Get Mystery Box with random crypto!

#ማርፈድ ¤ ምናለበት በዚህ ክረምት ዶፍ ዝናቡን ቢደፋብኝ፣ ጭቃ ድቡ አንሸራ'ቶ | ትዝታን በግጥም

#ማርፈድ

¤ ምናለበት በዚህ ክረምት
ዶፍ ዝናቡን ቢደፋብኝ፣
ጭቃ ድቡ አንሸራ'ቶ
ከወራጅ ጎርፍ ቢጨምረኝ፣
እንደ ፌስታል እንደ ቅጠል
ያ ጉሽ ውሃ በላዩ ላይ ቢያንሳፍፈኝ፤
ለምን? ካላችሁ
¤ ከ'የ ድንጋው እያማታ
ያ ማዕበል እኔን ወስዶ፣
ዶፍ ዝናቡ ሲበርድለት
ደጇ ይትፋኝ ጠዋት ማልዶ፣
ከዛ***
¤ ንጋቱ ላይ በዚያ ጭቃ በዚያ ጤዛ፣
አንገቷ ላይ ክታብ ነገር ጣል አድርጋ
ጀርባዋ ላይ ሸክላ እንስራ በ'ጇ ደግሞ ቅሏን ይዛ፤
ስትጣደፍ ወንዙን አልፋ
የምንጭ ውሃ ልትቀዳ፣
ጎርፍ ያመጣው እኔን ትየኝ
"ወይኔ" ትበል ደረት ትድቃ፤
ቀደም...
ያኔ የፍቅር ማዕበል ወስዶ~ ከእግሯ ግርጌ ሲወዝፈኝ፣
ጠዋት ማታ የሷ ሽሽት የኔ ምልጃ ሲያሰቃየኝ፣
እሺ ብትል ብትሰማ~ ከደረቷ ብትለጥፈኝ፣
ዛሬ ' የእሷ ደረት አይደቃ~ እኔም ሞቴን አልመኝ።
ዳሩ ግን..
"ጅብ ከሄደ.." ነው ተረቱ

በቁምህ ዞሮ ያላየህ~ ስትሞት እንባውን ይራጫል፤
የውስጥ የልብህን ሳያውቀው~ ከበድን ፊት ወዮ! ወዮ! ያበዛል።


ሙሉጌታ