Get Mystery Box with random crypto!

“አሏህ እና መላእክቱ ለነቢዩ ይሰግዳሉን?” -ሶለዋት ላይ የተነሳው ማምታቻ በአላህ ስም እጅግ በ | Tiriyachen | ጥሪያችን

“አሏህ እና መላእክቱ ለነቢዩ ይሰግዳሉን?” -ሶለዋት ላይ የተነሳው ማምታቻ

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው። 

"አላህ እና መላእክቱ በነቢዩ ላይ የአክብሮት እዝነትን ያወርዳሉ፡፡"
ሱራ አል አህዛብ 33፥56

አንድ ቃል ቋንቋዊ ፍቺው “መዕና ሉገዊይ” مَعْنًى لُغَوِيّ ሲባል ሸሪዓዊ ፍቺው ደግሞ “መዕና ሸርዒይ” مَعْنًى شَرْعِيّ ይባላል፥ አንድ ቃል ቋንቋዊ ፍቺው ሆነ ሸሪዓዊ ፍቺው ብዙ ትርጉም ይይዛል። ለምሳሌ፦ “በዐሰ” بَعَثَ ማለት “ላከ” ማለት ነው፦

"ባዩህም ጊዜ ያ አላህ መልእክተኛ አድርጎ የላከው ይህ ነውን እያሉ መሳለቂያ እንጂ ሌላ አያደርጉህም፡፡"
ሱራ አል ፉርቃን 25፥41

እዚህ አንቀጽ ላይ “ላከ” ለሚለው የገባው ቃል “በዐሰ” بَعَثَ ሲሆን “አርሠለ” أَرْسَلَ ማለት ነው፥ ነገር ግን “በዐሰ” بَعَثَ ማለት “ቀሰቀሰ” ወይም “አስነሳ” ማለት ነው፦

"ወይ ጥፋታችን! ከመኝታችን ማን ቀሰቀሰን? ይህ ያ አዛኙ ጌታ በእርሱ የቀጠረን መልክተኞቹም እውነትን የነገሩን ነው» ይላሉ፡፡"
ሱራ ያሲን 36፥52

እዚህ አንቀጽ ላይ “ቀሰቀሰ” ለሚለው የገባው ቃል “በዐሰ” بَعَثَ ሲሆን “አስነሳ” ማለት ነው፥ ስለዚህ “አላህ መልእክተኛ አድርጎ የቀሰቀሰው ይህ ነው” ወይም “ወይ ጥፋታችን! ከመኝታችን ማን ላከን” ብለን ብናስቀምጠው ትርጉም አልባ ነው። ሌላ ምሳሌ፦ “ሠበሐ” سَبَّحَ ማለት “አሞገሰ” “አመሰገነ” “አጠራ” ማለት ነው፦

"በሌሊት እና በቀንም “ያጠሩታል”፤ አያርፉም፡፡"
ሱራ አል አንቢያ 21፥20