Get Mystery Box with random crypto!

#Update የ2014 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ብሄራዊ ፈተና ከመስከረም 30 እስከ ጥቅምት 11/201 | መርጌታ ጥላሁን

#Update

የ2014 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ብሄራዊ ፈተና ከመስከረም 30 እስከ ጥቅምት 11/2015 ዓ.ም በሁለት ዙር እንደሚሰጥ የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት አሳውቋል።

በሁለት ዙር በሚሰጠው ፈተና ከ984 ሺህ በላይ ተማሪዎች ፈተናውን እንደሚወስዱ የአገልግሎቱ የኮሚዩኒኬሽን ጉዳዮች ዳይሬክተር ረዲ ሽፋ ለኦቢኤን ተናግረዋል።

ፈተናውን ከሚወስዱት ውስጥ 622,739 የሚሆኑት የማህበራዊ ሳይንስ ተማሪዎች ሲሆኑ ቀሪዎቹ 361,279 ፈታኞች የተፈጥሮ ሳይንስ ተማሪዎች መሆናቸውን ገልጸዋል።

የማህበራዊ ሳይንስ ተማሪዎች በመጀመሪያው ዙር ከመስከረም 30 እስከ ጥቅምት 03/2015 ዓ.ም ፈተናው እንደሚሰጣቸው ዳይሬክተሩ ተናግረዋል።

የተፈጥሮ ሳይንስ ተማሪዎች በሁለተኛው ዙር ከጥቅምት 08 እስከ 11/2015 ዓ.ም ፈተናውን እንደሚወስዱ አስረድተዋል።

የዘንድሮው ፈተና በመንግስት ዩኒቨርሲቲዎች የሚሰጥ ሲሆን ፈታኞቹም የዩኒቨርሲቲ መምህራን መሆናቸው ተገልጿል።

ፈተናው ከዚህ በፊት ይሰጥ የነበረበትን አራት ኮድ እንዲጨምር መደረጉን የገለጹት ዳይሬክተሩ፤ ፈተናው ተዘጋጅቶ እየታተመ መሆኑን ጠቁመዋል።

https://t.me/Timhrtministers