Get Mystery Box with random crypto!

መቼም ቂል የሆነ ሰው ካልሆነ ሴት ለወንድ “እርሻ” ናት ሲባል ሞፈርና ቀንበር አዋዶ የሆነው የጓሮ | Tiriyachen | ጥሪያችን

መቼም ቂል የሆነ ሰው ካልሆነ ሴት ለወንድ “እርሻ” ናት ሲባል ሞፈርና ቀንበር አዋዶ የሆነው የጓሮ አትክልት አሊያም ሰብል ናት ማለት እንዳልሆነ እሙንና ቅቡል ነው፥ ቃሉ የወከለው እሳቤ እማሬአዊ ሳይሆን ፍካሬአዊ ነው። የሴት ልጅ ማኅፀን ዘር የሚዘራበት “እርሻ” ሲመሰል የእንሥት ማህፀን ላይ የሚገናኘው የተባእት ዘር ሕዋስ ደግሞ ገበሬ እርሻ ላይ በሚዘራው “ዘር” ተመስሏል፥ ወንድ ዘሩን ዘሪ ሲሆን ሴት ያንን ዘር የምታፈራበት እርሻ ናት። ምክንያቱም አንድ ገበሬ እርሻው ላይ ከዘራ በኃላ ዘሩ ዳብሮ ለፍሬ የሚበቃው በእርሻ ውስጥ እንደሆነ ሁሉ አንድ ተባእትም አንድ እንስት ማኅፀን ውስጥ ዘሩን ተገናኝ ሆኖ ከዘራ በኃላ ሂደቱ ሁሉ ተከናውኖ ለፍሬ የሚበቃው ማኅፀን ውስጥ ስለሆነ ነው።

ሙሉ ጽሁፉን ጥሪያችን ድረገጽ ላይ ያገኙታል።
https://tiriyachen.org/?p=3888
----------------------------
Tiriyachen|ጥሪያችን

#እርሻ
#ሴት
#ሴቶች_እርሻ_ናቸው
#ተራክቦ
#የእግዚአብሔር_እርሻ
#TiriyachenArticles

Follow us on:
----------------------------
https://fb.me/tiriyachen
https://t.me/tiriyachen
https://tiriyachen.org