Get Mystery Box with random crypto!

በአዲስ አበባ የ6ኛ እና የ8ኛ ክፍል ተማሪዎች የ2016 ዓ.ም ከተማ አቀፍ ፈተና በሰኔ ወር መጀመ | Tmhrt ministers

በአዲስ አበባ የ6ኛ እና የ8ኛ ክፍል ተማሪዎች የ2016 ዓ.ም ከተማ አቀፍ ፈተና በሰኔ ወር መጀመሪያ ይሰጣል፡፡

ከተማ አቀፍ የ6ኛ እና የ8ኛ ክፍል ፈተና ትምህርት ሚኒስቴር በሚሰጠው አቅጣጫ መሰረት በዚህ ዓመት በሰኔ ወር መጀመሪያ ላይ እንደሚሰጥ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ኃላፊ ዘላለም ሙላቱ (ዶ/ር) ገልፀዋል። 

በዚህም በአዲስ አበባ ለ6ኛ ክፍል 86,691 ተማሪዎች እንዲሁም ለ8ኛ ክፍል 88,028 ተማሪዎች በከተማ አቀፍ ፈተናው ይቀመጣሉ ተብሎ እንደሚጠበቅ ተናግረዋል። 

ከመደበኛው ትምህርት ጎን ለጎን ተፈታኝ ተማሪዎችን ለከተማ አቀፍ ፈተና እንዲዘጋጁ የማብቃት ሥራ እየተሠራ እንደሚገኝም ጠቁመዋል፡፡ 

የትምህርት ሚኒስቴር ትክክለኛ የተረጋገጡ ዜናዎችን ለ ጓደኛዎ ያጋሩ

ትምህርት ሚኒስቴር

ተጨማሪ ትምህርታዊ መረጃ ለማግኘት ቻናላችን ይቀላቀሉ

https://t.me/Tmhrt_Ministers
https://t.me/Tmhrt_Ministers