Get Mystery Box with random crypto!

#የሥራ_ቅጥር_ጥቆማ የዲላ ዩኒቨርሲቲ ህክምናና ጤና ሳይንስ ኮሌጅ በስምንት የጤና ሙያ መስክ የሥ | Tikvah-University

#የሥራ_ቅጥር_ጥቆማ

የዲላ ዩኒቨርሲቲ ህክምናና ጤና ሳይንስ ኮሌጅ በስምንት የጤና ሙያ መስክ የሥራ መደቦች ባለሙያዎችን አወዳድሮ መቅጠር ይፈልጋል፡፡

➤ ተፈላጊ ባለሙያዎች ብዛት፦ 48
➤ የትምህርት ደረጃ፦ ከመጀመሪያ ዲግሪ ጀምሮ
➤ የሥራ ልምድ፦ ዜሮ ዓመት
➤ የሥራ ቦታ፦ ዲላ ዩኒቨርሲቲ ህክምናና ጤና ሳይንስ ኮሌጅ
➤ የማመልከቻ ጊዜ፦ ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10 ተከታታይ የሥራ ቀናት
➤ የምዝገባ ቦታ፦ አዲስ አበባ ቦሌ ርዋንዳ ኤምባሲ ፊት ለፊት በሚገኘው የዲላ የኒቨርሲቲ ጉዳይ አስፈፃሚ ጽ/ቤት ወይም ዲላ ዩኒቨርሲቲ በኦዳያአ ግቢ የሰው ኃብት አስተዳደር ቢሮ ቁ. G1/012

Note:
በድረ-ገጽ የተመዘገባችሁ አመልካቾች ለፈተና ስትጠሩ የትምህርት ማስረጃችሁንና ተያያዥ ስነዶችን ዋናውና የማይመለስ ኮፒ ይዛችህ መቅረብ ይኖርባችኋል፡፡

የትምህርት ማስረጃችሁ ከአገር ውስጥ ትምህርት ተቋማት ከሆነ ዋናውና ኮፒ እንዲሁም በውጭ አገራት ትምህርታችሁን የተከታተላቹ የአቻ ግመታ ሰነድ ማረጋገጫ ማቅረብ ይጠበቅባችኋል፡፡

ለተጨማሪ መረጃ፦ 0926208813

@tikvahuniversity