ክርስቲያናትን እነጹ። ይህችን ዕለት የሚያከብራትን አከብረዋለሁ።" ብሏቸው ከድንግል እናቱ ከመላዕክቱ ጋር ዐረገ።

✣✣✣✣✣✣✣✣✣✣✣✣✣✣✣✣✣✣

#ቅዱስ_ቶማስ

ዳግመኛ በዚህ ቀን ሐዋርያው ቅዱስ ቶማስ ይታሰባል። ይኸውም ከሕንድ አውራጃዎች በአንዱ ወንጌልን ሰብኮ እኩሎቹ ሲያምኑ እኩሎቹ እንቢ አሉ። ቅዱስ ቶማስም ያመኑትን "ከጣዖት አምልኮና ከዝሙት ሸሹ" ብሎ መከራቸው። ምክሩን ከሰሙት አንዱ በዚያው ምሽት ሊጠጣ ወደ መሸታ ቤት ይገባል። ሰው ሁሉ ከወጣ በኋላ ባለ መሸተኛዋ ሴት እንደለመደችው አብረው እንዲተኙ ስትጠይቀው "እንዴት ሐዋርያው ከዝሙት ሽሹ እያለ እንዲህ ትይኛለሽ?" በሚል ሰይፍ አውጥቶ አንገቷን ቆረጣት።

እርሱ መልካም ያደረገ መስሎታል። የሠራው ሥራ (መግደሉ) ግን አሕዛባዊ ግብር ነው። በማግስቱ ቅዱስ ቶማስ ነገሩን ሰምቶ ሰዎችን ሰበሰበና "ይህንን የአውሬ ድርጊት የፈጸመ ማነው?" ሲል ጠየቀ። ፈጻሚው ግን አልታወቅም በሚል ዝም አለ። ወዲያው ቅዱሱ ሐዋርያ ዳቦ አንስቶ ቆረሰና "ለበረከት እያነሳችሁ ውሰዱ" አለ። ሰውየው ተራውን ጠብቆ ሊያነሳ ሲል እጁ ሰለለች።

ሐዋርያው "ምነው ልጄ! ምን ሆንክ?" አለው። እሱም እንዳላመለጠ ሲያውቅ እውነቱን ተናዘዘ። ቅዱስ ቶማስ ግን ሕዝቡ ሁሉ እንደተሰበሰበ ያን ወጣት ገስጾ "አስከሬኑን አምጡልኝ" አለ። የወጣቱን እጅ ፈውሶ "በል . . .
የገደልኩሽ እኔ: የሚያስነሳሽ ግን ጌታየ_ኢየሱስ_ክርስቶስ ነው . . . ብለህ አንገቷን ቀጥለው" አለው።

እንዳለው ቢያደርግ የሞተችው አፈፍ ብላ ተነሳች። ይህንን ተአምር ያዩ አሕዛብ አምነው ተጠምቀዋል።

ከሐዋርያው በረከት ይክፈለን።

-----------------------------------------------------------
"ስለ ጽዮን ዝም አልልም . . .
አሕዛብም ጽድቅሽን: ነገሥታትም ሁሉ ክብርሽን ያያሉ። የእግዚአብሔርም አፍ በሚጠራበት በአዲሱ ስም ትጠሪያለሽ። በእግዚአብሔር እጅ የክብር አክሊል በአምላክሽም እጅ የመንግሥት ዘውድ ትሆኛለሽ።" (ኢሳ. 62:1-3)

<<< ወስብሐት ለእግዚአብሔር >>>

"ፍቅር ያጌብረኒ ከመ እንግር ዜናሆሙ ለቅዱሳን"። /የቅዱሳንን ዜና(ታሪክ) እንድመሰክር ፍቅር ያስገድደኛል። አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ /መጽሐፈ ምሥጢር/

#ስንክሳር_ዘወርሃ_ሰኔ
https://t.me/DIYAKONAE
1.7K views05:53
ክፈት / አስተያየት ይስጡ