Get Mystery Box with random crypto!

የኢትዮጵያ ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ተማሪዎች ኅብረት የሥራ አስፈጻሚዎች ምርጫ በመቐለ ዩኒቨርሲቲ | Tikvah-University

የኢትዮጵያ ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ተማሪዎች ኅብረት የሥራ አስፈጻሚዎች ምርጫ በመቐለ ዩኒቨርሲቲ አካሒዷል፡፡

የመቐለ ዩኒቨርሲቲ የተማሪዎች ኅብረት ፕሬዝዳንት ሐየሎም ስዩም የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ተማሪዎች ኅብረት ፕሬዝዳንት ሆኖ ተመርጧል፡፡

የሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ የተማሪዎች ኅብረት ፕሬዝዳንት ምክትል ፕሬዝዳንት እንዲሁም የጅግጅጋ ዩኒቨርሲቲ የተማሪዎች ኅብረት ፕሬዝዳንት ጸሐፊ ሆነው የተመረጡ ሲሆን ሌሎች ዘጠኝ የሥራ አስፈጻሚዎች ከተለያዩ ዩኒቨርሲቲዎች መመረጣቸውም ታውቋል።

አዲሶቹ አመራሮች ኅብረቱን ለቀጣይ ሁለት ዓመታት እንደሚያገለግሉ ተገልጿል።

@tikvahuniversity