Get Mystery Box with random crypto!

እዚህ አንቀጽ ላይ “ያጠሩታል” ለሚለው የገባው ቃል “ዩሠቢሑነ” يُسَبِّحُونَ ሲሆን ሥርወ- | Tiriyachen | ጥሪያችን

እዚህ አንቀጽ ላይ “ያጠሩታል” ለሚለው የገባው ቃል “ዩሠቢሑነ” يُسَبِّحُونَ ሲሆን ሥርወ-ቃሉ “ሠበሐ” سَبَّحَ ነው፥ ነገር ግን “ሠበሐ” سَبَّحَ ማለት “ዋኘ” ወይም “ተንቀሳቀሰ” ማለት ነው፦

"እርሱም ሌሊትንና ቀንን፣ ፀሐይንና ጨረቃንም የፈጠረ ነው፡፡ ሁሉም በፈለካቸው ውስጥ “ይዋኛሉ”፡፡"
ሱራ አል አንቢያ 21፥33

እዚህ አንቀጽ ላይ “ይዋኛሉ” ለሚለው የገባው ቃል “የሥበሑነ” يَسْبَحُونَ ሲሆን ሥርወ-ቃሉ “ሠበሐ” سَبَّحَ ነው፥ ስለዚህ “በሌሊት እና በቀንም “ይዋኙታል” ወይም “ሁሉም በፈለካቸው ውስጥ “ያጠራሉ” ብለን ብናስቀምጠው ትርጉም አልባል ነው። አንድ ቃል ብዙ ትርጉም እንዳለው እዚህ ድረስ ከተግባባን ዘንዳ ይህ በነሕው ደርሥ “ኢሥሙል ሙሽተሪክ” ይባላል፥ “ኢሥሙል ሙሽተሪክ” اِسْم المُشْتَرِك ማለት “ተመሳሳይ ቃል ግን የተለያየ ትርጉም ያለው አሳብ”Homonym” ነው። “ሶላ” صَلَّىٰ ማለት “ሰገደ” “ጸለየ” ማለት ነው፦

"የጌታውንም ስም ያወሳ እና “የሰገደ”፡፡"
ሱራ አል አእላ 87፥15

እዚህ አንቀጽ ላይ “ሰገደ” ለሚለው የገባው ቃል “ሶላ” صَلَّىٰ ሲሆን የአምልኮ ክፍል የሆነውን ሶላት ያመላክታል፥ ነገር ግን “ሶላ” صَلَّىٰ  ማለት “ባረከ” ማለት ነው፦

"አላህ እና መላእክቱ በነቢዩ ላይ የአክብሮት እዝነትን ያወርዳሉ፡፡"
ሱራ አል አህዛብ 33፥56

“የአክብሮት እዝነትን ያወርዳሉ” ለሚለው የገባው ቃል “ዩሶሉነ” يُصَلُّونَ ሲሆን “ይባርካሉ” ማለት ነው፥ ዐረቢኛ ላይ ተመሳሳይ ቃል ቢኖረው እንኳን ተመሳሳይ አሳብ እና ትርጉም አለው ማለት አይደለም። የአንድን ቃል አማራጭ ትርጉም የሚወስነው ቃሉ የሚገኝበት አረፍተ ነገር ወይም ዐውድ እንደ ሆነ ቅቡል ነው፥ መታየት ያለበት ቃሉ ብቻ ሳይሆን ቃሉ የወከለው አሳብም ጭምር ነው፥ አሏህ እና መላእክቱ ሶለዋትን የሚያወርዱት በነቢያችን ብቻ ሳይሆን በአማኞችም ላይ ጭምር ነው፦

"እርሱ ያ “በእናንተ “ላይ” እዝነትን” የሚያወርድ ነው፡፡ መላእክቶቹም እንደዚሁ፡፡"
ሱራ አል አህዛብ 33፥43

“እዝነትን የሚያወርድ” ለሚለው የገባው ቃል በተመሳሳይ “ዩሶሊ” يُصَلِّي ነው፥ አንድ አማኝ በነቢያችን ላይ ሶለዋት ሲያወርድ አሏህ በእርሱ ላይ አሥር ሶለዋት ያወርድለታል፦

"እናንተ ያመናችሁ ሆይ! በእርሱ ላይ የአክብሮት እዝነትን አውርዱ፡፡ የማክበርንም ሰላምታ ሰላም በሉ፡፡"
ሱራ አል አህዛብ 33፥56

አቢ ሁረይራህ”ረ.ዐ.” እንደተረከው፦
“የአላህ መልእክተኛ እንዲህ አሉ፦ ”በእኔ ላይ ሶለዋት ያወረደ አሏህ በእርሱ ላይ አሥር ሶለዋት ያወርድለታል”።
ጃምዒ አት-ቲርሚዚይ መጽሐፍ 3, ሐዲስ 33

እንደ ሚሽነሪዎች መጃጃል “አሏህ እና መላእክቱ ወደ ነቢዩ ይጸልያሉ ወይም ለነቢዩ ይሰግዳሉ” ካሉ አሏህ እና መላእክቱ ወደ አማኞች ሶለዋት ማውረዳቸውን ሲያውቁ “ወደ አማኞች ይጸልያሉ ወይም ለአማኞች ይሰግዳሉ” ብለው ሊረዱት ነው? “አንድ ቃልን ለሁለት የተለያዩ ነገሮችን የሚውለውን”two different things by the same word” አንድ ነገር አርጎ መውሰድ “አሻሚ ሕፀፅ”fallacy of equivocation” ነው። ለምሳሌ፦
premise 1
Since only man is rational.
premise 2
And no woman is a man.
conclusion 
Therefore, no woman is rational.
ብሎ መተርጎም አሻሚ ሕፀፅ ነው፥ በ 1ኛው ነጥብ “Man” የተባለው “ሰው”human” ሲሆን በ 2ኛው “Man” የተባለው “ወንድ”male” ነው፥ ስለዚህ አንድ ቃልን ለሁለት የተለያዩ ነገሮችን ወክሎ የሚውለውን በተቃራኒው “Man” የሚለውን “ወንድ” ብቻ ብለን ተርጉመን፦ “ወንድ ብቻውን ዐቅለኛ ነው፣ ሴት ወንድ አይደለችም፣ ስለዚህ ሴት ዐቅለኛ አይደለችም” ብሎ መረዳት በሥ-አመክንዮ ሙግት አሻሚ ሕፀፅ ነው። በተመሳሳይም “ሶላ” صَلَّىٰ ማለት “ባረከ” ማለትም ሆኖ ሳለ “ሰገደ “ጸለየ” ማለት ብቻ አርጎ መረዳት ክፉኛ ተፋልሶ”fallacy” ነው፦   

ጃቢር ኢብኑ ዐብደሏህ እንደተረከው፦ “አንዲት ሴት ለነቢዩ እንዲህ አለች፦ “በእኔ ላይ እና በባለቤቴ ላይ ሶላዋት አውርዱ” ነቢዩም ፦ “አሏህ በአንቺ ላይ እና በባለቤትሽ ላይ ሶላዋት ያውርድ” አሉ።
ሡነን አቢ ዳውድ መጽሐፍ 8, ሐዲስ 118

“ሶላ” صَلَّىٰ ማለት “ባረከ” ማለት ባይሆን ኖሮ ባርኩኝ ሲባሉ አሏህ ይባርክሽ ይሉ ነበር? ይህ መደበኛ ሕፀፅ”formal fallacy” ያለበት ኢ-ምንጨታዊ ሙግት”inductive argument” ነው፥ ምክንያቱም ሙግቱ ድምዳሜ ለማጽናት እክል ያጋጠመው ስለሆነ ነው። ቅሉ እና ጥቅሉ ግን በዚህ ዐውድ ላይ “ሶለዋት” صَلَوَات የሚለው ቃል “በረካት” بَرَكَات የሚለውን ቃል ተክቶ 
አቡ ሑመይድ አሥ-ሣዒዲይ”ረ.ዐ” እንደተረከው፦ “ሰዎች፦
“የአሏህ መልእክተኛ ሆይ! በእርሶ ላይ እንዴት ሶለዋት እናውርድ? አሉ፥ የአሏህ መልእክተኛም እንዲህ አሉ፦ “አሏህ ሆይ! ሶለዋትን በኢብራሂም ቤተሰብ ላይ እንዳወረድክ ሶለዋትን በሙሐመድ፣ በባልተቤቶቹ እና በዝርዮቹ ላይ አውርድ! በረካትን በኢብራሂም ቤተሰብ ላይ እንዳወረድክ በሙሐመድ፣ በባልተቤቶቹ እና በዝርዮቹ ላይ አውርድ! አንተ የተመሰገንክ እና የተከበርክ ነህ” በሉ።
ኢማም ቡኻርይ መጽሐፍ 60, ሐዲስ 48

ምን ትፈልጋለህ? እዚህ ዐውድ ላይ “ሶለይተ” صَلَّيْتَ የሚለው ቃል “ባረክተ” بَارَكْتَ በሚል ተለዋዋጭ ቃል መምጣቱ በራሱ ሶለዋት በረካት መሆኑን ያሳያል፥ አሏህ ሶለዋት የሚያወርደው በነቢያችን ብቻ ሳይሆን በባልተቤቶቻቸው ላይ እና በዝርያወቻቸው ላይ ጭምር መሆኑ በራሱ ሶለዋት ቡራኬን ያሳያል። 

በተጨማሪም “ወደ” የሚለው መስተዋድድ “ኢላ” إِلَى ሲሆን ለቡራኬ ጥቅም ላይ አልዋለም፥ ለቡራኬ የዋለው መስተዋድድ “ዐላ” عَلَى ማለትም “ላይ” ነው። “ላይ” ደግሞ ለሰላም፣ ለእዝነት እና ለበረከት የሚውል መስተዋድድ ነው፦

"ከአላህ ትዕዛዝ ትደነቂያለሽን የአላህ ራህመት እና በረካት በእናንተ እና በኢብራሂም ቤተሰቦች “ላይ” ይሁን! እርሱ ምስጉን ለጋስ ነውና» አሉ፡፡"
ሱራ ሁድ 11፥73

"ኑሕ ሆይ! ከእኛ በሆነ ሰላም እና በረካት በአንተ “ላይ” እና አንተም ጋር ባሉት ሕዝቦች “ላይ” በሆኑ የተጎናጸፍክ ሆነህ ውረድ፡፡"
ሱራ ሁድ 11፥48

ስለዚህ “በነቢዩ ላይ” የሚለውን “ወደ ነቢዩ” ወይም “ለነቢዩ” ብሎ መረዳት ጥራዝ ጠለቅ መረዳት ሳይሆን ጥራዝ ነጠቅ መረዳት ነው፦

"ስለዚህ “ለ-ጌታህ ስገድ” ሰዋም፡፡"
ሱራ አል ከውሰር 108፥2

እዚህ አንቀጽ ላይ “ስገድ” ለሚለው የገባው የግሥ መደብ “ሶል” صَلِّ ሲሆን ለአሏህ የሚቀርብ የአምልኮ ክፍል የሆነውን ሶላት የሚያመለክት ነው፥ የገባውም መስተዋድድ “ሊ” لِ እንጂ “ዐላ عَلَى አይደለም። ሆን ብሎ ማጣመም ዋጋ ያስከፍላል፥ የቁያማህ ቀንም ያስጠይቃል። አሏህ ሂዳያህ ይስጣችሁ! ለእኛም ጽናቱን ይስጠን! አሚን። 

“አሏሁመ ሶሊ ዐላ ሙሐመድ ወአሊ ሙሐመድ”
ٱللّٰهُمَّ صَلِّ عَلَى مُحَمَّدٍ وَآلِ مُحَمَّدٍ
“ሶለሏሁ ዐለይሂ ወሠለም”  صَلَّى ٱللَّٰهُ عَلَيْهِ وَسَلَّم 


ኡስታዝ  ወሒድ ዑመር

ለተጨማሪ ንባብ
https://tiriyachen.org/?p=4120

‐‐‐

https://fb.me/tiriyachen 
https://www.tiktok.com/@tiriyachen