Get Mystery Box with random crypto!

በአስር ሺዎች የሚቆጠሩ አርጀንቲናውያን መንግሥት ለሕዝብ ዩኒቨርሲቲዎች በሚሰጠው ድጎማ ላይ ጭማሪ | Tikvah-University

በአስር ሺዎች የሚቆጠሩ አርጀንቲናውያን መንግሥት ለሕዝብ ዩኒቨርሲቲዎች በሚሰጠው ድጎማ ላይ ጭማሪ እንዲያደርግ ለመጠየቅ በሀገሪቱ መዲና ቦነስ አይረስ ሰልፍ ወጥተዋል፡፡

ባለፈው ዓመት ወደ ስልጣን የመጡት የሀገሪቱ ፕሬዝዳንት ሐብየር ሚሌይ የመንግሥትን ወጪ መቀነስ ላይ ትኩረት በማድረግ ይታወቃሉ፡፡

የመንግሥት ዩኒቨርሲቲዎች የሶሻሊስት ርዕዩተ ዓለም አስተሳሰብ መጠመቂያ ማዕከላት በመሆናቸው የበጀት ቅነሳ እንደተደረገባቸው ፕሬዝዳንቱ ገልፀዋል፡፡

ይሁን እንጂ በሀገሪቱ ምርጥ የሚባሉ የመንግሥት ዩኒቨርሲቲዎች የበጀት እጥረት ፈተና እንደሆነባቸው ይገልጻሉ፡፡ ምርጥ ከሚባሉ የሀገሪቱ ዩኒቨርሲቲዎች አንዱ የሆነው ቦነስ አይረስ ዩኒቨርሲቲ፤ የበጀት ድጎማ ጭማሪ ካልተደረገለት በበጀት እጥረት ምክንያት በሦስት ወራት ውስጥ ሊዘጋ እንደሚችል ይፋ አድርጓል፡፡

ዛሬ በሀገሪቱ መዲና ቦነስ አይረስ የተደረጉ ሰልፎች ለዩኒቨርሲቲዎቹ የሚደረግ የበጀት ድጎማ ላይ ማሻሻያ እንዲደረግ የሚጠይቁ ነበሩ፡፡ #BBC

@tikvahuniversity