Get Mystery Box with random crypto!

#MoE የትምህርት ሚኒስቴር 'የመንግስት ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የአካዳሚክ ፕሮግራሞችና ሥርዓተ | መርጌታ ጥላሁን

#MoE

የትምህርት ሚኒስቴር "የመንግስት ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የአካዳሚክ ፕሮግራሞችና ሥርዓተ ትምህርት ቀረፃ፣ ክለሳና ማፅደቂያ መመሪያ"ን አጽድቋል።

መመሪያው የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የአካዳሚክ ፕሮግራሞችና ሥርዓተ ትምህርቶች ከዓለም አቀፍ፣ ከቀጠናዊ እና ከአካባቢያዊ የልማት አጀንዳዎች ጋር ተጣጥመው እንዲሄዱ ለማድረግ ያስችላል ተብሏል።

ሚኒስቴሩ የመንግስት ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የሚከፍቷቸውን ፕሮግራሞች ከሀገሪቱ የልማት ቀረፃና አስፈላጊነት አንፃር ተጠንተው ሲቀርቡለት አግባብነታቸውን አረጋግጦ የማጽደቅ ስልጣን እንዳለው በአዋጅ ተደንግጓል።

መመሪያ ቁጥር 917/2014 ሆኖ በፍትህ ሚኒስቴር የጸደቀውን አዲሱን መመሪያ፤ የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ተግባራዊ እንዲያደርጉ በትምህርት ሚኒስትሩ ብርሃኑ ነጋ (ፕ/ር) ተፈርሞ መሰራጨቱ ታውቋል።

አምስት ክፍሎች እና 22 አንቀጾች ያሉት አዲሱ መመሪያ፤ ከነሐሴ 01/2014 ዓ.ም ጀምሮ የጸና እንደሆነ ተደንግጓል።

(መመሪያው ከላይ ተያይዟል)
https://t.me/Timhrtministers