Get Mystery Box with random crypto!

መቐለ ዩኒቨርሲቲ የሁለተኛ እና የሦስተኛ ዲግሪ ፕሮግራም የመማር ማስተማር ሒደትን በድጋሜ ለማስጀመ | Tikvah-University

መቐለ ዩኒቨርሲቲ የሁለተኛ እና የሦስተኛ ዲግሪ ፕሮግራም የመማር ማስተማር ሒደትን በድጋሜ ለማስጀመር በዝግጅት ላይ እንደሚገኝ ገለፀ።

የቅድመ ምረቃ ፕሮግራም ትምህርት እየተሰጠ እንደሚገኝ የጠቆሙት የተቋሙ የአካዳሚክ ም/ፕሬዝዳንት አብዱልቃድር ከሪም (ዶ/ር) ፤ ዩኒቨርሲቲው በአሁኑ ወቅት ከ11 ሺህ በላይ ተማሪዎች እያስተማረ ይገኛል ብለዋል።

ዩኒቨርሲቲው ያጋጠመውን የበጀት እጥረት ተቋቁሞ በቅርቡ 2,035 ተማሪዎች ማስመረቁንም አስታውሰዋል፡፡

ዩኒቨርሲቲው በቀጣይ በተለይ የምርምር እና የመዋቅር ሪፎርም ሥራዎች ላይ ትኩረት በማድረግ ወደ ተግባር እንደሚገባ ምክትል ፕሬዝዳንቱ ለኢፕድ ተናግረዋል፡፡

@tikvahuniversity