Get Mystery Box with random crypto!

Daewa selefiya

የቴሌግራም ቻናል አርማ twhidfirstt — Daewa selefiya D
የቴሌግራም ቻናል አርማ twhidfirstt — Daewa selefiya
የሰርጥ አድራሻ: @twhidfirstt
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 540
የሰርጥ መግለጫ

ቅድመያ ለተውሂድ እንላለን ምክንያቱም የተፈጠርንበት አላማ ስለሆነ
(ጂንንም ሆነ ሰውን አልፈጠርኳቸውም እኔን [በብቸኝነት] እንዲያመልኩኝ እንጂ) [አዝዛሪያት:55]

Ratings & Reviews

3.33

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

1

4 stars

1

3 stars

0

2 stars

0

1 stars

1


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች

2022-08-03 12:02:15 ኢንና ሊልላሂ ወኢንና ኢለይሂ ራጂዑን:
አሳዛኝ እውነተኛ ታሪክ በጣም ልብ የሚነካ
#ሼርርርርአርጉት ለሚድያ ተጠቃሚ

#በተቀናበር. ፎቶ እራሷን ያጠፍችው እህታችን
በእድሜዋ አነስ ያለች ወጣት ሴት
የውሸት የሆነ ነገር መጣላት
በአንድ ፕሮግራም ላይ የተነሳችውን. ፎቶ ተላከላት እህቴ ሆይ በአላህ ንቂ
ልጆቻችንን አላህን እንድፍሩ ልናስጠነቅቅ ይገባል ።
ፎቶችሁን በማህበራዊ ሚድያ ላይ አትልቀቁ ዘመኑ እጅግ አስፍሪ ነው
አንዱን የሷን ፎቶ ይዘው ከሌላ ፎቶ ጋር አቀናብርው
የማትፍልገው የራቁት ፎቶ ጋር አቀናበሩት
ከዚያም ላኩላት
ወደእሷ እና ወደቤተሰቦቿ ብላክ ሜል አደርጓት
ቤተሰብወቿ አዋርድሺን አሏት አላመኗትም
አስርዳቻቼው አላመኖትም
እናቴ ሆይ ይህ የኔ ፎቶ አይደለም ስትል አስርዳቻት
ይህ የተቀናበር ፎቶ ነው የኔ አይደለም አለቻት
ይህ ፎቶ ተቆርጦ የተቀናበር ነው ነገር ግን
እድሜውን ሙሉ ታዛዥ ልጅ ነበርች

አጭር ደብዳቤ ፃፍች
እናቴ ሆይ በአላህ ይሁንብኝ እኔ ጨዋ ነኝ
በአላህ ይሁንብኝ እኔ ጥብቅ ነኝ ከዚህ አይነቱ ተግባር
ይህ የተመለከታችሁት ፎቶ በፍጹም የኔ አይደለም
ይህንን ፃፍች እና ከቤት ጠፋች
ከሁለት ቀናት ቡሀላ እራሷን አጠፋች
ኢናሊላሂ ወኢናሊላሂ እራጅኡን
እናት አባት ሆይ እናቶች ሆይበልጆቼችሁ ጉዳይ አላህን ፍሩ ያለንበት ጊዜ አስፍሪነው
ይህ አለም እና ዘመኑ እጅግ በጣም አስፍሪነው
የሰው ሂወት እየተቀጠፍ ነው እህቶቻችን
ልጆቻችንን. ወጥመድ እየዶሏቼው ነው
በሀሰተኛ ፎቶ
አላህ በቂያችነው ምንያማር መጠጊያ መመሪያ ኢስላምን ሰቶናል
እህቴሆይ ንቂ ኒቃብሺን ልበሺ ፎቶ ሺን
በሚድያም ሆነ ለማታውቂ ሰው አትላኪ
በዚህ ዘመን የሚታመን የለም ተጠቀቂ
ውድ እህት ሆይ
አላህዘንድም የተጠላነው አላህን አናምፅው


የሰለፎች ወዳጅ ነኝ

ቴሌግራም ተቀላቀሉ ምርጥ ትምህርት


https://t.me/+wUT227opw9AwMWZk
https://t.me/+wUT227opw9AwMWZk
58 viewsبنت محمد منهج السلفية, 09:02
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-02 21:36:18 *ቀብር ውስጥ እንዴት ነን?


አንድ ባሪያ ቀብር ውስጥ ያለው ሁኔታ ልክ ቀልብ ደረት ውስጥ እንዳላት ሁኔታ ብጤ ነው!

*ሰቆቃና እስር ቤት አልያም ፀጋና ነፃነት* ★

∅ቀብርህ ውስጥ ምን አይነት ሁኔታ ላይ እንደምትሆን ለማወቅ ከፈለክ ደረትህ ውስጥ ያለችውን ቀልብህን ያላትን ሁናቴ አስተውል!★

ቀልብህ በእርጋታ፣ በንፁህነትና በኢማን ደስታ የተሞላ ከሆነ በአላህ ፍቃድ ቀብርህም ውስጥ ያለህ ሁኔታ እንደዚሁ የተረጋጋ፣ የደስታና የሀሴት ይሆናል። ቀልብህ በጥርጣሬ፣ በእርጋታ እጦትና በቆሻሻ (ክፋት፣ ቅናት ፣ምቀኝነት፣ ኩራት ....) የተሞላ ከሆነ የቀብርህ ሁኔታም እንደዚሁ አስከፊ ይሆናል። ለዚህም ነው አላህን በፍፁማዊነት አምላኪ የሆኑ ግለሰቦች ከማንም በላይ የተረጋጉ፣ ገራገር እንዲሁም እጅግ ደስተኞች ሆነው የምታገኛቸው።

☞ኢማን
ጭንቅን ያስወግዳል፤ ውጥረትን ያበርዳል፤ የተውሒድ ሰዎች የአይን ማረፊያና አላህን በብዛት አምላኪዎች ሀሴት ነው። ተስቢሕን ያዘወተረ ጭንቁን ይገላገላል። አላህን ማመስገን ያዘወተረ መልካም ነገሮች ይከታተሉለታል። ኢስቲግፋርን ያዘወተረ የተዘጉ የእዝነት በሮች ይከፈቱለታል።

ابن القيم رحمه الله
الداء والدواء (١٨٧-١٨٨)

ረይስ

https://t.me/twhidfirstt
https://t.me/twhidfirstt
87 viewsإنه بطل يخشى الله, 18:36
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-02 21:28:39 ,. .. መርዘኛው ቅጠል ጫት!


ይህ መርዘኛ ቅጠል ምነኛ ጎዳን
ወንድሞችን ሁሉ አበላሸብን
ስንት አሳቢ ወጣት አሳበደብን
በፊት የነበረውን ቀልጣፋ ፈጣን
በሌሊት ተነስቶ የሚብከነከን
ጫት በመቃም ሰበብ አጥቷል ማንነቱን
በመጥፎ ተግባር ላይ ዘፍቋል ሂዎቱን
በጫቱ ሱስ ሰበብ አቁሟል መሮጡን
ብቻ ተቀምጦ ይጠብቃል ሞቱን
ሀቋን አያሟላም ያችን ባለቤቱን
በጫት ቢዚ ሁኖ ገድሎበት ስሜቱን
ያለ መጋርጃ አሰቀምጦ ሚስቱን
ቡና ቅጅ ይላል ጠርቶ ጓደኞቹን
ይህ መረዘኛ ቅጠል አጥፍቶት ቅናቱን
መቀለቡን ትቷል ሰርቶ ቤተሰቡን
እንደውም ይመኛል ከሚስቱ ገንዘብን
ወዳ ከሰጠችው ካልሆነ ፖርሳዋን
እሷ መች አወቀኝ ዱሮ ሚስራውን
ሳያገባት በፊት ሲያስለቅስ እናቱን
በስርቆት ተሰማርቶ ሲፈትሽ ጭጎቱን
ስለዚህ እህቴም ምረጭ ባልሽን
ጫት ቃሚ እዳትመርጭ እንዳትከፍቺ በሩን
ይዘሽ እንዳትመጭ በሱስ ያበደውን
ምን ያደርግልሻል አብዶ ከጨለለ
የፍየሏን ምግብ ልሙትበት ካለ
እንደ ግመል ምንጃክ ጉንጩን ከቆለለ
አፉ ተበላሽቶ ጨጓራ ከመሰለ
ለእርኩስ ጫት ብሎ አንችን ካታለለ
የጫትን ጥፋቶች መዘርዘር ይከብዳል
ትንሽ ግን መመልከት ዛሬ ግድ ሁኗል
ሲጋራ ለማጨስ በሮችን ይከፍታል
ወደ አሰካሪ መጠጥ በግድ ይገፋፋል
በጣም ያሳዝናል ሲቀባ በኢስላም ቅብ
አላማውን ቀይረው የፍየሏን ምግብ
ሲያላምጥ ይቆያል ያለ ጌዜ ገደብ
ቁጭ ብሎ እየዋለ በጁምዓ በሮብ
ሶላትን ኢባዳን በጫማው ስር ጥሎ
የሰይጣንን ድንኳን በሀድራ ስም ተክሎ
በሱፍዮች መንሀጅ ጫት ይሻላል ብሎ
በሸርክ በቢድዓ በጫት ተጠቅልሎ
ባጥማሚ ዱዓቶች ጋርዶ ተጠልሎ
ድን እያጠፋ ነው እነሱን ተከልሎ
82 viewsبنت محمد منهج السلفية, 18:28
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-02 15:07:07 ሰርግ እና ትዳር

ሰርግ የአንድ ቀን ጉዳይ ነው። ከነመልሱ ምናምን የአንድ ሳምንት፤ ዝግጅቱን ምናምን እንጨምር ከተባለ የወራት ጉዳይ ነው።

ትዳር ግን በአላህ ፍቃድ እስከ ጀነት የሚቀጥል ትልቅ ፕሮጀክት ነው። ለሚያገባ ሰው እኮ መልካም ምኞታችንን ስንገልፅ 'መልካም ጋብቻ' እንጂ 'መልካም ሰርግ' አንልም አይደል…?

የሚገርመው ግን ዝግጅት የምናደርገው ለትዳር ህይወት ሳይሆን ለሰርጉ መሆኑ ነው። የሙሽሮች ልብስ፣ የሚጠሩ፟ ሰዎች፣ የፕሮግራሙ ቦታ፣ የምግብ አይነቶች፣ የሙሽሮች ማረፊያ፣ መልስ፣ ቅልቅል፣ የጫጉላ ሽርሽር... ሁሉም የሚመለከተውም የማይመለከተውም የሚጨነቅባቸው ነገሮች ናቸው።

ነገር ግን የትዳር ህይወት እስካሁን ከኖርኩት በምን ይለያል?
በባልና ሚስት መሀል የሚፈቀዱ ነገሮች ምን ምን ናቸው?
የሚከለከሉትስ? ምን አይነት ሚስት/ባል መሆን አለብኝ?
የባል/ሚስት ሀቆች ምን ምን ናቸው?
የመልካም ወላጅ መገለጫዎች ምን ምን ናቸው?
ልጆቼን እንዴት ማሳደግ አለብኝ?
በትዳር ውስጥ የሚከሰቱ ግጭቶችን እንዴት እንፍታ? እና ሌሎችም ለህይወቱ አሳሳቢ የሆኑ ጥያቄዎችን ማንም አያነሳም።
ቢነሱም መላሹ ብዙም አይደለም።

እና አንቺ ለማግባት እየተዘጋጀሽ ያለሽ #ልዩ_ሴት ምን ልልሽ ፈልጌ ነው… ለሰርግሽ ሳይሆን ለትዳርሽ የሚገባ፟ውን ዝግጅት አድርጊ። ትዳርሽ አላህ የሚወደውና አንቺን ደስተኛ የሚያደርግሽ እንዲሆን ለማድረግ የሚጠቅሙሽን መረጃዎች እውቀት ካላቸው ሰዎች፣ ልምድ ካላቸው ሰዎች፣ ከመፅሀፍት ፈልጊ። በትዳርሽ ደስተኛ ሁኚ እንጂ ሰርግሽ ታሪክ ነው!!
88 viewsبنت محمد منهج السلفية, 12:07
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-02 12:09:44 ከሃሜት ለመራቅ
▸▸▸▸▸▸▸▸▸▸▸▸▸▸▸▸▸▸▸▸▸▸▸▸▸▸▸▸▸▸▸▸▸▸▸▸▸▸▸▸▸▸▸▸▸▸▸▸▸
ከሃሜት ለመራቅ የሚያግዙ ⓵⓵ነጥቦች

➫ክፍል ⓻ ዱዓ

አላህ ምላሳችንን ከሃሜት እንድጠብቅልን መማፀን አንዱ ከሃሜት መራቂያ መንገድ ነው።

➫ክፍል ⓼እውነተኛ ተውበት


ለምንፈፅመው የሃሜት ጥፋት እንድሁ
የዋዛ ፈዛዛ ''አስተግፊሩላህ''ሳይሆን መስፈርት
የሚያሟላ እውነተኛ ተውበት ማድረግ ያስፈልጋል።


አንድ ሰው ያለ አግባብ የወሰደው የሰው ሐቅ ካለ በዚህ ጥፋቱ ከአላህ ፊት እንዳይጠየቅ የሚያስፈልጉ የተውበት መስፈርቶች አሉ።እነሱም


1 አላህን ብቻ በማሰብ መመለስ አኽላስ
አላህን አስቦ እስካልተመለሰ ድረስ ከጥፋቱ
መራቁ ብቻውን ቀድሞ ከተፈፀመው ጥፋት
ከመጠየቅ አያተርፈውም።
2 ስለሚፈፅመው ጥፋት መፀፀት(ጉዳዩን
አቅልሎ ሊያይ አይገባምና)
3 ከጥፋቱ ሙሉ ለሙሉ መራቅ ❨የሰው ሀቅ ካለበት መመለስ
4 ዳግም ወደዛዚያ ጥፋት ላይመለስ
ቁርጠኛ ውሳኔ ማድረግ
5 ተውበቱ የተውበት በር ባልተዘጋበት ጊዜ
ውስጥ መደረጉ ነው።

ከነዚህ መስፈርቶች አንዱን ያጓደለ ተውበቱ ትክክለኛ አይደለም።ይህንን መነሻ በማድረግ ሃሜት ላይ በወደቅን ቁጥር እውነተኛ የሆነን ተውበት ብናደርግ በቀጣይ ተመሳሳይ ጣጣ ውስጥ ላለመግባት እንጠነቀቃለን።

➫ክፍል⓽ከወንድም ክብር ላይ መከላከል ያለው ፋይዳ ማሰብ

ወንድምህ ሲታማ ከሱ መከላከላከልህ
ለአንተ ትልቅ ሽልማት አለው።
ነብዩ ከወንድሙ ክብር ላይ የተከላከለ አላህ
በቂያማ ቀን ከፊቱ እሳትን ያርቅለታል ይላሉ።

ስለዚህ ይሄ ሽልማት እንዳያመልጥህ ከወንድምህ ተከላከል።አንድ ሽልማት።ይሄ ተግባርህ ሃሜት ላይ የሚወድቅ ወንድምህንም ከጥፋት ስለሚያቅበው ሌላም ሽልማት አለህ።
ያለበለዚያ ግን ከአፍታ ቡኋላ እራስህም
የሃሜቱ አካል ሆነህ ልታገኘው ትችላለህ።

➫ክፍል ⓾ ሆደ ሰፊ መሆን፦

ለሃሜት ከሚገፉን ነገሮች አንዱ በሌሎች
ላይ የሚኖረን ቅሬታ ነው።ታጋሽ ይቅር ባይ
ብንሆን ግን ስለ ሰዎች ክፉ እንዳናስብና
በክፉ እንዳናነሳቸው ይረዳናል።

ክፍል⓵⓵ሃሜት የሚፈቀድባቸው ሁኔታዎች ጠንቅቆ መለየት


የሰዎች ድክመት ወይም ጥፋት መናገር
የሚፈቀድባቸው ወይም ግደታ
የሚሆንባቸው ውስን ሁኔታዎች እንዳሉ
የሚታወቅ ነው። እነዚያ ሁኔታዎች
ለአስገዳጅ ምክንያት ብቻ የሚፈቀዱ ስለሆነ
ያለ አግባብ እየመነዘርናቸው እንዳይሆን
መጠንቀቅ አንዱ ከሃሜት መራቂያ ስልት ነው።


አንዳንዱ በሸሪዐዊ ምክንያቶች አስታኮ የግል ቂሙን የሚያወራርድ ተያያዥነት በሌላቸው ግለሰባዊ ጉዳዮች ውስጥ ዘልቆ የሚገባ አልፎም እንደ አካላዊ ቅርፅ፣ብሄር፣ቋንቋ ወዘተ ያሉ የፈጣሪ ስጦታዎችን ሳይቀር እያነሳ የሚያንቋሽሽ ያጋጥማል።

ለዚህ አይነቱ ጥፋት ራስን መሸወድ ካልሆነ በስተቀር ሃሜት የሚፈቀድባቸው ሁኔታዎች ማጣቀስ አያዋጣም።

የአላህ ሶላትና ሰላም በነብያችን ላይ ይሆኑ

ሃሜትን መራቅ ከሚለው ከኢብኑ ሙነወር ፁሁፍ የተወሰደ


በዚህ ተጠናቀቀ።
➻➻➻➻➻➻➻➻➵➵➵
ሁላችንም እራሳችንን የምንፈትሽበት ነው ሃቂቃ አንብበው ከተጠቀሙት አላህ ያድርገን።

by ibnu Munewor hafiazohullah

ቴሌግራም ቻናል
https://t.me/abu_reyyis_arreyyis
https://t.me/abu_reyyis_arreyyis
79 viewsبنت محمد منهج السلفية, 09:09
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-01 23:49:36 =>ትዳርና ሕይወት

⇄ አሉ ባልታ በትዳር ውስጥ⇖

.አሉ ባልታ በትዳር ውሥጥ ብቻ ሳይሆን በየትኛውም የህይወት እንቅስቃሴ ውሥጥ የማናጣው የደካሞች መሳሪያ ነው ።መሠረት የለለውና ያልተጣራ ወሬ ይዘው ከወዳ ወድህ ፣የሚያዳርሱ ሰዎችን እንደመሳሪያ ተጠቅሞ ነው ሰይጣን አሉባልተኞችን የሚያጠነክረው..
በትግሥት የማይታለፍ ከሆነ አሉ ባልታ ለዓመታት የተገነባን የትዳር ጎጆ ፣ሊያዘም በልጆችና በፀጋ የተሞላን ትዳር ሲበታትን አንዳችም የርህራሄ ሰነድ የለውም ።ትኩረት ለሚሰጠው ጎጅ ነው።ምላሽ ለሚቀበለው ደግሞ ገዳይ ነው ። ይበልጥ የሚስተዋለው በባለትዳሮች ውሥጥ ነው..

» ..በተለይ በመሃል የገባ ሰው ካለ ነገሩን ለአሉባልታ የማጋለጥ እድሎ ሰፊ ይሆናል ።የዚያን የትዳር ስንጥቅ ማስፍፍትም ማጥበብም የሚችለው ከሁለቱ ተጋቢዎች ይልቅ ዳኛ ሆኖ የገባው ይኸው ሰው ነው ማለት ነው ። ስለዚህ ጋብቻ ጥላ ስር የሚኖሩ ሰዎች ከአሉባልታ ይልቅ በአንድ አንሶላ ስር የውሥጥ ሚስጥን አዋቂ ሆኖ የሚ ያድረው ወይም የምታድረው የፍቅር የጋር ሊሰሙና ሊታመኑ ይገባል...
« ቁርአን ነገር አሳባቂን በተመለከተ እንድህ ብሏል.

መሐለኛ ወራዳንም ሁሉ አትታዘዝ ሰወን አነዋሪና በማሳበቅ ኼያጅን ለበጎ ነገር በጣም ከልካይን ፣ወሰን አላፊን ኃጢአተኛንልበ ደረቅን ከዚህ በኀላ ዲቃላን ሁሉ አትታዘዝ)አል ቀለም ,10,13)
,, ዓሉባልታን የስብቀኛን ወሬን ማዳመጥ የትዳር መሰሶን ከሚያፈርሱ አደጋዎች ግባር ቀደሙ ነው ። በዓለማችን የበርካታ ሰዎችን ትዳር በተኮለኞች ፈርሷል ። የዓላህ መልክተኛ ሰለለላህ አለይሂ ወሰለም የሰዎችን ግንኙነት ማበላሸት (እምነትን የሚላጭ ተግባር ነው።ማለታቸውን አቡዳውድና ቲርሚዚ ተግበውታል..
"" ራሱን ለአሉባልታ አሻግሮ የሚሰጥ ሰው ብዙ ጊዜ ተጠርጣሪና ቀናተኛ ነው። ቅናት መኖሩ የማይከፍ የፍቅር ባህሪ ቢሆንም መስመሩን የለቀቀ ጥርጣሬ ግን ከፍይዳው ይልቅ ጎጅነቱ ጉልህ ሆኖ ነው የሚታየው ።እነሆ ቀለል ያለ #ምሳሌ, አንድ በቀናተኛ ባህሪው አገር ያወቀው ባል ሚስቱን ከአንድ ወንድ ጋ ተቃቅፍ በመሄድ ሲያልፍ ይመለከታት ኖሯል..
" ዕሱም ሚስቱን በዚህ ሁኔታ በማየቱ እጅግ ይደነግጣል ፣ራሱ ይዞርበታል ፣ካጠገባቸው ቀርቦ አንዳች እርምጃ መውሰድ ፈልጎ ነበር ። ግን ፍይዳ እንደማይኖረው በማመኑ ወደ ቤቱ አቀና ።ብዙም ሳይቆዩ እነሱም እየተሳሳቁ ወደ ቤት ገቡ
ገና ከመግባታቸው ከሳሎን ያዪት ግን ራሱን ሰቅሎ የሞተ ባሏን ነበር ።ቅናት መነሻው እንኳን ሳያጣሩ አደጋ እንድፈጠር ምክንያት የሚሆን የህይወት እሾህ መሆኑን ልብ ይላል ሚስቱ እየማገጠች አልነበረም ለአመታት በውጭ ሀገር ቆይቶ ከመጣ ወንድሟ ጋር ነበር ተቃቅፍ የተመለከታት ...እንድህ አይነት ቅናት ጤናማ ሊሆን አይችልም ።በነገራችን ላይ የኢስላም ምሉዕ ጥዑም የፍሬ ጭማቂ የተጎነጨ አማኝ በፍቅር ወይም በአንዳችን ፍጡራዊ ገጠመኝ ራሱን አያጠፍም ።ራስን መግደል የራስም ነፍስ ቢሆን መብት አይደለም ።የሰው ነብስ የአላህ ስሪት ናት አላህ ብቻ ነው ያሻውን ሊያደርጋት የሚችለው
ልብ ያለው ልብ ይበል ስንት ቤቶች ናቸው በአሉባልታ የፈረሱት ?? ቤቱ ይቁጠረው ስንቶቻችን ነን ባልተረጋገጠ ወሬ ትዳራችንን ምቅርቅሩን ያወጣን ? መልሱን ለናተው
https://t.me/joinchat/AAAAAFCDp1BWbiwkZaF8TA
75 viewsبنت محمد منهج السلفية, 20:49
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-01 18:46:20 تلاوة من سورة الفرقان
القارئ: #عبدالباري_الثبيتي
•••━══❁✿❁══━•••
81 viewsبنت محمد منهج السلفية, 15:46
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-01 16:45:20 ከሃሜት ለመራቅ
▸▸▸▸▸▸▸▸▸▸▸▸▸▸▸▸▸▸▸▸▸▸▸▸▸▸▸▸▸▸▸▸▸▸▸▸▸▸▸▸▸▸▸▸▸▸▸▸▸
➧ከሃሜት ለመራቅ የሚያግዙ ⓵⓵ነጥቦች

ከክፍል ሶስት የቀጠለ

የጓደኛ ጣጣ መቸም ሃሜት የጋራ ወንጀል2 ነው። ሀሜት የሰማ ሰው በመቃወሙ የሚከተል አደጋ ካልኖረ በስተቀር መቃወም ግደታው ነው።ይህን ያልቻለ ቢያንስ በልቡ ሊጠላ ይገባዋል።ያልበለዚያ አድማጩም እንደተናጋሪው ተጠያቂ ነው።

መቸም እራሳችንን ሆንን ጓደኛችን በቀላሉ ነገሮችን ወደ ሃሜት የሚለውጥ አይጠፉም።ይህን ችግር አስተውሎ ለህክምናው መታገል ብልሃት ነው።ችግሩ ከኛ ከሆነ ተቅዋን መላበስ ሁነኛ መፍትሔ ነው።

ከጓደኞቻችንም ለዚህ ጥፋት የሚያጋልጡንን ከቻልን ግልፅ መመካከር ኖሮ ተያይዞ ከጥፋት በመራቅ ወደ ኸይር መጓዝ ።ካልሆነ ግን በመራቅም ቢሆን ቢያንስ እራስን ከጥፋት ማትረፍ ትልቅ ብልሃት ነው።

ይሄ ውሳኔ ለአንዳንዶቻችን ትልቅ መስዋእትነት ሊጠይቅ ቢችልም የሚከተለውን መዘዝ ማሰባችን ጉዳዩን ያቀለዋል።የልብ መድረቅ ፦እንዳያውም ቁልፉ እዚህ ላይ ነው። ስለዚህ ተቅዋችን የጨመር ዘንድ ልንታገል ይገባል።

ክፍል ⓸ ሙራቀባ በእያንዳንዱ እንቅስቃሴ ላይ

ዘወትር አላህን ማሰብ ፦''ከሱ ዘንድ
ረቂብና ዐቲድ ቢኖሩ እንጂ
አንድም ንግግር አይናገርም ''የሚለውን
ቁርኣናዊ መልእክት ማሰብ ጥሩ ነው።

ክፍል ⓹ ነፍስን መቆጣርና መተሳሰብ

ህይወትን በግምት መግፋት አይገባም።ለራሳችን ከሐራም ነገሮች ያለንን ርቀት ከግደታ ነገሮች ያለንን መዘንጋት የምንገመግምበት ፋታ ልንሰጥ ይገባል።

ካልሆነ ግን እራሳችንን ሳናስተውለው በቀላሉ ከማንመለስበት ርቀት ላይ ልናገኘው እንችላለን።

ክፍል ⓺የመልካም ቀደምቶችን አርአያ መከተል

ሌላው ከሃሜት መራቂያ ብልሃት ነው ።
በዚህ ረገድ የሰለፎች አቋም ምን ይመስል
እንደነበር ተግባራዊ ተሞክሮዎችን
ማጥናት ጠቃሚ ዘዴ ነው።

➤ምን ያክል ሃሜትን ይፀየፉ እንደነበር ለሃሜተኛ ምን አይነት መልስ ይሰጡ እንደነበር መመልከት።

ይሔ ለሚያስተውል ሁሉ በራሱ ማንነት
እንደሚሸማቀቅ በማድረግ በተጨባጭ
የሚታይ ውጤት የሚያስከትል ስለሆነ
ትኩረት ሊሰጠው የሚገባ ዘዴ ነው።

◉ሃሜትን መራቅ ከሚለው የኢብኑ ሙነወር ፁሁፍ የተወሰደ።

ይቀጥላል.......
86 viewsبنت محمد منهج السلفية, 13:45
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-31 11:58:13 ከሃሜት ለመራቅ
▸▸▸▸▸▸▸▸▸▸▸▸▸▸▸▸▸▸▸▸▸▸▸▸▸▸▸▸▸▸▸▸▸▸▸▸▸▸▸▸▸▸▸▸▸▸▸▸▸
ከሃሜት ለመራቅ የሚያግዙ ⓵⓵ነጥቦች

ክፍል ሁለት❷ የሃሜትን አስከፊነት መገንዘብ

አብዛሃኞቻችን ሃሜት ምን ያክል አስከፊ እንደሆነ በሚገባ አናውቅም።አንድ ሁለት ምሳሌ ብቻ ብንመለከት የጉዳዩን አስፈሪነት ቁልጭ አድርጎ ያሳየናል።

➧ምሳሌ፦አንድ

የመጀመሪያው ሃሜት ልክ የሞተ ወንድምን ስጋ እንደመብላት ነው የሚለው ቁርአናዊ መልዕክት ነው።ትኩረት ብንሰጠው ይሔ እጅግ ቀፋፊ ነገር ነው።


እስኪ አስቡት አንድ ጨካኝ ገዢ ''ሰዎችን በሃይል እየደበደበ የሞቱ ሰዎችን ስጋ እንድበሉ አደረጋቸው''የሚል ዜና ከምስል ጋር ብንመለከት ምን ይሰማናል?!

ሰቅጫጭ ነው አይደል ?! የሆኑ ሰዎች የሰው ስጋ እየመተሩ ፣እየዘለዘሉ ሲበሉ ብንመለከትስ ምን ይሰማናል?! በቃ ጌታችንም ሃሜት ማለት
የሞተ ወንድምን ስጋ እንደመብላት ነው አለን።


ሰው ባማን ቁጥር በአይን ህሊናችን ጥርሳችን የተቦጫጨቀ የሰው ስጋ እንደያዘ ወይም እያኘከ እንደሆነ ብንስለው ዘግናኝ ምስል ይታየናል።

ኢብኑ ዐባስ ረዲየላሁ ዐንሁ እንድህ ይላሉ፦
አላህ ይህን ምሳሌ የሰጠው የሞተን መመገብ አፀያፊ የሆነ ሐራም ስለሆነ ነው።ሃሜትም እንድሁ በሃይማኖት የተወገዘ፣ከነፍስ ዘንድ የሚያፀይፍ ነው።

ምሳሌ፦ ሁለት

ነብዩ እንድህ ማለታቸው ነው። ''በእርግጥም አንድ ሰው ደንታ ሳይሰጠው በተናገረው ንግግር ሰባ አመት ወደ ጀሀነም ይምዘገዘጋል''አልባኒ ሶሂሕ ብለውታል።

ምሳሌ ሶስት
ነብዩ በሁለት ቀብሮች ዘንድ አለፉ። ሰዎቹ በቀብራቸው ውስጥ የሚቀጡ ናቸው።'አንዱ' ሰዎችን ያማ የነበረ ነው''አሉ።❮ሶሂሑል ኣዳብ አልሙፍረድ 275❯እነዚህ ምሳሌ ናቸው። ሌሎችንም አስፈሪ መረጃዎችን አልፎ አልፎ ብንመለከትና ደዕዋዎችን ብናዳምጥ ጠቃሚ ነው።

ክፍል ሶስት❸ለሃሜት የሚያጋልጡ መንገዶችን መለየት፦

በአብዛሀኛው ለሃሜት የሚያጋልጡን መንገዶች የሚከተሉት ናቸው፦ ስራ መፍታት፦ስራ ፈቶች በብዛት ሃሜተኞች ናቸው።እራሳችንን በስራ መጥመድ አንድ ከሃሜት መራቂያ ብልሃት ነው።

ስለሆነም አዕምሯችንን ስለ ሰዎች ከማሰብ ዞር ቀሚያደርጉን ስራዎች ላይ መጥመድ ፋይዳው ድርብርብ ነው። በተጨማሪም ቁርኣን በመቅራት ፣ዚክር በማድረግ፣ጠቃሚ ፁሁፎችን በማንበብ፣ሙሃደራዎች ወይም ዳዕዋዎችን በማዳመጥ ትርፍ ጊዜያችንን ከሃሜት በመራቅ በጠቃሚ ነገር ላይ ማሳለፍ እንችላለን።

ዑለማዎቻችን እንደሚሉት ምላስ በጥሩ ነገር ካልጠመድናት ያለ ጥርጥር በመጥፎ ነገር መጠመዷ አይቀርም።

ወሬ ማብዛት፦ ወሬው የበዛ ሰው ያለ ጥርጥር ለጥፋት የቀረበ ነው። ነብዩ ''ዝም ያለ ተረፈ''ይላሉ

ስለዚህ በዝምታ ውስጥ ያሉ ፋይዳዎችን ልናስተነትን ይገባል።ባጭሩ ወሬ መቀነሳችን ለሃሜት ከምንጋለጥባቸው መንገዶች ዋናውን መቀነስ ነው።

ሃሜትን መራቅ ከሚለው ከኢብኑ ሙነወር ፁሁፍ የተወሰደ።

➤ይቀጥላል.............

Ibnu munewor hafizohullah

ቴሌግራም ቻናል
https://t.me/abu_reyyis_arreyyis
https://t.me/abu_reyyis_arreyyis
116 viewsبنت محمد منهج السلفية, 08:58
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-31 08:37:03 #10_የልብ_ህመሞች

1…… በአላህ (ሱብሀነ ወተአላ) እናምናለን እንላለን ነገር ግን ትዕዛዙን አንተገብርም።

2….. ረሱልን (ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም ) እንወዳሉን እንላለን ግን የሳቸውን ፈለገ ሱናቸውን በመተግበር አልተከተልንም ።

3….. ቁርዐን እንቀራለን ነገር ግን ወደተግባር አንለውጠውም።

4….. የአላህ (ሱወ) ፀጋ ሁሌ ይደርሰናል ነገር ግን አመስጋኝ አልሆንም።

5…. ሸይጧን ጥላታችን እንደሆነ እንናገራለን ግን ከእርሱ ተቃራኒ አልቆምንም።

6…. ጀነት መግባትን እንፈልጋለን ነገር ግን ለመግቢያ የሚያግዘን ስራ እየስራን አይደለም።

7…. ጀሀንብ መግባትን አንፈልግም ነገር ግን ከሱ ለመራቅ ምንም አይነት ሙከራ አላደረግንም።

8…. ሁሉም ህይወት ያለው ነገር እንደሚሞት እናውቃለን ነገር ግን ለሞት እየተዘጋጀን አይደለም።

9…. ሰዎችን እናማለን ስህተታቸውን ለማውጣት እንጥራለን ነገር ግን የራሳችንን ጥፋትና ወንጀል እረስተናል።

10…. ሙታንን እንቀብራለን ነገር ግን ከዚህ ተግባራችን ትምህርት አንወስድም


ቻናላችን ይቀላቀላሉ



https://t.me/twhidfirstt
https://t.me/twhidfirstt
125 viewsإنه بطل يخشى الله, 05:37
ክፈት / አስተያየት ይስጡ