Get Mystery Box with random crypto!

አዕምሮህን አንግሰው! ፨፨፨፨፨///////፨፨፨፨፨ አዕምሮህ ከስሜትህ መብለጥ አለበት። በስሜህ ተመ | ትዝታን በግጥም

አዕምሮህን አንግሰው!
፨፨፨፨፨///////፨፨፨፨፨
አዕምሮህ ከስሜትህ መብለጥ አለበት። በስሜህ ተመርተህ የወሰንካቸዘው መጥፎና ደካማ ውሳኔዎች አስታውስ። ስሜትህ እንድትተኛ ይገፋፋሃል፤ አዕምሮህ ደግሞ ተነስ ይልሃል።
ስሜትህ አስቂኝ ቀልድ ተመልከት ይልሃል፤ አዕምሮህ በምትኩ ስራህን ስራ ይልሃል።
ስሜትህ ያስለመድከውን የየእለት ተራ ልማድ እንድታደርግ ይገፋፋሃል፤ አዕምሮህም ወቀሳውን ይጀምራል፤ ይወቅስሃል፤ ውጤት ያለው ተግባርን እንድትፈፅም ያገፋሃል። ስሜትህ ድካምህን እንድታስታምም፣ ስነፍናህን እንድታሽሞነሙን ይፈልጋል፤ አዕምሮህ በምትኩ ከእነርሱ እንድትላቀቅ፣ በእራስህ እንድትቆም ይሞግትሃል። አዕምሮ ሲያመዛዝን ስሜት ጊዜያዊ ደስታውን ያያል፤ አዕምሮ ሲያነፃፅር ስሜት ቅፅበታዊ እረፍቱን ያስቀድማል፤ አዕምሮ ለዘላቂ ጥቅምህ ሲተጋ፤ ስሜት አሁን ከሚያገኘው ያለፈ ፍላጎት አይኖረውም።
አዎ! ጀግናዬ..! አዕምሮህን አንግሰው፤ ስሜትህን አስከትለው። አዕምሮህ ይቆጣጠርህ፤ ይመራህ ዘንድ ከፊት አስቀድመው። የስሜት ተጠቂነት ውጤቱ ግልፅ ነው። ፈቀቅ የማይል የማይዘልቅ ጊዜያዊ ደስታ፣ እረፍት ወይም ሰላም። ስሜትህ ለአሁን ካገኘ ለቦሃላ አይጨንቀውም፤ ዛሬን በልቶ ማደሩ እንጂ ነገን ስለመራብ አይጨነቅም።
አዎ! የስሜትህ መጫወቻ አትሁን፤ እንደፈለገው ሊያዝህ ቢፈልግ ለምን በል፤ በጊዜያዊ ስሜት ግዞት ለከባዱ ፀፀት እራስህን አታጋልጥ። መጥፎ ውሳኔ ያስወሰነህን፣ ስህተት ያሰራህን፣ ትርፍ አልባ ነገር ያስፈፀመህን ስሜት ከጊዜ ቦሃላ ብትፈልገው አታገኘው፤ በእርሱ ምክንያት ያጣሀውም በፀፀት መልኩ ይከተልሃል። በየደቂቃው የሚቀያየረው ስሜት አዕምሮን ስራ ያበዛበታል። ጫናውን ለመቀነስ በስሜት ሳይሆን በስሌት፣ በአዕምሮ ጥበብ፣ በሚዛናዊነት ተመራ። ስሜትህ እንዳዘዘህ በዘፈቀድ መናገር፣ መወሰን፣ ማድረግ አቁም። የስሜቱ ባሪያ ነፃነቱን አያውቅምና ከስሜት ግዞት ውጣ፤ የሚዛናዊነትን፣ የነፃነትን፣ የአላሚነትን ብርቱ አለም ተቀላቀል።
ውብ ምሽት ይሁንልን!
ምክረ-አዕምሮ ለተሻለ ነገ!

@MentalCounsel