Get Mystery Box with random crypto!

#MoE በሰኔ ወር 2016 ዓ.ም የሚሰጠውን የመውጫ ፈተና ለመጀመሪያ ጊዜ የሚፈተኑ ተፈታኝ ተማሪ | Tikvah-University

#MoE

በሰኔ ወር 2016 ዓ.ም የሚሰጠውን የመውጫ ፈተና ለመጀመሪያ ጊዜ የሚፈተኑ ተፈታኝ ተማሪዎች እያንዳንዳቸው የአገልግሎት ክፍያ 500.00 (አምስት መቶ) ብር ብቻ እንደሚከፍሉ ትምህርት ሚኒስቴር ለሁሉም የመንግሥት ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት በፃፈው ደብዳቤ አሳውቋል።

የዚህን ደብዳቤ ትክክለኛነትና ከደብዳቤው ጋር በተያያዘ ያላቸውን ጥርጣሬ በርካታ ተፈታኝ ተማሪዎች ለቲክቫህ ዩኒቨርሲቲ አድርሰዋል፡፡

ደብዳቤው ትክክለኛ መሆኑን ቲክቫህ ዩኒቨርሲቲ አረጋግጧል፡፡ የተገለፁትም የኢሜይል አድራሻዎች ህጋዊ የተቋሙ አድራሻዎች እንደሆኑ ለማወቅ ችለናል፡፡

Note:

#ዩኒቨርሲቲዎች ተፈታኝ ተማሪዎች የከፈሉትን ብር ሰብስበው በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ሒሳብ ቁጥር 1000553176097 ለትምህርት ሚኒስቴር ገቢ ማድረግ እንዳለባቸው ሚኒስቴሩ አሳስቧል፡፡

በተመሳሳይ ተቋማቱ ተፈታኞች የከፈሉበትን ደረሰኝ ኮፒ በኢሜይል አድራሻ antedefar@gmail.com እና lakbt2013@gmail.com መላክ ይኖርባቸዋል።

@tikvahuniversity