Get Mystery Box with random crypto!

ትንቢተ ሕዝቅኤል 7

የቴሌግራም ቻናል አርማ tinbitehezkeyel7 — ትንቢተ ሕዝቅኤል 7
የቴሌግራም ቻናል አርማ tinbitehezkeyel7 — ትንቢተ ሕዝቅኤል 7
የሰርጥ አድራሻ: @tinbitehezkeyel7
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 745
የሰርጥ መግለጫ

#ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል።
#ፍጻሜ መጥቶአል፥ ፍጻሜ መጥቶአል፥ ነቅቶብሻል፤ እነሆ፥ ደርሶአል።
#በምድር የምትቀመጥ ሆይ፥ ተራህ ደርሶአል፥ ጊዜ መጥቶአል፥ ቀን ቀርቦአል፤ የሽብር ቀን ነው እንጂ በተራራ ላይ ያለ እልልታ አይደለም።
#አሁን በቅርብ መዓቴን አፈስስብሻለሁ፥ ቍጣዬንም እፈጽምብሻለሁ፥ እንደ መንገድሽም መጠን እፈርድብሻለሁ፥ ጕስቍልናሽንም ሁሉ አመጣብሻለሁ። ትን.ሕዝ 7÷5-8

Ratings & Reviews

2.67

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

1

3 stars

1

2 stars

0

1 stars

1


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች

2022-08-07 18:36:40 እስራኤል በጋዛ በሰነዘረችው ጥቃት የሟቾች ቁጥር 32 ደረሰ

በጥቃቱ ከ265 የሚልቁ ሰዎችም ቆስለዋል ተብሏል። ከሟቾች መካከል ሁለት የፍልስጥኤም እስላማዊ ጂሃድ ቡድን አመራሮች ይገኙበታል።
211 views15:36
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-07 18:29:15
መብረቅ
ነጩ ቤተመንግስት ከመብረቅ ለትንሽ ተረፈ። መብረቁ ከኋይት ሀውስ 100 ሜትር ርቀት ላይ ነው የወደቀው።በመብረቅ አደጋው እስካሁን 3 ሰዎች የሞቱ ሲሆን አንድ ሰው በከፍተኛ ጉዳት ውስጥ ይገኛል፡፡
በአሜሪካ አሁን ላይ እየተመዘገበ ያለው ሙቀት ባለፉት 30 ዓመታት ታሪክ ውስጥ ከፍተኛው መሆኑ ተገልጿል።
በከፍተኛ ሙቀት እና ቅዝቃዜ አየር መጋጨት ምክንያት እንደሚፈጠር የሚገለጸው መብረቅ በአሜሪካ ቁጥሩ ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጨመረ እንደሆነ የሀገሪቱ የአየር ንብረት አገልግሎት ማዕከልን ዋቢ አድርጎ ሮይተርስ ዘግቧል።
እንደ ተቋሙ ጥናት ከሆነ በአሜሪካ በዓመት በአማካኝ 40 ሚሊዮን የመብረቅ አደጋ የሚደርሱ ሲሆን አብዛኞቹ በሰዎች ላይ አደጋ አያደርሱም ተብሏል።
አላስካ እና ካሊፎርኒያ ግዛቶች በአንጻራዊነት ብዙ የመብረቅ አደጋዎች የሚደርስባቸው ግዛቶች ሲሆኑ፤ ፍሎሪዳ ደግሞ ብዙ ሰዎች በመብረቅ አደጋ የሚሞቱበት ግዛት ነው ተብሏል።
214 viewsedited  15:29
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-06 19:25:20
በአፋር ክልል ጭፍራ ወረዳ በጣለዉ ከፍተኛ ዝናብ በተለያዩ የቤት እንስሳት ላይ ከፍተኛ ጉዳት ማድረሱ ተገለጸ።

የክልሉ አደጋ መከላከልና ስጋት አመራርና ምግብ ዋስትና ማስተባበሪያ ኮሚሽን የቅድመ ማስጠንቀቂያና ፈጣን ምላሽ ዳይሬክተር አቶ አይዳሂስ ያሲንእንደገለጹት፤ ከትናንት በስቲያ ከምሽቱ 1 ሰአት ጀምሮ ሌሊቱን ሙሉ በጣለው ከፍተኛ መጠን ያለው ዝናብ ምክንያት 13 ሺህ 834 ፍየል እና በግ፣ 180 የቀንድ ከብት፣ 20 ግመሎችና 3 አህዮች ሞተዋል።@Ayu Ze habesa
263 views16:25
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-29 16:42:55
''አረማዊ የሆነው የፋሺስት መንግሥት ቤተክርስቲያንን ለማቃጠል፣ ሕዝበ ክርስቲያንን ለመግደል፣ ሃይማኖትን ለማጥፋት፣ ታሪካችንን ለማበላሸት የመጣ ነው፡ እንጂ በጎ ለመሥራት፣ እውነተኛ ፍርድ ለመስጠት ስላልመጣ ለዚህ ለግፈኛ አትገዙ፡፡ ስለ ውድ ሀገራችሁ፣ ስለ ቀናች ሃይማኖታችሁ ተከላከሉ።ነጸነታችሁን ከሚረክስ ሙታቹህ ስማችሁ ሲቀደስ ታላቅ ዋጋ ያለው ክብር ታገኛላችሁ። የኢትዮጵያ ህዝብ ለዚህ ለጠላት እንዳይገዛ አውግዣለሁ፤ የኢትዮጵያ መሬት ጠላትን ብትቀበል የተረገመች ትሁን። በፈጣሪየ በኢየሱስ ክርስቶስ ስም የተገዘተች ትሁን።''
532 views13:42
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-29 16:36:38 ከዚያም በሕዝቡ ፊት ቆመው እንዲህ አሉ፤ ፋሽስቶች የሀገራችን አርበኞች ሽፍታ ቢሏቸው እውነት አይምሠላችሁ፤ ሽፍታ ማለት ያለ ሀገሩ መጥቶ የሰውን ሀገር የሚወር፣ የሠውን እርስትና ሀብት የሚቀማ፣ ደም የሚያፈስ፣ ይህ በመካከላችሁ የቆመው አረመኔ የኢጣሊያ ፋሽስት ነው። የኢትዮጵያ ሕዝብ ለእሱ እንዳይገዛ ውግዝ ይሁን ። የኢትዮጵያ መሬት እንዳትቀበለው የተገዘተች ትሁን። ብለው አማተቡ፤ ሲጨርሱም በጨርቅ አይናቸውን እንዲሸፍኑ ጥያቄ ቢቀርብላቸውም ሞትን ፊት ለፊት ገጥሜ ድል መንሣት ስለምፈልግ ባትሸፍነኝ ደስ ይለኛል። በማለት መለሱ። ከዚያም አቤቱ እግዚአብሔር አምላኬ ሆይ የእኔን ሞት ለኢትዮጵያ ሰማዕታት ደም መፍሰስ የመጨረሻ አድርገው፤ ወገኖቼ ብዙ ሳይቀሰፉ ፀሎታቸውን ስማ። ይቅር በለን ብለው ፀሎታቸውን እንደፈፀሙ።"
417 views13:36
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-29 16:34:31
ጋዜጠኛ ጳውሎስ ኞኞ «አቡነ ጴጥሮስ እንዴት ሞቱ?» ሲል ጣልያናዊ ጋዜጠኛን ጠይቋቸው እርሳቸውም የሚከተለውን ተናግረዋል።
«አቡነ ጴጥሮስ የተገደሉ ዕለት እዚያው ነበርኩ። መጀመሪያ በእጃቸው ይዘውት የነበረውን መጽሐፍ ቅዱሳቸውን ተሳለሙት። ቀጥለውም የያዙትን መስቀል አማትበው ሕዝቡን ባረኩ። የኪሳቸውንም ሰዓት አውጥተው ካዩ በኋላ መልሰው ከኪሳቸው ከተቱት። ወዲያው ወታደሮች በእሩምታ ተኩሰው ገደሏቸው።"
ሂያጅ ተሳፋሪ፣ ሰዎች ከሆናችሁ
ኧረ ለመቼው ቀን፣ ቤት ትሠራላችሁ
መልሱን ስጡት እንጂ፣ ለምን ዝም አላችሁ
ተጣርቶ ተጣርቶ፣ ያ ሰው ሄደላችሁ።
ምንጭ፦የኢትዮጵያና የኢጣሊያ ጦርነት በጳውሎስ ኞኞ
449 views13:34
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-25 20:16:35
#አባ ማትያስ ግን አብይን ይወዱታል? መለስና አባ ጳውሎስ በጣም ይዋደዱ ነበረ ለዚያም ነው የሐዲስ አለማየሁን መፅሀፍ በተግባር የተገበሩት።
#የአሁኖቹ ግን ይህን ያህል ፍቅር ያላቸው አይመስለኝም።
575 views17:16
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-21 20:20:39
ፕሬዝዳንት ጆ ባይደን በኮሮና ቫይረስ ተያዙ!

የኃይት ኃውስ ቃል አቀባይ ጽህፈት ቤት ባወጣው መግለጫ ፕሬዝዳንቱ በኮሮና ቫይረስ ተጠቅተው የህክምና ክትትል እየተደረገላቸው መሆኑን አስታውቋል ።

ጽህፈት ቤቱ አክሎም ፕሬዚዳንት ባይደን በካንሰር በሽታ ተጠቅተዋል ተብሎ እየተሰራጨ ያለው መረጃ ሀሰት መሆኑን አክሏል።የቀድሞው የአሜሪካ ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ በዚሁ ኮሮና ቫይረስ ተጠቅተው እንደነበር ይታወሳል።

@bbc_amharic1
746 views17:20
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-17 13:47:58 በዋግኸምራ ዞን ከሚገኙ 90 ሺሕ ተፈናቃዮች መካከል በክረምት ወቅት መጠለያ ውስጥ ያሉት ሩብ የማይሞሉ ተፈናቃዮች ብቻ መሆናቸውን የዋግኸምራ ብሔረሰብ አስተዳዳር አደጋ መከላከልና ምግብ ዋስትና መምሪያ ገልጿል።

የምግብና የመጠለያ እጥረት በመከሰቱ 74 ሺሕ የሚሆኑ ተፈናቃዮች በክረምት ወቅት ከመጠለያ ውጭ መሆናቸውን የዋግኸምራ ብሔረሰብ አስተዳደር አደጋ መከላከልና ምግብ ዋስትና መምሪያ ኃላፊ ሰለሞን ንጉሥ ለአዲስ ማለዳ ተናግረዋል።
826 views10:47
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-17 13:46:38 በፖርቹጋል፣ ስፔን፣ ግሪክ እና ፈረንሳይ የተነሳው የሰደድ እሳት ከቦታ ቦታ እየተዛመተ ነው ተባለ

የሰደድ እሳቱ መነሻ በሀገራቱ ያለው ከፍተኛ የሙቀት መጠን ሊሆን እንዲሚችል ተገምቷል።

ሰደድ እሳቱን ተከትሎ እስካሁን 11 ሺህ ሰዎች ከፖርቹጋል እንዲሁም ከስፔን 2 ሺህ 300 ሰዎች ቤት ንብረታቸውን ጥለው ለመሸሽ ተገደዋል።

ከዚህም በተጨማሪ በስፔን እና ፖርቹጋል ከከፍተኛው ሙቀት ጋር በተያያዘ ከ300 በላይ ሰዎች መሞታቸው ፍራንስ-24 ዘግቧል።

አሁን ላይ በሺዎች የሚቆጠሩ የእሳት አደጋ ሰራተኞች በተለያዩ አገራት የተነሳውን የሰደድ እሳት ለማጥፋት እየታገሉ ነው።

ከማክሰኞ ጀምሮ በፖርቹጋል እስከ 47 ዲግሪ ሴንቲግሬድ ድረስ ሙቀት የተመዘገ ሲሆን፤ በስፔን ደግሞ ሙቀቱ ከ40 ዲግሪ ሴንቲግሬድ በላይ መሆኑ መረጃዎች ይጠቁማሉ።
762 views10:46
ክፈት / አስተያየት ይስጡ