Get Mystery Box with random crypto!

የ2015ዓ.ም የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና የሚወስዱ ተማሪዎች ምዝገባ ከ መጋቢት 20 - ሚያዚያ | ትምህርት ሚኒስቴር

የ2015ዓ.ም የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና የሚወስዱ ተማሪዎች ምዝገባ ከ መጋቢት 20 - ሚያዚያ 15 ይከናወናል።
------------------------
የ2015ዓ.ም የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና የሚወስዱ ተማሪዎች ምዝገባ ከ መጋቢት 20 - ሚያዚያ 15,2015ዓ.ም እንደሚከናወን የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት ገለፀ።

የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት የ2015ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ፈተናን የሚወስዱ ተማሪዎች ምዝገባን በተመለከተ መግለጫ ሰጥቷል።

መግለጫውን የሰጡት የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት ዋና ዳይሬክተር እሸቱ ከበደ (ዶ/ር) የ2015ዓ.ም የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና ምዝገባ በበይነ መረብ እንደሚከናወን ገልፀዋል።

መረጃዎችን በትክክል ባለመሙላት ምክንያት የፈተና ሂደት ላይ ችግር እንደሚፈጥር የገለፁት ዋና ዳይሬክተሩ ይህንን ለማስቀረት ተማሪዎች መረጃዎቻቸውን በወቅቱ ማስመዝገብ እንዳለባቸውም ተናግረዋል።

ያልተመዘገበ ተማሪ የ 2015ዓ.ም የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተናን እንደማይፈተንም ዶ/ር እሸቱ ገልፀዋል።

በ 2014ዓ.ም በነበረው የምዝገባ ሂደት የተፈታኞች ምዝገባ መረጃ ጉድለት የነበረበት እንደነበር እና በዚህም ምክንያት የፈተና አሰጣጥ ሂደቱ የተራዘመ እንዲሆን እንዳደረገው በመግለጫው ተነስቷል ።

በመግለጫው ምዝገባው ከ መጋቢት 20 እስከ ሚያዚያ 15,2015ዓ.ም ድረስ ለመደበኛና የማታ ተማሪዎች በመንግስት የመደበኛ ትምህርት ቤቶች ለ ድጋሜ ተፈታኞች እና የርቀት ትምህርት ተማሪዎች በተመረጡ የወረዳ ትምህርትጽ/ቤቶች አማካኝነት በበይነ መረብ ብቻ እንደሚያካሂዱ ተገልጿል።

መደበኛ ተመዝጋቢዎች ከ 9-12ኛ ክፍል በተከታታይ ሲማሩ የነበሩ እና በ2015 ዓ.ም በመማር ላይ መሆን እንደሚጠበቅባቸው የተገለፀ ሲሆን
የማታ እና የርቀት ተማሪዎች የ11ኛ ክፍል ሶስት ሴሚስተር እንዲሁም ለ12ኛ ክፍል የሁለት ሴሚስተር የትምህርት ማስረጃ ማሟላት እንደሚጠበቅባቸው ተገልጿል።

ድጋሜ ተፈታኞችም ከዚህ ቀደም የተፈተኑበትን የትምህርት ማስረጃ በመያዝ መመዝገብ እንደሚችሉ ተነግሯል።

ተማሪዎች ለምዝገባ ሲመጡም ማንነታቸውን የሚገልፅ መታወቂያ በመያዝ በአካል ተገኝተው በበይነ መረብ መመዝገብ እንደሚጠበቅባቸው ተገልጿል።

በመግለጫውም ተማሪዎች፣ ወላጆች ፣ መዝጋቢዎች እና መምህራን የሚጠበቅባቸውን ሃላፊነት እንዲወጡ ጥሪ ቀርቧል።

ፈተናው የሚሰጥበት ቀንን በተመለከተም ፈተናው በዩኒቨርስቲ ውስጥ እንደሚሰጥና ቀኑ ወደ ፊት የሚገለፅ መሆኑን ዋና ዳይሬክተሩ ገልፀዋል።