Get Mystery Box with random crypto!

የራያ ዩኒቨርሲቲ አሰራርን የሚያዘምኑ ሦስት መተግበሪያዎችን የተቋሙ መምህራን እና ባለሙያዎች አበል | Tikvah-University

የራያ ዩኒቨርሲቲ አሰራርን የሚያዘምኑ ሦስት መተግበሪያዎችን የተቋሙ መምህራን እና ባለሙያዎች አበልፅገው ሥራ አስጀመሩ፡፡

የበለፀጉት መተግበሪያዎች የንብረት አስተዳደር መረጃ ስርዓት፣ የፈተና አስተዳደር ስርዓት ፖርታል እና የራያ ዩኒቨርሲቲ ድረ-ገፅ መሆናቸው ተገልጿል፡፡

መተግበሪያዎቹ ብክነት ለመቀነስ፣ ደህንነት ለማስጠበቅ፣ እንዲሁም ቀልጣፋ እና ጥራት ያለው አገልግሎት ለመስጠት ያግዛሉ ተብሏል፡፡

የፈተና አስተዳደር ስርዓት ፖርታሉን በመጠቀም ባሳለፍነው ጥር ለዩኒቨርሲቲው የ2016 ዓ.ም ዕጩ ተመራቂዎች ውጤታማ የሞዴል ፈተና ተሰጥቶ እንደነበር ተነስቷል።

@tikvahuniversity