Get Mystery Box with random crypto!

የመቐለ ዩኒቨርሲቲ ሴኔት የተቋሙ የዘንድሮ ተመራቂ ተማሪዎች በሰኔ 2016 ዓ.ም ወይም በጥር 201 | Tikvah-University

የመቐለ ዩኒቨርሲቲ ሴኔት የተቋሙ የዘንድሮ ተመራቂ ተማሪዎች በሰኔ 2016 ዓ.ም ወይም በጥር 2017 ዓ.ም የሚሰጠውን የመውጫ ፈተና ለመውሰድ በግለሰብ ደረጃ እንዲወስኑና በውሳኔያቸው መሰረት ለፈተው እንዲቀመጡ ዩኒቨርሲቲው ዕድል እንዲፈጥር
ወስኗል፡፡

በዚህም በሰኔ ወር የመውጫ ፈተና ለመውሰድ ፍላጎቱ ያላቸው ተመራቂ ተማሪዎች ስም ዝርዝር በአስቸኳይ ወደ ትምህርት ሚኒስቴር መላክ ሰላለበት ተፈታኞች እስከ ሚያዝያ 17/2016 ዓ.ም መመዝገብ ይጠበቅባቸዋል ተብሏል፡፡

በተጠቀሰው ግዜ ውስጥ ስማቸውን ያላስመዘገቡ ተመራቂ ተማሪዎች በጥር 2017 ዓ.ም ፈተናውን ለመውሰድ እንዳቀዱ ተደርጎ እንደሚወሰድ ዩኒቨርሲቲው ገልጿል።

@tikvahuniversity