Get Mystery Box with random crypto!

ነገረ መፃህፍት 📚📗📓📖

የቴሌግራም ቻናል አርማ seido27hurelhub — ነገረ መፃህፍት 📚📗📓📖
የቴሌግራም ቻናል አርማ seido27hurelhub — ነገረ መፃህፍት 📚📗📓📖
የሰርጥ አድራሻ: @seido27hurelhub
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 1.16K
የሰርጥ መግለጫ

እናነባለን ያነበብነውን እናጋራለን በመፃህፍት ስለመፃህፍት እናወራለን
✅በዚህ ቻናል ድንቃድንቅ መረጃዎች፣ ጣፋጭ ግጥሞች፣ መጣጥፍና አጫጭር ልቦለዶች፣ የረዥም ልቦለድ ትረካ እና ወጎች ግጥሞች(በድምፅ)፣ ባጠቃላይ ጥበብ እና ጥበብ ነክ ነገሮች ይቀርቡበታል። ይቀላቀሉ!
👇👇👇👇
https://t.me/seido27hurelhub
To contact me @seido11

Ratings & Reviews

3.33

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

1

4 stars

0

3 stars

1

2 stars

1

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች

2022-08-24 20:29:25
" ዓምደ - ሀገር ሼህ ዓሊ ጎንደር "  የተሰኘው የኸድር ታጁ መጽሐፍ ሽያጭ ላይ ነን ::

የኢትዮጵያን ታሪክ የጻፉ ሊህቃን፣ ከጎንደሮች ክፍለ-ዘመን(
1558-1769) የቀጠለውን እና እስከ 1855 ዓ.ል የቆየውን ጊዜ ‹ዘመነ-መሣፍንት(1769-1855)› ይሉታል፡፡ ‹ዘመነ-የጁ›ም ይባላል፡፡

ሼህ ዓሊ-ጎንደር - ከ18ኛው አጋማሽ እስከ 19ኛው ክ/ዘመን አጋማሽ ነበር የኖሩ፡፡ ወሎ ተወልደው፣ ዓለምን ዙረው፣ በጎንደር ታጠሩ፡፡ በመማር ማስተማር፣ በሥነ-ጽሁፍ፣ በኪነ-ጥበብ፣ በንግድ፣ በሥነ-ምህንድስና፣ በፍልስፍና፣ በምንፍሥና፣ በሥነ-ምድር እና በሥነ-ተፈጥሮ ምርምር፣ በውትድርና እና በአስተዳደር፣ በሌሎች መስኮች ተጨባጭ ዓለማቀፋዊና ሀገራቀፋዊ ትሩፋት አበርክተዋል፡፡ መሠረታቸው ጠብቆ፣ ልህቀታቸው ርቆ ከ፬፻(አራት-መቶ) በላይ የዓለም መዲናዎችን ጎብኝተዋል፡፡ ከሱዳን፣ ከግብጽ፣ ከቱርክ ነገሥታት ጋር ግልጽ(ነጻ) ግንኙነት ፈጥረዋል፡፡ የእንግሊዝን ንግሥት፣ የህንድን መንግሥት፣ የሱዳንን ምስለኔ በአማካሪነት አግዘዋል፡፡ ፋናቸውን በከፊል የኤሮጳና የኤዥያ አህጉራዊ ግዛቶች አዝልቀው አነጥበዋል፡፡

ለኢትዮጵያ መሣፍንትና ንጉሦች ሥነ-መንግሥታዊ ትምህርት በመስጠት፣ ገንቢ ተሞክሮና ምክር፣ ድልብ ዕውቀትና ልምድ በማካፈል ክህሎታትን አበልጽገዋል፡፡ የእርስ-በርስ ግጭቶችን በዕርቅ በማቃለል ደሚቅ አሻራ አሳርፈዋል፡፡ በአጤ ዮሐንስ-፫ኛ፣ በእቴጌ መነን፣ በራስ ዓሊ(ትንሹ/አስጘር)፣ በደጃች ጎሹ እና በአጤ ቴወድሮስ ላይ በጎ አበርክቶ አትመዋል፡፡ በሐበሻ ክርስቲያኖች መካከል “የጸጋ ልጅ”፣ “ቅባት” እና “ተዋህዶ” ተሰኝተው የተከሰቱ ልዩነቶች የእርስ-በርስ እልቂት ከማስከተላቸው በፊት፣ ጣልቃ በመግባት አሸማግለዋል፡፡ የእሥልምና ሊቃውንትን ሕብረትና አስተሳሰብ በአግራሞታዊ የተሀድሶ ሥርዓት አበልጽገዋል፡፡
152 views17:29
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-04 19:48:07
420 views16:48
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-04 19:47:39
362 views16:47
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-04 19:47:03 " ንባብ ለህይወት " በደማቅ ስነስርዓት በይፋ ተከፍቷል!!
=================================
ዛሬ በመክፈቻው ላይ መፅሐፎች እንደቆሎ ሲሸጡ ተመልክተናል!!



"ንባብ ለሕይወት" በሚል ርዕስ የመጽሐፍትና የምርምር ተቋማት የተሳተፉበት ዓውደ ርዕይ ዛሬ ከረፋዱ 5:00 ላይ ከፍተኛ የመንግስት የስራ ሐላፊዎች ምሁራን በሙያቸው የተከበሩ ታላላቅ ኢትዮጵያውያን:አንጋፋና ወጣት ደራሲያን: ገጣሚያን ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች በተገኙበት በደማቅ ሁኔታ ተከፍቷል:: ይህ ኤግዚቢሽን ከሐምሌ 28-ነሐሴ 2 ቀን 2014 ዓ ም በአዲስ አበባ ኤግዚቢሽን ማዕከል ይካሄዳል።በዚህ ፕሮግራም ላይ በመቶዎች የሚቆጠሩ አሳታሚዎች ደራሲያንና የምርምር ማዕከላት ተሳትፈውበታል:: በሚሊዮን የሚቆጠሩ ኢ ቡክስ (E-books ) በነጻ ተዘጋጅተዋል።አዳዲስ መጽሐፍት በቅናሽ ይሸጣሉ።ከገበያ የጠፉ ተፈላጊ መጽሐፍት፡ጋዜጦችና መጽሔቶችን የልጆችን የመማሪያና የተረት መጽሐፎች በኢግዚቢሽኑ ላይ ያገኛሉ።

በዚህ ኢግዚቢሽን ላይ ከ50 በላይ የአንጋፋና ወጣት ደራሲያን አዳዲስ መጽሐፍቶች ይመረቃሉ።

ኢግዚቢሽኑ እስከ ነሐሴ 2 ቀን ድረስ የሚቆይ ሲሆን መግቢያው በነፃ ነው::
292 views16:47
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-04 17:56:21
#ሁላችሁም_ተጋብዛችኋል። (በነጻ)
-----
ልዩ መርሐግብር:- መጽሐፍ የማስፈረም: ከደራስያን ጋር የመተዋወቅና የመጨዋወት ልዩ ሥነስርዓት::

የዕለቱ የክብር እንግዳ ኤፍሬም ሥዩም

የተመረጠው መጽሐፍ:- የይሁዳ ድልድይ

የመርሐግብሩ አሰናጅ:- ዛጎል የመጻሕፍት ባንክ እና ዋልያ መጻሕፍት::

ቦታ:- አራት ኪሎ: ከቱሪስት ሆቴል ጀርባ: ኢክላስ ህንጻ ዋልያ መጻሕፍት::

ቀን:- ቅዳሜ: ሀምሌ 30: 2014:: ከሰዓት በኋላ ከ10:00 እስከ 12:00 ድረስ:: (በሰዓቱ ይጀመራል)

ማስታወሻ::

1) እንዲህ ዓይነቱ ፕሮግራም ቀጣይነት ያለው ነው::

2) ከዚህ ቀደም የተደረጉ መሰል ፕሮግራሞችን ለመከታተል በዋልያ ቡክ ስቶር ቻናል ያገኙናል።

( https://m.youtube.com/channel/UCT2s8ZltG5kIS6Q1n7NGGxw
280 views14:56
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-25 17:37:14
#የመጻሕፍ_ምርቃት

ሀምሌ 21/2014

ከ 11 ሰዓት ጀምሮ

በእለቱ የድንገቴ ፈንጠዚያ እንግዳ ይኖራል።

የፕሮግሙ አዘጋጅ ደራሲ ሰብለ ደምሴ
164 views14:37
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-25 14:35:45
Ricky Jackson ይባላል። Cleveland, Ohio ነዋሪ ሲሆን ገና በለጋ እድሜው ባልሰራው ወንጀል የሞት ፍርድ ተፍርዶበት 39 አመት ከታሰረ በሁዋላ (የሞት ፍርድ የሀገሪቱ ርዕሰ ብሄር ካላፀደቁት ወደ እድሜ ልክ ይለወጣል አብዛኛውን ግዜ) ትክክለኛው ወንጀል ፈጻሚ በመገኘቱ ዳጎስ ያለ ካሳ ተከፍሎት (ነዋይ ግዜንና ሞራልን ባይመልስም) ነፃ የተለቀቀ ሰው ነው። ልክ ተለቆ ከእስር ቤት ሲወጣ ያሳሰረውን ሰው አገኘውና ... «ይቅር ብዬሃለው» .... ብሎ አቀፈው።

ቃለ መጠይቅ ላደረጉለት ጋዜጠኞች ደግሞ እንዲ ሲል ተናገረ ....«እስር ቤት ውስጥ ነህ ማለት እስረኛ ነህ ማለት አይደለም»....

☞ ነጻነት ያለው ያላችሁበት ስፍራ ላይ ሳይሆን አይምሯቹ ውስጥ ነው። የቂምና የጥላቻ እስረኛ እንዳትሆኑ ይቅር በሉ!!
ይቅር በሉ፣ መራመድ አታቁሙ ፣ ጉዳታቹ ላይ አትቆዩ! ህይወት ሰፊና ፣ ብዙ ደርዝ ያላት የጉዞ ሃዲድ ናት!!
172 views11:35
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-23 17:59:12
221 views14:59
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-21 14:03:01
296 views11:03
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-04 16:22:33
የክረምት
የሥነ - ጽሑፍ
ሥልጠና
8 ኛ ዙር ምዝገባ ጀምሯል ::
578 views13:22
ክፈት / አስተያየት ይስጡ