Get Mystery Box with random crypto!

ከ2.5 ቢሊዮን ብር በላይ በሆነ ወጪ የሕንጻዎች እና መሠረተ ልማቶች ግንባታ እያካሔደ መሆኑን ወል | Tikvah-University

2.5 ቢሊዮን ብር በላይ በሆነ ወጪ የሕንጻዎች እና መሠረተ ልማቶች ግንባታ እያካሔደ መሆኑን ወልቂጤ ዩኒቨርሲቲ ገለፀ፡፡

ዩኒቨርሲቲው በበጀት ዓመቱ 25 የተለያዩ ሕንፃዎች እና መሠረተ ልማቶች በማስገንባት ላይ ይገኛል።

ግንባታዎቹ የትምህርት ጥራትን ለማስጠበቅና የተማሪ ቅበላ አቅምን ለመጨመር የሚረዱ መሆኑን የዩኒቨርሲቲው ግንባታ ጽ/ቤት ሥራ አስኪያጅ ተስፋሁን ገብሩ ለኢፕድ ተናግረዋል፡፡

የአስተዳደር እና የተማሪዎች አገልግሎት ሕንጻዎች፣ የመማሪያ ክፍሎች፣ የተማሪዎች ዶርሚተሪዎች፣ ቤተ-ሙከራዎች፣ አይ.ሲ.ቲ. ታወሮች እና ሌሎች መሠረተ ልማቶች በግንባታው መካተታቸውን ገልፀዋል፡፡

@tikvahuniversity