Get Mystery Box with random crypto!

#ጥቆማ በአዲስ አበባ ትምህርትና ስልጠና ጥራትና ቁጥጥር ባለስልጣን ፍቃዱ የታገደበት የጊብስን አ | Tikvah-University

#ጥቆማ

በአዲስ አበባ ትምህርትና ስልጠና ጥራትና ቁጥጥር ባለስልጣን ፍቃዱ የታገደበት የጊብስን አንደኛ እና መካከለኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ተማሪዎች የ6ኛ እና የ8ኛ ክፍል ክልላዊ ፈተና መውሰድ እንዲችሉ ምዝገባ እንዲያደርጉ የከተማ አስተዳደሩ ትምህርት ቢሮ ጥሪ አድርጓል፡፡

በዚህም የትምህርት ቤቱ የ6ኛ እና የ8ኛ ክፍል ተማሪዎች ምዝገባ ዛሬ ሚያዝያ 15/2016 ዓ.ም በጊብሰን የጉለሌ ብራንች መድኃኔዓለም 2ኛ ደረጃ ት/ቤት እና በጊብሰን የንፋስ ስልክ ላፍቶ ብራንች ብስራተ ገብርኤል ኢስት ዌስት አዳራሽ የሚካሔድ መሆኑ ተገልጿል፡፡

በተጠቀሱት ቦታዎች ወላጆች/አሳዳጊዎች ተማሪዎችን በመያዝ ምዝገባ በዛሬው ዕለት እንዲያካሒዱ ቢሮው አሳስቧል፡፡

@tikvahuniversity