Get Mystery Box with random crypto!

#WolaitaSodoUniversity ወላይታ ሶዶ ዩኒቨርሲቲ በቅድመ እና ድኅረ ምረቃ መርሐግብር | Tikvah-University

#WolaitaSodoUniversity

ወላይታ ሶዶ ዩኒቨርሲቲ በቅድመ እና ድኅረ ምረቃ መርሐግብር ያሰለጠናቸውን 256 ተማሪዎች ነገ ሚያዝያ 5/2016 ዓ.ም ያስመርቃል።

ተማሪዎቹ ነገ በተቋሙ ዳውሮ ታርጫ ካምፓስ በሚካሔድ የምረቃ ስነ-ስርዓት እንዲመረቁ የዩኒቨርሲቲው ሴኔት በሙሉ ድምፅ አፅድቋል።

በዩኒቨርሲቲው ጤና ሳይንስና ህክምና ኮሌጅ በቅድመ ምረቃ መርሐግብር ትምህርታቸውን ያጠናቀቁና የመውጫ ፈተና ወስደው የማለፊያ ውጤት ያመጡ 32 ተማሪዎች እንደሚመረቁ ተገልጿል።

በተለያዩ የድኅረ ምረቃ መርሐግብሮች ትምህርታቸውን ተከታትለው ያጠናቀቁ 224 ተማሪዎች እንደሚመረቁ ታውቋል።

@tikvahuniversity